Blog Archives

አድርባይነት በየዘመን መለወጫው እንደልክፍት ብቅ ይላል!

Image may contain: text – አድርባይነት በየዘመን መለወጫው እንደልክፍት ብቅ ይላል፡፡ አብዛኞቹ አድር-ባዮች ሰብዕናን ባወጣው ዋጋ የሚሸጡ ናቸው፡፡ በዚህ ሽቀላና ደጅ-ጥናት ላይ የተሰማሩ ሁሉ፤ አቋም ለበስመ-አብ-ወልዱም ስለሌላቸው፤ አቋም ያለው አይጥማቸውም ወይም ከናካቴው ይጠላሉ፡፡ አስመሳይ ሲወራጭ አድርባይ ያጅበዋል የዘንድሮ ሰውና የዘመኑ መስተዋት ግን አልግባባ ብሏል። አገር የሚባል ድባብ የማይዋጥላቸው ወገኖች በጎሳ ተደራጅተው ስለጎሳ መብት ብቻ ተሟጋች ሆኑ። – በጥቅም የታሰሩ ሃሳብ የለሽ የሆኑ አደርባዮች ቀን ለሰጠው መልካም መደላድል ለመሆኑ ዝግጁ ናቸው፡፡ ታዛቢ ዐይን ጠያቂ ታሪክ እንዳለ ይዘነጋሉ፡፡ የዓላማ ፅናት ስለሌላቸው ፅኑዎችን ይረግማሉ፡፡ ነውርን እንደ ክብር መቁጠር ስለበዛ ነው መሰል መስታወት ፊት ቆሞ ውሎ ነውሩን ሳይሸፍን እያቅራራ ከቤት ይወጣል።ያራባናቸው ፍልፈሎች ቤታችንን ሲንዱብን አቤት ባይ፣ ማርገጃ ሥፍራ ያጣን ሆንን ጊዜው ሁሉም ራሱን አጉልቶ ለማሳየት የሚሯሯጥበት የመሆኑ ጉዳይ እጅግ እየተለጠጠ መጣ። – አገር የሚባል ድባብ የማይዋጥላቸው ወገኖች በጎሳ ተደራጅተው ስለጎሳ መብት ብቻ ተሟጋች ሆኑ። ሰውነት፣ ሰው መሆን፣ አንድ አምሳል ተረሳ። በሰውነታችን ብቻ የሚጨነቀው ፈጣሪ ብቻ ሳይሆን አልቀረም አሁንስ? ከገዛ ጎጆው ጀምሮ ፍትሕን የሚደረምስ አባወራ ስለአገር ፍትሕ ቢደሰኩር ማን ይሰማዋል? የልጆቹን እናት እየበደለ የሚኩራራ ስለሰፊው ሕዝብ በደል ቢያወራ እንዴት ሆኖ? በዘረኝነት የተለከፈ ወናፍ ‹አገሬ አገሬ› እያለ ቢያቅራራ ማን ሰምቶ? በራስ ወዳድነት አገር የሚዘርፍ ሌባ ሕዝብ ሕዝብ እያለ ቢያናፋ ማን ይቀበለዋል? አስመሳይ ሲወራጭ አድርባይ ያጅበዋል ነው የተባለው? አድርባይነት በየዘመን መለወጫው እንደልክፍት ብቅ ይላል፡፡ አብዛኞቹ አድር-ባዮች ሰብዕናን ባወጣው ዋጋ የሚሸጡ ናቸው፡፡
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሌላኛው ትኩሳት – የአሻጥር እሳት …….. የሲሚንቶና የውጪ ምንዛሬ ጥቁር ገበያውን የተቆጣጠረው የመንግስት መዋቅር ሊሰበር ይገባል ።

ሌላኛው ትኩሳት – የአሻጥር እሳት …….. የሲሚንቶና የውጪ ምንዛሬ ጥቁር ገበያውን የተቆጣጠረው የመንግስት መዋቅር ሊሰበር ይገባል ። — (ምንሊክ ሳልሳዊ) —- የኢኮኖሚ አሻጥር በመንግስት መዋቅር ውስጥ ተንሰራፍቷል።የደሕንነት ቢሮው የውስጥ ችግሩን ለመፍታት እንቅስቃሴ እያደረገ ባለበት በዚህ ወቅት ላይ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ እየተሰራ ያለውን አሻጥር እየተዘናጋበት ይመስላል። የደሕንነት ቢሮ በጄኔራል አደም ተዝረክርኮ በደመላሽ ተፍረክርኮ ባለበት ሰዓት ተመስገን ደርሶ የማስተካከያ እርምጃዎች እየወሰደ መሆኑ ቢታወቅም በመንግስት መዋቅር ውስጥ የሚገኙ ወሳኝ አካላት በጥቁር ገበያው ላይ ኔትወርካቸውን ዘርግተው የሃገሪቱን ኢኮኖሚ እያዳከሙ ነው። – ሲሚንቶ በየጫካው በድብቅ እየተዘዋወረ ነው።በገሃድ የሚታይ የኢኮኖሚ አሻጥር በጥናት ይረጋገጥ ይመስል የሃገርንም በጀት ማባከን ሌላው በሃገር ላይ የሚፈጸም አሻጥር ነው። ሃገር ውስጥ የሚመረቱ ምርቶች እንደኮንትሮባንድ ከአንድ መኪና ወደ ሌላ መኪና በጫካ ውስጥ ሲዘዋወሩ ማየት እጅግ አስደንጋጭ ነው። የሲሚንቶ ዋጋ ላይ የሚሰራው አሻጥር ለሃገር ኢኮኖሚ መዳከም አንዱ ምክንያት መሆኑ እየታወቀ ለራሳቸው መክበር ብቻ የሚፈልጉ ነጋዴዎችና ደላሎች የመንግስት ባለስልጣናት የዘረጉትን ኔትወርክ ተጠቅመው ሲሚንቶን ወደ ጥቁር ገበያ ከማምጣት አልፈው መንግስት እርምጃ እንዳይወስድ ተፅእኖ እየፈጠሩ መሆኑን ስንሰማ በመንግስትና በጸጥታ አካላቱ አፍረናል። በዚህ ላይ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች በቂ ምርት እንዳያመርቱ የተለያዩ ማነቆዎች እየተደረጉ የምርት እጥረትና የዋጋ ንረት እንዲከሰት በስፋት እየተሰራ ነው። – ሌላኛው አደገኛው የኢኮኖሚ አሻጥር እየተፈጸመ ያለው በውጪ ምንዛሬ የጥቁር ገበያ ነው። ይህ አሻጥርም በመንግስት መዋቅር ውስጥ ያሉ ጥቂቶች የሚመሩት ኔትወርክ ዶላር በመሰብሰብ ላይ ተሰማርቶ የጥቁር ገበያውን ምንዛሬ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ተገደን ነው የሚል ቀልድ አይሰራም !!!

ተገደን ነው የሚል ቀልድ አይሰራም !!! ( ምንሊክ ሳልሳዊ ) ሌላ አካል (አስገዳጅ የተባለው) በአስቸኳይ ማንነቱ ይፋ ይሁን ። የሕግ የበላይነት ማስከበር የሚቻለው ከታች እስከ ላይ ያለው ገዳይና አስገዳይ አካል ለሕዝብ ይፋ ሲወጣ ስለሆነ መንግስት ዝርዝር ማብራሪያ ሊሰጥበት ይገባል። ይህ ካልሆነ በሕግ የበላይነቱ ላይ ተፅእኖ በመፍጠር የፍርድ ሒደቱን እንደማቅለያ ሊነዳው ይችላል። በሌላ -አካል -ተገደን ነው ሰው የምናርደው ጉበት የምንበላው፣ በቀስት የምንገድለው ቆዳ ገፈን ከበሮ የምንሰራበት” እያሉ ነው። ሲጀመር ወደው እና ፈቅደው የሚፈጽሙት ተግባር ነው!! ሲቀጥል ተገደን ነው ካሉ ደግሞ ያስገደዳቸውን ከነሱው ጋር በጥምር ሕግ ፊት ሊቀርብ ይገባል። ከዚያ ውጭ “ተገደን ነው በሚል” ቀልድ ለጨፈጨፏቸው ንጹሀን ተገቢውን ቅጣት ሳያገኙ ለማድበስበስ የሚደረገው ዘመቻ ፍጹም ተቀባይነት የለውም ብቻ ሳይሆን መተከል ላይ እስካሁን በተገደሉት ከ1000 በላይ ዜጎች ደምና እና ከ100 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች ስቃይ ላይ መቀለድ ነው ። #መተከል #MinilikSalsawi #Metekel #justiceformetekelmassacre
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ዐብይ አህመድ በቀጣይ ምርጫ በድጋሜ ይመረጣሉ – ፋይናንሻል ታይምስ

ዐብይ አህመድ በቀጣይ ምርጫ በድጋሜ ይመረጣሉ – ፋይናንሻል ታይምስ – የእንግሊዙ ፋይናንሻል ታይምስ ስለ ቀጣዩ የፈረንጆቹ አዲስ አመት (2021) ትንበያውን ዛሬ በድህረገፁ አውጥቷል፡፡ Will Ethiopia’s Abiy Ahmed be re-elected ? – የኢትዮጵያ ዐብይ አህመድ (ዶ / ር) እንደገና ይመረጣሉ? https://www.ft.com/__origami/service/image/v2/images/raw/https://d1e00ek4ebabms.cloudfront.net/production/ecabb42c-0da2-48c1-b18a-73cb9e7fd8b6.jpg?source=next&fit=scale-down&quality=highest&width=720Yes, but it will be touch and go. Abiy Ahmed has pledged to hold elections in 2021. An argument over postponement because of Covid sparked a rupture with the Tigray People’s Liberation Front, which had dominated for 27 years and fashioned two decades of near double-digit growth. Mr Abiy sent troops into Tigray to quell rebellion, but now faces discontent from other regions seeking greater autonomy. Memories of the prime minister’s 2019 Nobel Peace Prize and initial adulation are fading. But odds are he will survive and press on with his vision of a liberal economy and unitary state. David Pilling – የኢትዮጵያ ዐብይ አህመድ (ዶ / ር) እንደገና ይመረጣሉ? አዎ ፣ ግን መንካት እና መሄድ ይሆናል። አብይ አህመድ እ.ኤ.አ. በ 2021 ምርጫ ለማካሄድ ቃል ገብተዋል ፡፡ በኮቪድ ምክንያት ምርጫውን ማስረዘማቸው ለ27 አመት ስልጣኑን ይዞ በደብር ዲጅት እድገት አስመዘገብኩ ከሚለው ከትግራዩ ገዢ ፓርቲ ሕወሓት ጋር ክርክር ገጥመው በጦር ያሸነፉት አብይ አሕመድ ምርጫውን በዚህ የፈረንጆች አመት እንዲካሔድ ቃል ገብተዋል።ጠ / ሚሩ ዐመፅን
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አንጋፋው የጥበብ ባለሙያ ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሰሰ ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።

ነብስ ይማር አንጋፋ አርቲስትና የጥበብ አባት ተስፋዬ ገሰሰ አንጋፋው የጥበብ ባለሙያ ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሰሰ በ84 አመት እድሜአቸው ዛሬ ታህሳስ 7 ቀን 2013 ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል። በአገር ፍቅር በብሔራዊ ትያትር ብሎም በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የባህል ተቋም ኮሌጅ አገልግለዋል። በኢትዮጵያ በኢትዮጵያ ቴሌቭዝንም በጋዜጠኝነት አገልግለዋል። በኢትዮጵያ ቀደምትና አሉ በሚባሉት በብሔራዊ ትያትርና በአገር ፍቅር ትያትር ብሎም በአዲስ አበባ ዬንቨርስቲ የባህል ማዕከል በኃላፊነት ሰርተዋል። ለሠላሳ ዓመታት ደግሞ በመምህርነት አገልግለዋል። በአዲስ አበባዉ የዩንቨርስቲ ኮሌጅ በ22 ዓመታቸዉ ትምህርታቸዉን ሲያጠናቅቁ ሕግ ባለሞያ ለመሆን ትምህርታቸዉን ለመቀጠል አስበዉ ነበር። ነገር ግን በወጣቱ ተስፋዬ ገሰሰ የመድረክ ጥበብ የተማረኩት ጃንሆይ ወጣቱን ተስፋዬን ጠርተዉ አነጋገሩት በሥራዉን አመሰገኑት የነፃ ትምህርት እድል እንዲያገኝ ትዕዛዝ አስተላለፉ፤በትያትር፤ – « ልክ ነዉ። በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ኮሌጅ ተማሪ በሆኑኩበት ጊዜ በ1950 ዓ,ም የአራተና ዓመት ትምህርቴን አጠናቅቄ ነበር። ትምህርቴን እንደጨረስኩ ተመራቂዉ ክፍል ከሌሎች ተማሪዎች ጋር በመተባበር፤ « እዮብ » የተባለ ትያትር አዘጋጀን ያኔ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ትያትር ከተከፈተ ሁለት ዓመቱ ነበር ይህ ትያትር በ 1948 ዓ,ም እንደተከፈተ ይታወሳል። ያንን ትያትር ወስደን በአዲሱ ትያትር ቤት አሳያየነዉ። እኔ መሪ ተዋናዩን ሆኜ ይህን ትያትር የሰራሁት 1950 ዓ,ም ነዉ። እኔ ደግሞ በዚህ ትያትር መሪ ተዋናዩን እዮብን ሆኜ ነበር የተጫወትኩት። ይህን ትያትር ጃንሆይ ከዘመዶቻቸዉ ከሹማምንታቸዉ ጋር ሆነዉ ተመልክተዉ በጣም ተደሰቱበት ። እናም በማግስቱ ወደ ገነተ ልዑል ቤተ መንግሥታቸዉ አሁን አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ወደ ሆነዉ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጠሚ አብይ አባይ ሚዲያ ያሉት የተዘጋውን በደሕንነት ሹሙ ጌታቸው አሰፋ የቅርብ ዘመድ የሆኑት አቶ ሐጎስ ኃይሉ የተመዘገበውን”አባይ ኤፍ ኤም 102.9″ ነው

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያሉት የተዘጋውን የ”አባይ ኤፍ ኤም 102.9″ የሚባለውን የተዘጋ ሬዲዬ ጣቢያ ነው። – “አባይ ኤፍ ኤም 102.9” ጣቢያና ኢ ኤን ኤን ቲቪ (ENN TV ) ባለቤታቸው ተመሳሳይ ነበር። የደሕንነት ሹሙ ጌታቸው አሰፋ። – የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን እ.ኤ.አ በጁን 2014 በደሕንነት ሹሙ ጌታቸው አሰፋ ትእዛዝ ካለምንም ፎርማሊቲና መስፈርት አባይ ኤፍ ኤም ለተባለው የራዲዮ ጣቢያ ፈቃድ እንዲሰጠው ተደርጓል። በወቅቱ እንደ ባለስልጣኑ መግለጫ ለአዲስ አበባ ከተወዳደሩት መካከል መስፈርቱን አሟልቶ የተገኘው አባይ ኤፍኤም 102.9 ሬዲዮ ጣቢያ ሲፈቀድለት ሁለቱ ተወዳዳሪዎች ተሰርዘዋል፡፡#MinilikSalsawi – የአባይ 102.9 ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያ ባለቤት የደሕንነት ሹሙ ጌታቸው አሰፋ የቅርብ ዘመድ የሆኑት አቶ ሐጎስ ኃይሉ ነበሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያሉት የተዘጋውን የ”አባይ ኤፍ ኤም 102.9″ የሚባለውን የተዘጋ ሬዲዬ ጣቢያ ነው። “አባይ ኤፍ ኤም 102.9” ጣቢያና ኢ ኤን ኤን ቲቪ (ENN TV ) ባለቤታቸው ተመሳሳይ ነበር። የደሕንነት ሹሙ ጌታቸው አሰፋ። #Ethiopia pic.twitter.com/WH6A5j8pfu — Minilik Salsawi 💚 💛 ❤ (@miniliksalsawi) November 30, 2020
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የአሜሪካ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ረዳት ፀሃፊ ለግጭቱ መነሻ ምክንያት፣ ለግጭቱ መስፋፋት እና ለደረሰው አሰቃቂ ጭፍጨፋ ህወሓትን ተጠያቂ አደረጉ።

የአሜሪካ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ረዳት ፀሃፊ ለግጭቱ መነሻ ምክንያት፣ ለግጭቱ መስፋፋት እና ለደረሰው አሰቃቂ ጭፍጨፋ ህወሓትን ተጠያቂ አደረጉ። Briefing With Assistant Secretary for African Affairs Tibor P. Nagy and U.S. Ambassador to Ethiopia Michael A. Raynor on the Situation in Ethiopia’s Tigray Region Tibor P. Nagy, Jr., Assistant Secretary Bureau of African Affairs Michael A. Raynor, U.S. Ambassador to Ethiopia Via Teleconference MR ICE: Thank you. Good afternoon, everyone, and thank you for joining us for this briefing on the situation in Ethiopia. I’m sure you’ve all seen Secretary’s Pompeo’s statements on the issue where the United States has clearly expressed our deep concern over the continued fighting and the situation in Ethiopia’s Tigray region. Today, I am very happy to have with us Assistant Secretary for African Affairs Tibor Nagy and the U.S. Ambassador to Ethiopia Michael Raynor, who both have extensive knowledge of Ethiopia and can share insights into the current situation, provide the U.S. perspective, and elaborate on the U.S. policy behind our current response. Assistant Secretary Nagy is going to begin with some opening remarks, and then we’re going to take a few questions. Just as a reminder, this briefing is on the record but embargoed
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኤርትራ መንግስት 16 ክፍለጦሮች አሰልፎ ወረራ አካሂዶብናል – ዶክተር ደብረጺዮን

ደብረጺዮን ራሳቸው በለኮሱት ጦርነት የመከላከያ ሰራዊቱን ሲቃ በተናነቀው እንባ ባቀረረው ድምጽ መልእክታቸው አማረሩ። የኤርትራ መንግስት 16 ክፍለጦሮች አሰልፎ ወረራ አካሂዶብናል። የመከላከያ ሰራዊት የትግራይን ሕዝብ አልጠበቀም። የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ ተደብድቧል።ሲሉ ሲቃ በተናነቀው መልእክታቸው ተናግረዋል። በኤርትራ ጦር የሐገር ሉዓላዊነትን አስደፍሯል። የመከላከያ ሰራዊቱ አልጠበቀንም። ከጠላት ከበባ አላዳነንም አልተከላከለልንም ሲሉ በምሬት እንባ ባቀረረው ድምጽ ተናግረዋል። የሰሜን እዝ አዛዦችን ግብዣ ጠርተው ካቴና ያጠለቁ መሆናቸውን በ45 ደቂቃ ኦፕሬሽን 21 አመት አብሯቸው የኖረውን የሰሜን እዝ ወረራ በመፈጸም የመከላከያ ሰራዊቱን ረሽነዋል፤ በማይካድራ ንጹሃንን ጨፍጭፈዋል፣ ይህ ሁሉ ረስተው የመከላከያ ሰራዊት ከኤርትራ ጦር ከበባ አልጠበቀንም ሲሉ ምርር ብለው ተናግረዋል። Minilik Salsawi –
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሕወሓት ….. በቀላሉ ይሰበር ዘንድ አንገቱን አደነደነው !

አጼ ልብነ ድንግል ፈጣሪዬ ሆይ ምነው ጦርነት ነፈግከኝ እያለ መሬት በጅራፍ ይገርፍ ነበር አሉ። ፈጣሪም የአጼውን ልመና ሰምቶ ግራኝ አህመድን አስነሳለት። ንጉሡ የግራኝን ጥቃት ሽሽት ገዳም ውስጥ ተደብቆ እያለ ሞተ። የህወሓት ዕብሪት የልብነ ድንግልን ታሪክ ያስታውሰኛል። “በቀላሉ ይሰበር ዘንድ አንገቱን አደነደነው” እንዲል መጽሀፍ። (ምንሊክ ሳልሳዊ) ፖለቲካው የግልባጭ ሆኖ እንዳናገኘው ፍሩ። እብሪተኝነትና ትእቢተኝነት፣ ሕዝብን መናቅና ጭካኔ ወ ጥላቻ አግጥጠው አደባባይ ወጥተዋል። በመሐሉ ሕዝብ እየተጎዳ ነው። – አሮጊቷ ሕወሓትና ጎረምሳው ብልጽግና እየተራገጡ ነው። (እውነት ከሆነ፤ ፖለቲካ እኮ ሳትፈልግ ያጠራጥርሃል። ) ፖለቲካው ግን ሲታይ ለሃገርና ለሕዝብ አደጋ ይዞ የሚመጣ ነው። በሕግ አግባብ ከሔድን የትግራይ ክልል ለፌዴራሉ መታዘዝ ግዴታ አለበት። ሌላ የፖለቲካ አላማዎች በጋራ ካልተራመዱ በቀር – (ፖለቲካ እኮ ሳትፈልግ ያጠራጥርሃል። ) ወገን በሆነው በትግራይ ሕዝብ ላይ የሚደርሰውን ጫና ለማስቀረት የሌላው ኢትዮጵያውያን ሚና ያስፈልጋል። የፌዴራል መንግስቱም በመሐል አገር በሌሎች ፖለቲከኞች ላይ የሚወስደውን እርምጃ በሕወሓት ላይ በሕግ አግባብ ሊፈፅመው ይገባል። – የሕወሓት ሰዎች በስልጣን ላይ በነበሩበትንም ጊዜ ይሁን አሁን ላወጡት ሕግ ተገዢ አይደሉም። ይህ ደግሞ ባለፉት አመታቶች ብዙ ዋጋ አስከፍሏል። መጭውም ጊዜ አደጋው ካለፈው ከተከፈለው መስእዋትነት የባሰ እንዳይሆን ሊታሰብበት ይገባል። – አጼ ቴዎድሮስ በአንድ ወቅት በውሀ ቀጠነ ሰራዊታቸውን በግራም በቀኝም እየሰደዱ ባላገሩን ፈጁት። ይህም አልበቃ ብሏቸው ልቅሶ መቀመጥ አይቻልም የሚል አዋጅ አስነገሩ። በመሀሉ የአጼው አማች ደጃች ውቤ በመሞታቸው ንጉሡ ልቅሶ ይቀመጣሉ። ይህን ጊዜ ባላገሩ እርሙን
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ቴዲ አፍሮ ማንነትን መሰረት ያደረጉ የማያባሩ ጥቃቶች መንግስት ትኩረት ሰጥቶ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጠየቀ

ቴዲ አፍሮ ማንነትን መሰረት ያደረጉ የማያባሩ ጥቃቶች መንግስት ትኩረት ሰጥቶ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጠየቀ :: ቴዲ አፍሮ በፌስቡክ ገፁ የሚከተለውን አስፍሯል  – በቅድሚያ የከበረ ሰላምታዬን እያቀረብኩ በተለያዪ የሀገራችን ክፍሎች በተደጋጋሚ ጊዜ በዜጎች ላይ አላግባብ የሚፈፀሙ ኢሰብዓዊ እና ማንነትን መሰረት ያደረጉ የማያባሩ ጥቃቶች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እጅግ ባልተገባ መንገድ ተስፋፍተው መቀጠላቸውን ተያይዞ የዜጎችን ሰላምና ደህንነት በዋናነት መጠበቅ ያለበትና ይህ ጉዳይ በቀጥታ የሚመለከተው የመንግሥት አካል ለጉዳዩ አስፈላጊውን ትኩረት ሰጥቶ አግባብ ያለዉ መንግስታዊ ሀላፊነቱን እንዲወጣና መሰል ጥቃቶች ዳግመኛ እንዳይፈፀሙ የሚጠበቅበትን የቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርግ በጥብቅ ለማሳሰብ እወዳለሁ። በዚህ አጋጣሚ በነዚህ ጥቃቆች ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች ፈጣሪ ነፍሳቸውን እንዲምር እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናት እንዲሆንላቸው ከልብ እመኛለሁ። – ፍቅር ያሸንፋል! ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን ሲቪክ ካውስንል የትራምፕ ትክክለኛ ያልሆነ ዛቻን በመቃወም ለፕሬዝዳንት ትራምፕ ይፋዊ ደብዳቤ አስገብቷል

የኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን ሲቪክ ካውስንል የፕሬዝዳንት ትራምፕ ንግግርን ተከትሎ በርካታ ኮንግረሶችን እያናገረ ይገኛል። ይህንን የትራምፕ ትክክለኛ ያልሆነ ዛቻን በመቃወም ለፕሬዝዳንት ትራምፕ ይፋዊ ደብዳቤ ዛሬ አስገብቷል  
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ወፍራም አበል የሚቆረጥላቸው የለቅሶ ደራሽ ባለስልጣናት ፕሮፓጋንዳዎች !

ወፍራም አበል የሚቆረጥላቸው የለቅሶ ደራሽ ባለስልጣናት ፕሮፓጋንዳዎች ! (ምንሊክ ሳልሳዊ) መንግስት ቅድመ መከላከል አለማድረጉ አደጋው እንዲሰፋ በማንነት ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች ተፈፅመው አማራው እንዲገደል አድርጓል። በአማራው ላይ በየክልሉ ለሚፈጸሙ ማንነትን መሰረትያደረጉ ጥቃቶች የሕዝብ ውይይቶች ሳይሆን ፖለቲካዊ ውሳኔና ፖለቲካዊ መፍትሔዎች በግድ ያስፈልጓቸዋል። – የመንግስት አካላት ጥቃቶች ከተፈጸሙ ዜጎች ከተገደሉ ንብረት ከወደመ በኃላ ለቅሶ ደራሽ ሆነው የተፈናቀለውን ሕዝብ ለማወያየት በሚል ሰበብ አበል ተቆርጦላቸው ደርሰው ይመጣሉ። የባለስልጣናት ፕሮፓጋንዳዎች – በተለያዩ አካባቢዎች ከተፈጠሩ የጸጥታ ችግሮች ጋር በተያያዘ ተሳተፈዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ታወቀ፡፡ – የተፈጸመውን ጥቃት የሚመረምር ቡድን ተዋቅሮ ወደ ስራ መግባቱ ተገለፀ። – አንድን ብሔር ከሌላ በማጋጨት ሀገር ለማፍረስ የተደረገ ሴራ ነው። እየመረመርን እርምጃ እንወስዳለን። – የማያዳግም እርምጃ እንወስዳለን። እንቅፋት የሚሆን ሚኒሻ ትጥቅ እናስፈታለን። አጣሪ ቡድንም ተቋቁሟል። እናስታጥቃለን። – የተከሰተውን የጸጥታ ችግር ለማረጋጋት እና በቀጥታም ሆነ በተለያዩ መንገዶች በተዘዋዋሪ ተሳትፎ ባደረጉ አካላት ላይ የሕግ የበላይነትን ለማስከበር የክልሉና የፌዴራል መንግስት በትኩረት እየሠሩ ነው፡፡ – እስካሁን በተሠራው የህግ ማስከበር ሥራም ተጠርጣሪዎች በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በህግ እየታዬ እንደሚገኝ ታወቀ፡፡ – አንዳንድ ቀበሌዎች ከነበረው የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ አየተሠራ ባለው የሕግ ማስከበር ሥራ የተለያዩ ተሳትፎዎችን አድርገዋል የተባሉ ተጨማሪ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡ – ያልታወቁ ታጣቂዎችና የለውጡ አደናቃፊዎችን ተደምስሰዋል፤ ላይመለሱ ተቀብረዋል፤ ሰላምና መረጋጋት ተረጋግጧል። ሠራዊታችን የውስጥ እና የውጭ ጠላቶቻችንን ለመመከት የሚያስችል አቅም አለው ወዘተ ….. –
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ስታሴር ኢትዮጵያን ወዳጅ መስላ ከጀርባ ስትወጋ አዲስ አይደለችም።

አንድነታችንን ማሳየት የዜግነት ግዴታችን ነው !!! አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ስታሴር ኢትዮጵያን ወዳጅ መስላ ከጀርባ ስትወጋ አዲስ አይደለችም። – ትራምፕ – ኢትዮጵያ ግድቡን መገንባት አልነበረባትም ፣ ድርድሩን ማፍረስ አልነበረባትም። በዚህም ገንዘብ ከልክለናቸዋል። ግብጾች ደስተኞች አይደሉም፤ ግድቡን ያፈነዱታል …… ስምምነት እንዲደርሱ አድርጌ ነበር ኢትዮጵያ ግን ስምምነቱን ጥላ ወጣች ያን ግን ማድረግ አልነበረባቸውም። ትልቅ ስህተት ነው የሰሩት። በዚህም ብዙ እርዳታ አቋርጠንባቸዋል። ለስምምነቱ ተገዢ እስካልሆኑ ድረስ ያን ገንዘብ መቼም አያገኙትም። ትራምፕ ከእስራኤል እና ሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትሮች ጋር ባደረገው ውይይት ላይ የተናገረው – አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ስታሴር ኢትዮጵያን ወዳጅ መስላ ከጀርባ ስትወጋ አዲስ አይደለችም። በቅኝ ግዛት ወቅቶች ጀምሮ በሶማሌ ጦርነት ቀጥሎ የኢትዮጵያ አንድነት እስከመፈታተን ድረስ ተጉዛ ዛሬ ላይ የሕዳሴው ግድብ ላይ ጥርሷን በመንከስ ከግብጽ ጎን መቆሟን አሳይታናለች።ይህ ትልቅ ድፍረት ነው። ሰውየው የሚያወራውን አያውቅም፣ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን በእንዲህ አይነት ሀላፊነት የጎደለው አነጋገር ፍርሀት አይገባቸውም፣ ታሪክ ሁሉንም ያስተምራል። – አያት ቅድመ አያቶቻችን በቅኝ ገዢዎችና በወራሪዎች ላይ በ አንድነት ዘምተው ያስመዘገቡትን ድል እኛም በዚህ ዘመን በዓንድነት ቆመን በመድገም አሜሪካንን ማሳፈር አለብን። በሃገር ውስጥ እና በውጪ ሐገር የምንኖር ኢትዮጵያውያን አንድነታችንን በማሳየት የሕዳሴውን ግድብ በመጨረስና የከለከሉትን እርዳታ እጥፍ እጥፉን በማምረት በራሳችን መኖር እንደምንችል ማሳየት አለብን ። ድር ቢያብር አንበሳ ያስር !!! #MinilikSalsawi –
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በቤንሻንጉል ጉሙዝ የክልል፣ በመተከል የዞንና የወረዳ አመራሮች ለፍርድ መቅረብ አለባቸው

ከኃላፊነት በማንሳት ሌላ የስልጣን ሽግሽግ ውስጥ መክተት ሳይሆን በሕግ ፊት አቅርቦ መቅጣት ለሌላው መማሪያ ነው። …. ለአከባቢው ሰላምና ለዜጎች ደሕንነትም ፖለቲካዊ መፍትሔና ውሳኔ ግድ ይላል። – በመተከል ዞን በተከሰተው የፀጥታ ችግር ውስጥ እጃቸው ያለባቸውና በቸልተኝነት ኃላፊነት በአግባቡ ባልተወጡ ከክልል እስከ ወረዳ ያሉ አመራሮች ህጋዊና ፖለቲካዊ እርምጃ ተወስዶባቸዋል። የሚሉ ዘገባዎች ከመንግስት የመገናኛ ብዙሃን እየሰማን ነው። – እነዚህ እርምጃ የተወሰደባቸው በተለይ የስልጣን ሽግሽግ ተደርጎላቸው በመንግስት ወንበር ላይ እንዲቀመጡ የተደረጉት ባለስልጣናት በቤንሻንጉል ለተከሰተው የጸጥታ ችግር መግደልና ማፈናቀል ሚና ሲጫወቱ የነበሩ መሆኑን ካሁን ቀደም ሰምተናል። ባለስልጣናቱ በተለይ በፖለቲካው መስክ የጸጥታና ደሕንነት ባለስልጣናት የክልሉ ሰላም ደፍርሶ ዜጎች ላይ ሰቆቃ እንዲፈጸም ወንጀል ሲሰሩ እንደነበር በተደጋጋሚ መረጃዎች እና የአከባቢው ነዋሪዎች ጠቁመዋል። – የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልልና የመተከል ዞን እንዲሁም ወረዳዎች አመራሮች ተነስተዋል መባሉ መልካም ነው። ይሁንና አብዛኛዎቹ በሕግ መጠየቅ ያለባቸው ናቸው። እንደ አበራ ባያታ የመሳሰሉት ሰዎች በርካታ ጭፍጨፋዎች ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እጃቸው አለበት የሚባሉ ሰዎች ከአንዱ ስልጣን ወደሌላኛው መዘዋወር ሳይሆን ለፍርድ ነው መቅረብ ያለባቸው! – ችግሩን በመፍታት ማስተማር ካስፈለገ በቤንሻንጉል ጉሙዝ የክልል፣ በመተከል የዞንና የወረዳ አመራሮች ለፍርድ መቅረብ አለባቸው። በሌላ በኩል መተከል ዞንና ወረዳዎች ላይ አመራር ሲነሳ፣ ሕዝቡን በሚወክል መልኩ እንጅ ሕዝብን በሚያስጠቃው አሰራር መሰረት አመራር ይተካ ከተባለ መፍትሔ ሊሆን አይችልም። ትልቁ መፍትሔ ሕዝቡ ተገቢውን ውክልና እንዲያገኝ ማድረግ በመሆኑ አንዱን አንስቶ ዝም ብሎ በቆየው አሰራር ሌላውን መተካት
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አፋር ቀጣዩን ሱልጣን ልትሾም ተዘጋጅታለች

አፋር/አውሳ ቀጣዩን ሱልጣን ልትሾም ተዘጋጅታለች።- ምንሊክ ሳልሳዊ በቅርቡ በሞቱት በአፋር ሱልጣን ሐንፍሬ አሊሚራህ ሐንፍሬ ምትክ የአፋር ሕዝብ ቀጣዩን ሱልጣን ሹመት ለመቀበል መዘጋጀቱ ተሰምቷል:: በቀጣይ አውሳ መሪዋን በአለም አደባባይ ፊት ትሾማለች። ለዚህም ቀጣይ እጩ ከ2004 ተለይቶ ለምትክነት አጭታለች። የአሜሪካዊ ጥምር ዜግነት ባለቤት የሆነው አፋርን ከአሜሪካ ዝሪያ ጋር አዋህዶ ከአሜሪካዊት ባለቤቱ የዘጠኝ ልጆች ባለቤት የሆነው የ65 አመቱ አህመድ አሊሚራህ በቀጣይ ወራቶች ውስጥ የሱልጣንነት ባለሽሙቱን ከአፋር ህዝብ እጅ የሚረከብ ይሆናል። አህመድ አሊሚራህ የአፋር ነፃ አውጪ ድርጅት ALFን የወታደራዊ ክንፍ በመምራት በአፋምቦ ኦብኖ ፣ በኤሊዳአር ኡሙሌይታ ፣ ከአሳኢታ ገማሪ አካባቢዋ ከደርግ ጋር የተደረጉ ጦርነትን ከ1967_1973 ድረስ በአውሳ ተራሮች ጉያዎች ተቀምጠው በአውሮፓና አሜሪካ የኖሩትን ቅንጦ ህይወት ረስተው ታግለው ያታገሉ ከፍተኛ ውጤት በደርጎች ላይ የተመራበት ጦርነት የመሩ ጀግና ታጋይ ናቸው። የሽግግር መንግስት ስቋቋም የሽግግሩ ምክርቤት አባል በመሆን ያገለገሉ ሲሆን በከፍተኛ ት/ት በአሜሪካን ዩንቨርስቲ የተመረቁ ባለብዙ ልምድ ባለቤት የሆኑ ጀግና ናቸው። ዛሬ ላይ በሳዑዲና በአሜሪካን ምድር መኖሪያ አድርገው ነው የሚኖሩት። ለማንኛውም አውሳ በቀጣይ ሱልጣን አህመድ አሊሚራህን ለመቀበል ለማሾም በጉጉትና በናፍቆት ትጠበበቃለች። ( ምንሊክ ሳልሳዊ )
Posted in Amharic News, Ethiopian News

መስከረም ሁለት የአብዮት በዓል በነበር ከቀሩ ባለታሪክ ቀኖች አንዱ

ኢትዮጵያ ትቅደም ! ….. ያለምንም ደም ! …… አቆርቋዥ ይውደም ! … መስከረም ሁለት የአብዮት በዓል በነበር ከቀሩ ባለታሪክ ቀኖች አንዱ – መስከረም 2 ሰው ጎዳና የሚሞላበት የፌሽታ ቀን ነበር፡፡ ዛሬ አብዮት አደባባይ ቦታው እንጂ ስሙ የለም፡፡ ዛሬ ይሄ ግዙፍ የሀገሪቱ ጎዳና ደመራ ሲበራ ብቻ የሚደምቅ ስፍራ ሆኗል፡፡ ዛሬ መስከረም ሁለተኛው ቀን የበዓል ማግስት ብቻ ሆኖ በሌላ ትውልድ በአንጎቨር ሳቢያ እስከ ረፋድ የሚተኛበት ቀን ሆኖ አርፏል፡፡ ትናንትና በዚህ ቀን ማንም አይተኛም፤ መስከረም ሁለት በዘመኑ ማልዶ የሚቀሰቅስ የክት ቀን ነበር፡፡ ቀን ቀንን ጣለው፤ መስከረም ሁለት ከደመቀው ክቡሩ ወርዶ የዘመን መለወጫው ማግስት ሆነ፡፡ዛሬ ተራ ቀን ሆነ፡፡ – ዛሬ ግን መስከረም ሁለት ቀን ነበር፡፡ በነበር ከቀሩ ባለታሪክ ቀኖች አንዱ መጨረሻው ይኽው የአዲስ ዓመት ማግስት ሆኖ ቀረ፡፡ በዘመኑ መስከረም ሁለት ማግስት አልነበረም፡፡ ይልቁንም መስከረም አንድ ዋዜማ ነበር፡፡ . ሀገር ዳሷን ጥላ ሽር ጉድ የምትልበት ቀን መስከረም ሁለት እንዳልነበር ዛሬ ይህ ቀን የአዲሱ ዓመት ድባብ ሲነጋ የሚያንዣብብበት ሆነና አረፈው፡፡ መስከረም ሁለት ባለ አደባባይ ነው፡፡ . መስከረም ሁለት ሰው ጎዳና የሚሞላበት የፌሽታ ቀን ነው፡፡ መስከረም ሁለት ሰማያዊ ለባሽ ኮሚኒስቶች ከፍ ካለው ስፋራ ቆመው ግራ እጃቸውን ወደ ሰማይ የወረወሩበት የደስታ ቀን ነው፡፡ ዛሬ አዘቦት ሆኗል፡፡ ተራውን ለነ ግንቦት ሃያ የሰጠ መጻተኛ ቀን፤ በዚህ ሰዓት በዚያ ዘመን ራዲዮ ስለ ድል ያወራል፡፡ ጥላሁን ገሰሰ ይለያል ዘንድሮ ይላል፡፡ ከያኒያን አብዮቱን
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የአመቱ በጎ ሠው! መሐመድ አል አሩሲ

የአመቱ በጎ ሠው! መሐመድ አል አሩሲ …. እንኳን ደስ አለህ ! – ፖለቲከኛው ስልጣን አክቲቪስቱ ጥቅማ ጥቅም በሚፈልግበት ሃይማኖተኛው አስመሳይና አጨብጫቢ በሆነበት በዚህ ወቅት ስለሐገር የቆመ ሰው ማግኘት መታደል ነው። – መሀመድ አልአሩሲ محمد بن محمد العروسي ለኢትዮጵያ ስለኢትዮጵያ ኢትዮጵያዊነትን ያላጓደለ ከታላቅም አልፎ ታላቅ ስለሐገር ደሕንነትና ልማት ሰላምና ብሔራዊ ጥቅም በግንባር ቀደምትነት ታላቅ ስራ እየሰራ የሚገኝ ውድ ኢትዮጵያዊ ነው። ፖለቲከኞች የውስጥ ቀውስን ተገን አድርገው ከውጪ ኃይሎች ጋር በሚያሴሩበት ዘመን ጋዜጠኛ፣ የፖለቲካ ተንታኙና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ መሐመድ አል አሩሲ ግን ሐገራችንን ለመበጥበጥ የሚያሴሩ የውጪ ኃይሎችን ፊት ለፊት የተጋፈጠ እንቁ ኢትዮጵያዊ ነው። – ሃገር እንምራ ሕዝብ እናስተዳድር የሚሉ ፖለቲከኞች ስለሐገርና ሕዝብ ጥቅም ቆመናል ብለው ጥቅማቸውን የሚያደላድሉ አክቲቪስቶችንና ስማቸው የማይጠቀስ ምናምናቸውን ሽፋን አድርገው የሚያጨበጭቡትን አቅፈን እርር ድብን በምንልበት በዚህ ወቅት ስለሕዳሴው ግድብና ስለ አባይ ወንዝ ባለቤትነታችን ጠላቶቻችንን ፊት ለፊት በመቅረብ በዓለም ሚዲያዎች ፊት ያሳፈረልን ውድ ወንድማችን ዜጋችን የኢትዮጵያዊነት ድምቀታችን ነው ሰው የጠፋ እለት ሰው ሆኖ የተገኘ መሐመድ አል አሩሲ።#MinilikSalsawi –
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አሜሪካ ለኢትዮጵያ የምታደርገው ድጋፍ በከፊል እንዲቆም ወሰነች – ፎሬይን ፖሊሲ

አሜሪካ ለኢትዮጵያ የምታደርገው ድጋፍ በከፊል እንዲቆም ወሰነች – ፎሬይን ፖሊሲ መፅሄት – ፎሬይን ፖሊሲ የተሰኘው መፅሄት ትላንት ምሽት እንደዘገበው የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዎ ሀገሪቱ ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ድጋፍ በከፊል እንድታቆም ፍቃዳቸውን ሰጥተዋል ብሏል። አስቸኳይ የሰብአዊ ድጋፎች እንዲሁም የጤና እርዳታዎች አይቋረጡም ብሎ የኮንግረስ ምንጮቹን ጠቅሶ ፅፏል። – Exclusive – U.S. Halts Some Foreign Assistance Funding to Ethiopia Over Dam Dispute with Egypt, Sudan – Some U.S. officials fear the move will harm Washington’s relationship with Addis Ababa. ከዚህ በፊት አሜሪካ ለኢትዮጵያ የማደርገውን ድጋፍ አጤነዋል በማለት ማሳወቋ ይታወሳል።ውሳኔው አሜሪካ ከህዳሴ ግድብ ሙሌት ስምምነት ጋር በተያያዘ ነው የተባለ ሲሆን ለኢትዮጵያ ከምትሰጠው እርዳታ 130 ሚልየን ዶላር ለማስቀረት አቅዳለች ። – አሜሪካ በህዳሴ ግድብ ሙሌት አዳራዳሪ የነበረችውሲሆን ከአደራዳሪነት በኢትዮጵያ ጥያቄ እንድትወጣ የተደረገችው አሜሪካ ለኢትዮጵያ ከምትሰጠው አመታዊ እርዳታ ውስጥ እሰከ 130 ሚልየን ዶላር ልትቀንስ የምትችልበት እቅድን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ማይክ ፖምፕዮ ማፅደቃቸውን ፎሬይን ፖሊሲ መፅሄት ፅፏል። U.S. Halts Some Foreign Assistance Funding to #Ethiopia Over Dam Dispute with #Egypt, #Sudan. Some #US. officials fear the move will harm Washington’s relationship with Addis Ababa. #GERD Via @ForeignPolicy https://t.co/CJxBkVHC4t — Minilik Salsawi 💚 💛 ❤ (@miniliksalsawi) August 28, 2020 ይህም የትራምፕ አስተዳደር ኢትዮጵያ ፣ ግብፅ እና ሱዳንን በህዳሴ ግድብ ዙርያ ለማወያየት የጀመረው እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ ተቃውሞ ገጥሞት መቆሙን
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሻሸመኔ የኃይሌ ሪዞርት ሲቃጠል የመከላከያ እና የፖሊስ ኃይል አባላት እየሳቁ እሳት ይሞቁ ነበር

‹‹በመንግሥት የፀጥታ አካላት ፊት ሕይወትም ንብረትም ጠፍቷል››የሻሽመኔ ከተማ ነዋሪዎች ‹‹የኃይሌ ሪዞርት ሲቃጠል የመከላከያ እና የፖሊስ ኃይል አባላት እየሳቁ እሳት ይሞቁ ነበር››የሻሸመኔ ከተማ አስተዳደርናፀጥታ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል ተከስቶ በነበረው የፀጥታ መደፍረስ ምክንያት ተጠቂ የነበሩ ዜጎች የሚገኙበትን ወቅታዊ ሁኔታ የሚገመግም በብሔራዊ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት የሚመራ ቡድን በማቋቋም ችግሮች ወደ ተከሰቱባቸው ከተሞች በማቅናት የችግሩን ጥልቀት እና ተጎጂዎች ያሉበትን ወቀታዊ ሁኔታ ተመለከተ፡፡ ቡድኑ በሻሸመኔ ከተማ የተለያዩ ቦታዎች የደረሱትን ውድመቶች ተዘዋውሮ ተመልክቷል፡፡ስለ ሁኔታው ያነጋገራቸው ጉዳት የደረሰባቸው የከተማው ነዋሪዎች የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ሞት ከተሰማበት ከሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ.ም ከምሽቱ 4፡00 ሰአት ጀምሮ በከተማዋ ግርግር የሚመስሉ እንቅስቃሴዎች ይስተዋሉ እንደነበር ገልፀዋል፡፡የተጠና በሚመስል ሁኔታ በእለተ ሰኞ ለሊት (ሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ.ም)ለማክሰኞ (ሰኔ 23 ቀን 2012 ዓ.ም)አጥቢያ ከለሊቱ8፡00 ሰዓት ጀምሮ ጩኸት ከየቦታው መሰማት መጀመሩን እና በተመረጡ ቤቶች ላይ ቤንዚን እየተርከፈከፈ ቤቶች ይቃጠሉ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ ይህ ሲሆንም በቦታው የደረሰው የመከላከያ ሠራዊትም ሆነ የከተማዋ ፖሊስ ሠራዊት ቆሞ ከማየት በዘለል ትእዛዝ አልተሰጠንም በሚል ምክንያት ሁኔታውን ለመቆጣጥር ባለመፈለጋቸው በሰው ሕይወት እና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጥፋት እንዲደርስ ሆኗል ብለዋል፡ ፡ ‹‹እኛም ሕይወታችንን ለማትረፍ ምንም ሳንይዝ ወደ አብያተ ክርስቲያናት በመሮጥ ሸሽተን አምልጠናል›› በማለት ክስተቱን መለስ ብለው አስታውሰዋል፡፡ ስለክስተቱ እንዲያስረዱ የሻሸመኔ ከተማ አስተዳደርና ጸጥታ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ስንታየሁ ጥላሁን ተጠይቀው በሰጡት አስተያየት
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃል የተገባው የሁለትዮሽ የጋራ መድረክ አልተፈጠረም

«የኢዜማን መዋቅር ለማዳካም ሆን ተብሎ ሥራ እየተሠራ ይገኛል» – ዋስይሁን ተስፋዬ – የኢዜማ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ጠቅላይ ሚንሰቴር ዐቢይ አሕመድ ከተፎካካሪ ፓርተዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ የሁለትዮሽ የጋራ ግንኙነት ይጀመር ብለው ቃል በገቡት መሠረት የጋራ መድረኩ ከአዲስ አበባ ውጭ በክልሎች ላይ ሊፈጠር ባለመቻሉ መድረኩ እንዲፈጠር የሚመለከታቸው አካላት ላይ ግፊት እያደረገ መሆኑን ገለጸ፡፡ በተፎካካሪ ፓርቲ አባላት መታሰር እና መዋከብ እንዲሁም በፓርቲዎች ላይ የሚፈጠረው አግባብ ያልሆነ ጫና ለመፍታት ታልሞ በጠቅላይ ሚንስትሩ የተዘጋጀው የሁለትዮሽ ጋራ መድረክ በአዲስ አበባበ ፓርቲዎች መካከል ቢፈጠርም በሌሎች ክልሎች ላይ ለሚገኙ አመራሮች ኢዜማ ተደጋጋሚ ጥያቄ አቅርቦ በሥራ መብዛትና በስብሰባ እያመካኙ ሊገኙ ባለመቻላቸው ለአመራሮቹ ጥያቄዎቻቸውን ማቅረብ አለመቻላቸውን የኢዜማ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ዋስይሁን ተስፋዬ ገልጸዋል፡፡ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊው በኮንሶ የተፈጠረውን እንደምሳሌ በማንሳት «በኮንሶ አሌ ስድስት የምርጫ ወረዳ ሲኖር በወረዳው ላይ በምርጫ ተወዳድረን እንዳናሽንፍ ጫና እየተደረገብን ነው፡፡ የኢዜማን መዋቅር ለማዳካም ሆን ተብሎ ሥራ እየተሠራ ይገኛል»በማለት በፓርቲያቸው በኩል አሁንም ጉዳዩ እንዲፈታ የጋራ መድረኩን የሚወከሉ ሰዎችን በመምረጥና በማዘጋጀት ወደ ሥራ ለመግባት ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውን አሳውቀዋል፡፡ ከዚህ በፊት የተፈጠረው ችግር በዘላቂነት ሳይፈታ አካባቢው ወደ ብጥብጥ ቢሄድ ተጎጂ የሚሆነው ሁሉም መሆኑን የገለጹት ዋስይሁን«የሰላም መደፍረስ አንዱን ተጠቃሚ፤ አንዱን አክሳሪ የሚያደርግ አለመሆኑን ማወቅ ሲገባቸው የአካባቢው አመራሮች ግን እነሱ አትርፈው እኛ የምንከስር እየመሰላቸው ይገኛል» ብለዋል፡፡በዚህ ተግባር ላይ የሚሳተፉ አካላት ከዚህ ሥራቸው ሊታቀቡ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡በዚህ መንገድ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ያልተጠና ኢላማና ሰብአዊነት የጎደለው አካሄድ ተፅእኖው ከፍተኛ ነው ! – ምንሊክ ሳልሳዊ

ምንሊክ ሳልሳዊ – በኦሮሚያ ክልል የቀጠለው የሰው ሕይወት የመጥፋትና የሽብር ተግባር እጅግ አሳሳቢ በመሆኑ መንግስት አስቸኳይ መፍትሔ ሊያበጅለት ይገባል። በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች በጸጥታ አካላት በተሰነዘረ ጥቃት ሰላማዊ ዜጎች፣ የሃይማኖት ሰዎች፣ አዛውንትና ሕጻናት መሞታቸው እና መቁሰላቸው ተሰምቷል። ሕግ ለማስከበር መንግስት በሚወስደው እርምጃ የሰላማዊ ዜጎችን ደሕንነት የመጠበቅ ግዴታ አለበት። በክልሉ የሚነሱ ተቃውሞዎች ዜጎች በነጻነት ጥያቄዎቻቸውን እንዲያቀርቡ መከልከል ከሕግ አንጻር ተገቢ አይደለም። ዜጎች ጥያቄዎቻቸውን ሲያቀርቡም መንግስት የሚወስደው የኃይል እርምጃም ሊጤን ይገባዋል። የሞት ጉዳቶቹ የደረሱት የኦሮሞ ተቃዋሚ ፓርቲ ፖለቲከኞች እንዲለቀቁ በተጠሩ የተቃውሞ ሰልፎች እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል፡፡ መንግስት በመዋቅሮቹ ውስጥ ያሉትን የግጭት ነጋዴዎችና ግጭቱን የሚመሩ እኩይ አካላትን መንጥሮ በማውጣት ችግሮችን መግታት ይጠበቅበታል። መንግስት የኃይል እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ ችግሮች ይከሰታሉ በሚባልባቸው የክልሉ አከባቢዎች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማወጅ በኮማንድ ፖስት በመቆጣጠር ችግሮችን ከስራቸው ለማድረቅ መፍትሔ ሊሆን ይገባል። በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞ የሚያሰሙ ሰዎች የጥቃት ሰለባ እንዳይሆኑ መንግስት ተገቢውን ጥንቃቄ ሁሉ ማድረግ ይኖርበታል። መንግስት አስቸኳይ በሆነ ሁኔታ የደረሱትን ጥፋቶችና የኃይል እርምጃዎች ያስከተሉትን ግድያዎች በተመለከተ በገለልተኛ አካል በማጣራት የዜጎች የመኖር ሕልውና በሕግ የበላይነት እንዲከበር አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ አለበት። በኡስታዝ አቡበከር አሕመድ አባባል ጽሁፌን ስዘጋ እንዲህ ብለዋል ፦ ” …… በየወቅቱ መፍትሄን ሰላማዊ ባልሆነ መልኩ የማምጣት ሙከራዎች በሁሉም በኩል ይታያል። በተለይም ለችግሮች የሚሰጡ መፍትሄዎች ሌላ ችግር እየፈጠሩ ተደጋጋሚ አዙሪቶች ውስጥ ስንገኝ ይታያል። የዚህ አንዱ መነሻ ለሰላማዊ ጥያቄ ንፁሃንን ተጎጂ ማድረግ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የዳግማዊ አጼ ምኒልክ 176ኛ እና የእቴጌ ጣይቱ 180ኛ የትዉልድ ቀን

የዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ የትዉልድ ቀን ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ከአባታችው ከሸዋው ንጉሥ ኃይለ መለኮት ሣህለ ሥላሴና ከእናታቸው ወይዘሮ እጅጋየሁ ለማ አድያም ቅዳሜ ነሐሴ ፲፪ ቀን ፲፰፻፴፮ ዓ.ም. ደብረ ብርሃን አካባቢ አንጎለላ ከሚባል ሥፍራ ተወልደው፤ በአንጎለላ መቅደላ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ክርስትና ተነሱ። አያታቸው ንጉሥ ሣህለ ሥላሴ የልጁን መወለድ ሲሰሙ “ምን ይልህ ሸዋ” በሉት ብለው ስም አወጡ። እሳቸው “…ምኒልክ በሚል ስም የሚነግሥ ንጉሥ ኢትዮጵያን ታላቅ ያደርጋታል” የሚል ትንቢት ስለነበር ‘ምኒልክ’ የኔ ስም ነው ብለው ነበር። ሆኖም፣ በህልማቸው ከልጁ ጋር አብረው ቆመው ከሳቸው ጥላ የልጁ ጥላ በልጦ፤ በእግር የረገጡትን መሬት ሲያለካኩ እሳቸው ከረገጡት ልጁ የረገጠው ረዝሞ አዩ። ከዚህ በኋላ “ምኒልክ የኔ ስም አይደለም። የሱ ነው። ስሙን ምኒልክ በሉት” ብለው አዘዙ ይላል ጳውሎስ ኞኞ “አጤ ምኒልክ” በተባለው መጽሐፉ (ገጽ ፲፪) ምኒልክ እስከ ሰባት ዓመታቸው ድረስ መንዝ ውስጥ ጠምቄ በሚባል አምባ ከእናታቸው ዘንድ አደጉ።አያታቸው ንጉሥ ሣህለ ሥላሴ ሲሞቱ የሸዋውን አልጋ የምኒልክ አባት ንጉሥ ኃይለ መለኮት ሣህለ ሥላሴ ወረሱ። ዓፄ ተዎድሮስ በጥቅምት ወር ፲፰፻፵፰ ዓ/ም ትግራይንና ወሎን አስገብረው፣ አቤቶ ምኒልክ ገና የአሥራ ሁለት ዓመት ልጅ ሳሉ፤ የድፍን አማራንና የወሎን ጦር አስከትተው የሸዋውን ንጉሥ ኃይለ መለኮትን ለማስገበር ሸዋ ገቡ። ሁለቱ መሪዎች ጦርነት ለመግጠም ተዘጋችተው ሲጠባበቁ ንጉሥ ኃይለ መለኮት ባደረባቸው ሕመም ጥቅምት ፴ ቀን አረፉ። በዚህ ጊዜ የሸዋ መኳንንት ሕጻኑን ምኒልክን ከጠላት እጅ እንዳይወድቅባቸው ይዘው ሸሹ፤ ዳሩ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የወላይታው ግርግር ብልጽግና ፓርቲ እና አመራሮቹ የፈጠሩት ችግር ነው ! ሰርጎ ገቦችም አደመቁት ! – ምንሊክ ሳልሳዊ

የወላይታው ግርግር ብልጽግና ፓርቲ እና አመራሮቹ የፈጠሩት ችግር ነው፡  ሰርጎ ገቦችም አደመቁት – ምንሊክ ሳልሳዊ የወላይታው ግርግር በሌሎች ክልል እንሁን ዞኖችም ለመቀጠሉ ዋስትና የለም። ክልል ሆኖ የስልጣን ጥማትን ማስተንፈስ የፈለጉት የወላይታ ባለስልጣናት መታሰራቸውን ሰማን። የወላይታ ባለስልጣናት የክልል ጥያቄያቸው ምላሽ እንዲያገኝ ራሳቸውን ከደቡብ ክልል ምክር ቤት አግልለው እንደነበር ይታወሳል። ባለስልጣናቱ የብልጽግና ፓርቲ የደቡብ ቅርንጫፍ አመራሮች ናቸው። ባለስልጣናቱ ሕዝቡን ወደ ግርግር ለመውሰድ የልብ ልብ የተሰማቸው መንግስት በደቡብ ክልል ላይ የሚከተለው አዲስ የ አደረጃጀት ፖሊስ መሆኑ የማይካድ ሐቅ ነው። ብልጽግና መራሹና ገዢው ፓርቲ ኦዴፓ የደቡብ ክልልን ወደ ትናንሽ ክልሎች ለመከፋፈል የሚሔድበት አካሔድ የግርግሩ መነሻና ለወላይታ ባለስልጣናትም የትእቢት መሰረት መሆኑ እሙን ነው። የደቡብ ክልልን ለማፍረስ የሚኬድበት መንገድ የልብ ልብ የሰጣቸው የወላይታ ብልጽግና አመራሮች የሲዳማ ክልል መሆን የፖለቲካ ቅናት ስላስከተለባቸው የራሳቸውን ክልል መመኘታቸውና ከፌዴራል መንግስቱና ከደቡብ ክልል ምክር ቤት ማፈንገጣቸው አይፈረድባቸውም። የሐገራችንን ሰላምና ደሕንነት የማይፈልጉ ኃይሎች የገዢው ፓርቲ በደቡብ ክልል ላይ የሚከተለውን አዲስ ፖሊስ ተገን አድርገው ሰርገው በመግባት ግርግር እንደሚፈጥሩም ቀድሞ ማወቅና መጠንቀቅ ያስፈልግ ነበር። የወላይታው ግርግር በሌሎች ክልል እንሁን ዞኖችም መቀጠሉ የማይቀር ሐቅ ነው። የዞን አስተዳዳሪዎች የስልጣን ጥማቸውን ለማርካት ካልሆነ በስተቀር የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥያቄ ክልል የመሆን ሳይሆን በመላው ሐገሪቱ በሰላም ተዘዋውሮ የመስራት ንብረት አፍርቶ የመኖር የሕልውና ጥያቄ ነው። ጉዳዩን የለኮሰውም ሆነ የደቡብ ክልል ለማፈራረስ እቅድ ይዞ የሚንቀሳቀሰው ገዢው ፓርቲ የወላይታን ባለስልጣናት አፍሶ ማሰሩና በዞኑ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

እነለማ ቀድሞውኑ ራሳቸውን ያገዱ ባለስልጣናት ናቸው

እነለማ ቀድሞውኑ ራሳቸውን ያገዱ ባለስልጣናት ናቸው ! – ምንሊክ ሳልሳዊ – ገዥው ፓርቲ አገድኳቸው ያላቸው ባለስልጣናት ቢያንስ ባለፉት አንድ አመት ውስጥ በፓርቲው ውስጥ የነበራቸውን እንቅስቃሴዎችና ሂደቶች መለስ ብለን ካሰብን የፓርቲው አባል አይመስሉኝም። ምንም ሊዋጥልኝ አልቻለም። – ለማ መገርሳ ብልጽግናን አንቅሮ ተፍቶ የራሱ ፓርቲ አድርጎ ካለመቁጠሩም በላይ ባለፉት ስብሰባዎች ሁሉ ካለመኖሩም በተጨማሪ በሚኒስትሮች ስብሰባ እንኳን አንዳንዴ ብቅ ሲል አኩሩፎ የሚታይ ሰው ነው። ይህ ሰው ታገደ አልታገደ ከጅምሩ ራሱን አግዷል። – ዶክተር ሚልኬሳ ካሁን ቀደም አምርሮ በመንግስት በደል እየደረሰብኝ ነው ሲል ሰምተነዋል።ቤቴን መኪናዬን ተነጠኩ፣ ደሕንነትና ፖሊስ አሳደዱኝ አስፈራሩኝ፣ የመኖር ሕልውናዬ ተደፍሯል ወዘተ እያለ ሲያማርር የነበረ ሰው ሲሆን መታገዱን ሲሰማ የማላምንበትን ስራ ላይ ስለነበር አይደንቀኝም ብሏል ። አላሰራ አሉኝ በሚል ምክንያት ራሱን አግዱ ቤቱ የሚውልበት ጊዜ ስለሚበልጥ መታገዱ አልደነቀውም። – ወ/ሮ ጠይባ ሀሰን ሌላኛው የታገደችው ባለስልጣን ከተሾመችበት ጊዜ ጀምሮ የቤሮዋን ቁልፍ ያልተረከበችና በተለያዩ ሕመሞችና በወሊድ ቤቱ የተቀመጠች ፖለቲካውንም የረሳችው ነች። የካድሬነቷን ባሕሪ ረስታው ወደ ቤት እመቤትነት ከተለወጠች ስለቆየች ታገደች መባሉ ውሐ አያነስም። – ኦዴፓ አመራሮቼ ናቸው የሚላቸውን በጊዜያዊነት አግጃለሁ ኃላፊነታቸውን አልተወጡም ሲል እየተካሄደ ያለው ፖለቲካ ተከታታይ ጥያቄዎች እንዲነሱበት ያደርጋል። እነዚህ ቀድመውኑ ራሳቸውን ያገዱ የፓርቲው ሰዎች ዛሬ ላይ ታግደዋል ቢባል ከመሳለቅ ውጪ ምንም አይፈጠርም። #MinilikSalsawi
Posted in Amharic News, Ethiopian News

እቅዳቸውን ለማክሸፍ የሚሞክረውን ሁሉ ጦርነት እንደሚገጥሙት ነግረውናል- ጉዳዩ ፖለቲካ ነው፤ የበላይነትን የመፍጠር የተረኝነት አባዜ ነው

(ምንሊክ ሳልሳዊ) – መንግስትን ለሰላምና ለፍቅር እንዲበረታታ መደገፍ ማለት መንግስት በሕዝብ ላይ ተንኮል ሲያሴር እያዩ ዝም ማለት አይደለም። መተቸት ካለበት መታረም ካለበት ሽመልስ ብቻ ሳይሆን ፓርቲው ከነመሪው ነው። እቅዳቸውን ለማክሸፍ የሚሞክረውን ሁሉ ጦርነት እንደሚገጥሙት ነግረውናል። – የሽመልስ አብዲሳን ጉዳይ ሿሚው አካል አያውቅም ማለት ራስን ማታለል ነው። አብይ ይህን ጉድ አያውቅም ብሎ ለመታለል መሞከር ሞኝነት ነው። ጉዳዩ ፖለቲካ ነው፤ የበላይነትን የመፍጠር የተረኝነት አባዜ ነው። አብይ የኦሕዴድ ወይም የኦሮሞ ብልጽግና ፓርቲ ሊቀመንበር ነው። አብይ የማያውቀው ሽመልስ የሚናገረው የተረኝነት ለውጥ ሂደት በፍጹም የለም። – ታከለም ሰራው ፤ሽመልስም ሰራው ፤ሌላው የኦሕዴድ አመራር ሰራው፤ አብይ በደንብ ያውቀዋል። ሽመልስን ከስልጣን ቢያባርሩትም ያሰቡትንና የነደፉትን ከመስራት ወደኃላ እንደማይሉ ኦሕዲዶች ራሳቸው እየነገሩን ነው። ደጋግመን ሰምተነዋል ይህንን እቅዳቸውን ለማክሸፍ የሚሞክረውን ሁሉ ጦርነት እንደሚገጥሙት ነግረውናል። እነ እስክንድር ነጋና የ አስራት ሚዲያ ሰዎችን የዚሁ ጦርነት ሰለባ ናቸው። – ብትወዱም ባትወዱም ቄሮን የፈጠረው ኦህዴድ ነው።ሰልፍ ስናስወጣም ስንበትንም የነበርን እኛ ነን። አምስት ቋንቋ የመረጥነው ለእነሱ አስበን አይደለም፣ ለኦሮምኛ ብለን ነው።አዲስ አበባ ውስጥ በሕገወጥም ሆነ በህጋዊ መንገድ ሰው እናስገባለን። ብለውናል። እንግዲህ ሌላውን ለመደፍጠጥና የራስን ተረኝነት ለማበልጸግ ብቻ ሲባል ቋንቋዎች አመራረጥ ላይ ለሌላው አስቦ እንድልሆነ መናገር የሚያሳፍርና ከአንድ መሪ የማይጠበቅ ነው። አዲስ አበባንም የማትጠቅም ከተማ ለማድረግ እየሰሩ እንደሆነም ነግረውናል። የቄሮንም ወንጀል መሸከም የኦዴፓ ድርሻ ሊሆን ነው። ( https://mereja.com/video2/watch.php?vid=90ae85708 ) ብልጽግና መራሹ ኦሕዴድ እየሔደበት ያለው መንገድ ለሕዝብም
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሕወሓት ሰዎች ስልጣናቸውን ስላጡ ብቻ በሶስት ወር ውስጥ ሐገር ለማተራመስ አቅደዋል። (ምንሊክ ሳልሳዊ)

የሕወሓት ሰዎች የስልጣን ጥማት ገደብ የለውም። (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ……. ስልጣናቸውን ስላጡ ብቻ ለሕዝብና ለሐገር ጥፋትና ውድመት ይመኛሉ። – ……. ስልጣናቸውን ስላጡ ብቻ ኢትዮጵያ ሶሪያ እንድትሆን ይመኛሉ። – …….. ስልጣናቸውን ስላጡ ብቻ ኦሮሚያም እንድትወድም እኩይ ቅስቀሳቸውን ያደርጋሉ። – …….. ስልጣናቸውን ስላጡ ብቻ ኢትዮጵያ እንድትወድም ይሰራሉ። – ………. ስልጣናቸውን ስላጡ ብቻ በሶስት ወር ውስጥ ሐገር ለማተራመስ አቅደዋል። – ……. ስልጣናቸውን ስላጡ ብቻ ከፍተኛ ባለስልጣናትንና የጦር ጄኔራሎችን ለመግደል ይመኛሉ። – …….. ስልጣናቸውን ስላጡ ብቻ የመንግስትን መዋቅር አፈራርሰው ሐገርን ለመበታተን ያሴራሉ። – ….. የሕወሓት ሰዎች እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል እንዳለቸው እንሰሳ እኛ ካሌለን ኢትዮጵያ ትውደም እያሉ ያሟርታሉ። አፍርሰን እንገንባ ይሉናል። የነሱ ግንባታ ዝርፊያና ብልት ላይ ሃይላንድ ማንጠልጠል ነው። መንግስትም ሆነ ሕዝቡ እነዚህን ከንቱዎች ዝም ማለት የለብንም። ኢትዮጵያ አትወድምም ለዘላለም ትኖራለች። #MinilikSalsawi
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሐይማኖት ተቋማትና የመንግስት ፖሊሲዎች ለትውልዱ መላሸቅ ተጠያቂዎች ናቸው – ኃላፊነትም ሊወስዱ ይገባል።

የሐይማኖት ተቋማትና የመንግስት ፖሊሲዎች ለትውልዱ መላሸቅ ተጠያቂዎች ናቸው። ኃላፊነትም ሊወስዱ ይገባል። ምንሊክ ሳልሳዊ – የሐይማኖት አስተማሪዎችና የመንግስት ፖሊሲዎች ትውልድን በመቅረጽ ረገድ ግዴታ አለባቸው። ግዴታቸውን የማያውቁ የሐይማኖት ተቋማትና የፖሊሲ አውጪዎችና አስፈፃሚዎች ወንጀለኞች ናቸው። ኢሕአዴግ ስሙን ከመቀየር ጀምሮ የተወሰኑ የለውጥ ሂደቶችን በተግባር ከማሳየቱ ውጪ መንግስታዊ መዋቅሮችም ይሁኑ ፖሊሲዎች አለወጠም። ከመለስ ዜናዊ ሲወርድ ሲዋረድ በመጣው የዘር ፖለቲካ ፖሊሲና የዳሸቀ የትምሕርት ፖሊሲ ወጣቱን የሞት ዲቃላ እንዲሆን አድርጎታል።ለዚህም ገዢው ፓርቲ ለወጣቱ በጥፋት ኃይሎች መታለል ኋላፊነቱን ሊወስድ ይገባል። መንግስት የደኸዩ ፖሊሲዎቹና ብቃት የሌላቸው የፖሊሲ አስፈጻሚዎችን ታቅፎ ተቀምጦ ስር ነቀል የመዋቅር ማሻሻያ አለማድረጉ ተጨምሮበት ተደራራቢ አደጋዎችን እያስተናገደ ነው። የሃይማኖት ተቋማት ወጣቱን ቅን አሳቢ፤ ለወገንና ለሐገር ተቆርቋሪ፣ በፈጣሪው ተስፋ የሚያደርግ፣ መረጋጋትን የተላበሰ አስተዋይ ክብርንና ፍቅርን የመሳሰሉን እንዲያውቅ እንዲሆንና እንዲመራበት አድርገው በሐይማኖታዊ ቀኖናቸው ባለመቅረፃቸው ለሚደርሱት ጥፋቶች ኃላፊነቱን ሊወስዱ ይገባል።በርካታ ቤተክርስቲያናት፣ በርካታ መስጂዶች፣ በርካታ የፕሮቴስታት አደራሾች በተገነቡበት፣ በርካታ ቀሳውስት፣ በርካታ ኡስታዞች፣ በርካታ ፓስተሮችና ነቢይ ነን ባዮች እንዲሆም በየስርቻው የተወሸቁ የሃይማኖት አስተማሪ ነን ባዮች በፈሉባት አገር ላይ ወጣቱ ሞራሉ በፈጣሪ ፍርሐት እንዳይታነጽ ሆኖ በግድያና በንብረት ማውደም ላይ ሲሰማራ ማየት የሃይማኖት ተቋማት የሞራል ልእልና መሞቱን ይመሰክራል። በሐገሪቱ በማይረባ የትምሕርት ፖሊሲ የተደቆሰውን ወጣት ኃይል በተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ እንዲኖር በስራ ማጣት እንዲሰቃይ የሚያደርጉ የመንግስት የዘር ፖለቲካና የትምሕርት ፖሊሲዎች ሊወገዱ ይገባል። የሃይማኖት ተቋማትም ሕዝብን እያጭበረበሩ ገንዘብ ከመሰብሰብና የራስን ዝና ከመገንባት ወጥተው ወጣቱ በአፋጣኝ በግብረገብነት
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ያልተቀደሰው ጋብቻ ፤ የድሐ ልጅ መሞት ለፅንፈኛ ዲያስፖራዎች ፖለቲካ ነው።

ያልተቀደሰው ጋብቻ ፤ የድሐ ልጅ መሞት ለፅንፈኛ ዲያስፖራዎች ፖለቲካ ነው። – ሕወሓትን ወደ ስልጣን ለመመለስ በውጪ የሚኖሩ የሕወሓት አባላት ደፋ ቀና እያሉ መሆናቸውን ሰሞኑን ከሽንፍላ ዘረኞች ጎን ተሰልፈው አይተናቸዋል። የኦሮሞ ደም በየሜዳው ሲፈስ የኦሮሞ ወጣቶች በየስርቻው ሲታረዱ በእሬቻው ቀን ወደ ገደል ሲወረወሩ የሕወሓት ሰውች አሸንዳዬ ሲጨፍሩ ነበር። – በሕወሓት የስልጣን ዘመን የኦሮሞ ሕዝብ ሲታሰር ሲገደል ሲሰደድ ሲንገላታ እናት በልጇ ሬሳ ላይ ተቀምጭ ስትባል ኢትዮጵያዊያን የዲያስፖራ ኮሚኒቲዎች የሕወሓትን አገዛዝ በመቃወም ሰልፍ ሲወጡ የሕወሓት አባላት የትግራይ ተወላጆች ግን ዝር ብለው አያውቁም። ሕወሓት በኦሮሞ ፖለቲከኞች ክፍተትና በደቡብ የክልል አደረጃጀት ጥያቄዎች ላይ ሰርጎ ገብ በመሆን ሃገርን በማተራመስ ስልጣን ለመያዝ የምታደርገው ሩጫ ስለከሸባት በሰው አገር ሰልፍ መውጣት ጀምራለች።የደሃ ልጅ መሞት ለፅንፈኛ ዲያስፖራዎች ፖለቲካ ነው። – ሕወሐት በስልጣን ዘመኑ ያላረጋገጠውን መብት ዛሬ ላይ ለመብትና ለነፃነት ተከራካሪ ሆኖ መቅረቡና አደባባይ ላይ ሰልፍ መውጣቱ ከሕወሓት አይናውጣ ባሕሪ አንጻር ባያስደንቅም የኦሮሞ ሕዝብ ተከራካሪ የሆነበት ሞራል ግን አስገራሚ ነው። የሕወሓት ዲያስፖራዎች ባንድራቸውን ይዘው አደባባይ የሕዝብ መብት ተቆርቋሪ መሆናቸውን ማየት አስቂኝ ነገር ነው። ዳግም ወያኔን ወደ ስልጣን ለመመለስ የሚደረገው ሩጫ ባልተቀደሰው ጋብቻ ምክንያት የረከሰ መሆኑን የሕወሓት ሰዎች ሊያውቁ ይገባል። #MinilikSalsawi
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ቀለበታዊ የፀሀይ ግርዶሽ “ring of fire” Solar Eclipse ታሪካዊ ክስተት በአዲስ አበባ 90% ገደማ ይታያል።

ግርዶሹ በመላው ኢትዮጵያ ይታያል። በአዲስ አበባ 90% ገደማ ይታያል።   በኢትዮጵያ ቀለበታማ የፀሀይ ግርዶሽ ከምዕራብ ወለጋ አንስቶ ሰሜናዊ ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች እንደሚሸፍን  …. ቀለበታዊ የፀሀይ ግርዶሽ ሰኔ 14 ቀን 2012 ዓ.ም ላሊበላ አካባቢ ይከሰታል።  ሰኔ 14/2012 ዓ.ም በዓለም ሰማይ ላይ ፀሐይ በጨረቃ ትሸፈናለች፤ በከዋክብትም ትከበባለች፤ ሰማይም ልዩ ገጽታ ይኖራታል፡፡ ያልሰሙት ሲደናገጡ የሰሙት ደግሞ ይደነቃሉ፡፡ ቀኑም የተለዬ ይሆናል፡፡ – June 21, 2020 — Annular Solar Eclipse — Addis Ababa Sun close to horizon, so make sure you have free sight to East-northeast. Maximum Eclipse Moon is closest to the center of the Sun. The annular phase of this solar eclipse is not visible in Addis Ababa, but it can be observed there as a partial solar eclipse. The ‘ring of fire’ solar eclipse of 2020 occurs Sunday. Here’s how to watch online. – በሃገራችን ደግሞ ከምዕራብ እስከ ሰሜን ምስራቅ ኢትዮጵያ በተለይም ላሊበላ አካባቢ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ ሰኔ 14 ቀን ከጥዋቱ 12፡45-6፡33 ድረስ እንደሚቆይ ታዉቋል፡፡ በእለቱም ከእረፋዱ 3፡40 አካባቢ ለተወሰኑ ሴኮንዶች ጨለማ እንደሚፈጠር ተጠቁመዋል፡፡ – The time of maximum eclipse, when that “ring of fire” event happens, will be at 2:40 a.m. EDT (0640 GMT) Sunday, June 21, when the moon crosses into the center of the sphere of the sun, from Earth’s
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በ2 አመት አብይን አምባገነን ያሉት ሕወሓቶች እነሱ 27 አመት ምን እንደነበሩ ሊነግሩን ይገባል።

ሕወሓት አሁንም ቅርሻቷን መትፋቷን ቀጥላለች። በፖለቲካ ኩርፊያ ስልጣን አይገኝም፤ ሐገርም አይሸበርም። – ስልጣን ካላገኘን ካልዘረፍን ካልገደልን እንቅልፍ አይወስደንም የሚሉ የሕወሓት ሹመኞች በፈበረኳቸው ሚዲያዎች በኩል የሚያስተላልፏቸው መልእክቶች ምን ያህል ለሕዝብ ያላቸውን ንቀትና ለሃገር ያላቸውን ጥላቻ እያስመሰከሩበት ነው። በ2 አመት አብይን አምባገነን ያሉት ሕወሓቶች እነሱ 27 አመት ምን እንደነበሩ ሊነግሩን ይገባል። – እፍረት፣ይሉኝታና ይቅርታን የማያውቁ ደናቁርቶቹ ሕወሓቶች ከብልጽግና ፓርቲ ጋር የገቡበትን ኩርፊያ ይዘው ጥላቻቸውንና ክፋታቸውን እየተፉ ነው። ሕወሃቶች ብልጽግናን እንደሐገር ወይም ሕዝብ ወስደው ሳይሆን ስልጣኑን ለምን ተነጠኩኝ በሚል እደምታ አደገኛ ተግባራትና እኩይ ፕሮፓጋንዳ ላይ ተሰማርተዋል። – ሕወሓት የፖለቲካ ኩርፊያቸውን ለሐገር ክሕደት አውለውታል። በዓባይ ጉዳይ ላይ ከግብፅ ጎን እስከመቆም ደርሰዋል። ትግራይንም ለመገንጠል ከራሳቸው ጭምር አጋር ፓርቲዎችንም ፈልፍለው ስለ ሐገር መገንጠል የድሮ ቅርሻታቸውን መትፋት ጀምረዋል። ሐገር የማስገንጠልና የመገንጠል የጥላቻ ስራቸውን ከድሮ ጀምረን የምናውቅ ቢሆንም ይህንኑ ጥቅማቸው ሲቀር ማውራት ጀምረዋል። – ይህ ሁሉ ችግራቸው ስለ ትግራይ ሕዝብ አስበው ሳይሆን ስልጣን በማጣታቸው፣ ዝርፊያው ስለቀረባቸው ፣ መግደልና ማሰር ሱስ ስለሆነባቸው፣ ወዘተ ነው። ሕወሓቶች ቆም ብለው ማሰብ ካልጀመሩ በለውጡ ወቅት በአንገታቸው የገባላቸውን ሸምቀቆ እያጠበቁ እንደሚገኙ ሊያውቁት ይገባል። #MinilikSalsawi
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የድንቁ ደያስ ገበና አደባባይ የተዘረገፈው ሰውየው የፖለቲካ ትኩሳት ውስጥ ገብተው በአቋራጭ ያገኙትን ገንዘባቸውን ለተሸነፉ ቡድኖች የማዋላቸው ችግር የፈጠረው ግጭት ነው።

የጉልበተኛው ድንቁ ደያስ ገበና አደባባይ የተዘረገፈው ሰውየው የፖለቲካ ትኩሳት ውስጥ ገብተው በአቋራጭ ያገኙትን ገንዘባቸውን ለተሸነፉ ቡድኖች የማዋላቸው ችግር የፈጠረው ግጭት ነው። ካሁን ቀደም ሐምሳ ሚሊዮን መድበው ሐያ ሺ ፎሌ በማሰልጠን ራሳቸውን መንግስት ለማድረግ አቅደው ነበር። – በአቋራጭ ኢንቨስተር የሆኑት ድንቁ ደያስ ባለሐብት ሳይሆን በባለስልጣናት ድጋፍ የሚዘርፍና በባለስልጣናት አይዞህ ባይነት የከበረ ሰው ነው። ይህ በሕወሓት ዘመን የምናውቀው የብዝበዛ ስልትና ዛሬም ላይ በ አማራ ክልል የምናየው የባለስልጣናት የእከክልህ እከክልኝ የብልጽግናና የሐብት ማመንጫ ዋናው መንገድ ነው። – የሐገርን ሰላም የሚያደፈርሱ የኦሮሞ አክቲቪስቶች እንዲሁም ከአክቲቪስቶቹ ጀርባ ያሉ የስልጣን ጥመኞች በድንቁ ደያስ ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ ይደረግላቸው እንደነበር ባለፉት ጊዜያት የሚወጡ ዘገባዎች አስነብበውናል። – አሜሪካን አገር ተሸሽገው የሚገኙት ድንቁ ደያስ በባለቤትነት የሚያስተዳድሩት ሪፍት ቫሊ ኮሌጅ ተመራቂዎች የኦሮሞ ተወላጆች ብቻ ተለይተው ስራ እንዲቀጠሩ ይደረግ እንደነበርና በቅርቡ እንኳን የ አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የሰራውን ሽፍጥ የምናስታውሰው ጉዳይ ነው። – ድንቁ ደያስ በአቋራጭ ኢንቨስተር የሆኑበት የሶደሬው ሪዞርት ጉድ ሲጋለጥ VIDEO – – መንግስት ለሕዝብ ካሳ የሚከፍለው 1.3 ሚሊዮን ብር ሲሆን አቶ ድንቁ ደያስ ግን ራሱ በተመነው ዋጋ በ200 ሺህ ብር ሕዝብን ሜዳ ላይ ይጥል ነበር – ሁሉም ለሰውየው( ለአቶ ድንቁ) ነው የቆመው። የኦሮሞ ተወላጅ የሌለው ባሕሪ ነው በአቶ ድንቁ ላይ የሚታየው። – ጉዳዩ የሕዝቡ ሮሮ በጨፌ ኦሮሚያ ስብሰባ ላይ ሳይቀር ቀርቦ ምንም ምላሽ አላገኘም። – ያመረትናቸው ምርቶች በስካቫተርና በግሬደር
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

የተጎዱትን ቁስል ማሻር የሚቻለው ከዘጋቢ ፊልሞች ይልቅ ወንጀለኞችን በሕግ ፊት በማቆም ብቻ ነው።

ለሰቆቃ ሰለባዎች ፍትሕ እንጂ ፕሮፓጋንዳ ምንም አይፈይድም ! በሕወሓት መራሹ የኢሕአዴግ አገዛዝ የተፈጸመው ግፍ እጅግ ይሰቀጥጣል።ያማል። ለዚህ መፍትሔው ግን ፕሮፓጋንዳ ሳይሆን ወንጀለኞችን በግድም በውድም ይዞ ሕግ ፊት ማቅረብ ነው። ከፕሮፓጋንዳው ይልቅ ፍትሐዊ እርምጃ ለሌላው ትምሕርት ነው። የተጎዱትን ቁስል ማሻር የሚቻለው ወንጀለኞችን በሕግ ፊት በማቆም ብቻ ነው። ዘጋቢ/ዶክመንተሪ ፊልም የሚባሉ የፖለቲካ ፍጆታዎችን ማራመጃዎች (መንግስታዊ የፖለቲካ ማስተርቤሽን) የሌላውን ፖለቲካ ማራከሻዎች የሕወሓት ሰዎች ጋር የፖለቲካ ብሽሽቅ ለማድረግ በመንግስት መገናኛ ብዙሐን የተለመዱ ትርክቶች የኢሕአዴግ ማደንዘዣ ማራከሻዎች ሲሆኑ ለብልጽግና በውርስ የተላለፉለት ንብረቶች ናቸው፤ ዘጋቢ ፊልሞች። ሕወሓት መራሹ አገዛዝ የዛሬዎችን የለውጥ ኃይሎችን አስከትሎ በሕዝብ ላይ ከፍተኛ ወንጀልና ሰቆቃ ፈጽሟል። ይህ የማይካድ እውነታ ግን በፕሮፓጋንዳ ሳይሆን የሚፈታው በሕግ ፊት ብቻ ነው። የተጎዱትን ቁስል ማሻር የሚቻለው ወንጀለኞችን በሕግ ፊት በማቆም ብቻ ነው። ወንጀለኞቹን በሃገሪቱ ክልል ውስጥ አስቀምጦ ፊት ለፊት ዘራፍ እንዲሉ ፈቅዶ የሕግ የበላይነትን ከማስከበር ይልቅ የሚዲያ ፕሮፓጋንዳ መስራት (መንግስታዊ የፖለቲካ ማስተርቤሽን) የራስን የፖለቲካ ፍላጎት ለማርካት ከሚደረግ ሂደት ተለይቶ አይታይም። ምእራፍ አንድ የኢሕአዴግ አገዛዝ አልፎ ወደ ምእራፍ ሁለት የኢሕአዴግ አገዛዝ ስንሸጋገር የነበሩትን ግሳንግሶች አብሮ ይዞ ከመሻገር ይልቅ የሕግ የበላይነትን ለማስከበር ቁርጠኝነት የለውጡ አካል መሆን ነበረበት። በዋልታ ቲቪ የተሰራው ዘጋቢ ፊልም ለፖለቲካ ፍጆታ መሰራቱ የሚታወቀው የሰቆቃውን ሰለባዎች ከሚዲያ ቃለመጠይቅ ውጪ ዞር ብሎ በድጋሚ የሚያያቸው አለማግኘታቸው ሲሆን ለሰለባዎቹ መድሐኒት የሚሆነው ወንጀለኞቹን ለፍርድ ማቅረብ ሲቻል ብቻ ነው። መንግስት ትግራይ ላይ ከመሸጉ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ግንቦት 20 ዘረኞች የነገሱበት ሐገር የተዋረደችበት የተረገመች ቀን

(ምንሊክ ሳልሳዊ) – የበርካቶች ተስፋ የጨለመበት፣ ከሐገር አልፎ አሕጉርንና አለምን ያስደመሙ የኢትዮጵያ የጦር ሰራዊት የተበተነባት፣ ምሁራን የተገፉበት ፣ ለሐገርና ለወገን የሚተቅሙ የተገደሉባት የተሰደዱባትና ዘረኞችና አናሳ የአፓርታይድ ስርዓት አራማጆች ስልጣን በጠበንጃ የጨበጡባት እለት ናት።ሕወሓት/ኢሕአዴግ ስማቸውን እየቀያየሩ በሕዝብ አናት ላይ የሚዘፍኑባት አገር የተፈጠረችው በዛሬው እለት ነው። – ዛሬ ላይ ቆመን የምናያቸው ሐገርን ለማተራመስ አመጽ የሚሰብኩ፣ ፖለቲካውን በዘር የሚለኩ፣ ቢሮክራሲውን በጎጥና በብሔር የሞሉ፣ ቅድሚያ ለዜጎች ሳይሆን ለዘር የሚሰጡ፣ አደርባዮች፣ የአፓርታይድ አራማጆች፣ የሚናገሩትና የሚያደርጉት የተለያየ የሆኑ ባለስልጣኖች። አስመሳዮችና በወሬ የሚደልሉ ታሪክ አጥፊዎች፣ የፖለቲካ ደላሎችና የ አዞ እንባ አፍሳሾች፣ ያዘኑ መስለው ሕዝብን የካዱ ውርጃዎች የግንቦት ሃያ ፍሬዎች ትሩፋቶች ናቸው። አሁንም አብረውን አሉ። – በግንቦት 20 ኢትዮጵያ አገራችን በጨለማ ጉም ተሸፈነች:: አገርና ህዝብ ጥቁር የሃዘን ልብስ ለበሱ:: ሲጠሏት እና ታሪኳን እና ህዝቧን ሲያዋርዱን ሲያንቋሽሹ በነበሩት ወያኔ ህወሃት ለእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ ተዳረገች:: ዘረኛው እና ጎጠኛው ወያኔ ህወሃት በመለስ ዜናዊ የሚመራው የማፍያ ፋሺስት ግልገል እና ግብረ አበሮቹ ጸረ ሀገር እና ጸረ ህዝብ የሆኑትን ለዘመናት የተከበረው የምኒሊክ ቤተ መንግስት ተቆጣጥረው የግልገል ፋሺስቶች መንደላቀቂያ ሆነ:: እነሱም ስልጣን እንደጨበጡ ኤርትራን አስገንጥለው የቀይ ባህር ንግስት የነበረችው ኢትዮጵያ ወደብ ወይም የባህር በርዋን አጥታ አንገትዋ የተቆረጠ ዝግ አገር አደረጉዋት:: – ወያኔ ህወሃት ከደደቢት ይዞት የመጣውን ህገ ደንቡን የኢትዮጵያ ህገ መንግስት አደረገው:: ኢትዮጵያን በዘር ፣ በቋንቋ እና በሃይማኖት ከፋፍሎ የህዝቡን አንድነት እና ኢትዮጵያዊነት አጠፋዋለሁ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

መገናኛ አካባቢ ዘመናዊ የሆነ የብዙሀን ትራንስፖርት ተርሚናል ግንባታ ሊጀመር ነው።

መገናኛ አካባቢ ዘመናዊ የሆነ የብዙሀን ትራንስፖርት ተርሚናል ግንባታ ሊጀመር ነው መገናኛ አካባቢ ዘመናዊ የሆነ የብዙሀን ትራንስፖርት ተርሚናል (public transport hub)ግንባታ ሊጀመር ነው።በሰአት እስከ 30 ሺህ ተጠቃሚዎችን የሚያስተናግደው ተርሚናሉ ከቀላል ባቡር አገልግሎትና ከፈጣን አውቶብስ አገልግሎት ጋር የተሳሰረ መሆኑ ተገልጿል። ምክትል ከንቲባው አቶ ታከለ ኡማ በትዊተር ገጻቸው የመገናኛውን ግንባታ የሚያመለክት አራት ቪዲዮዎችን ለቀዋል። ቪዲዮዎቹን ከታች ያገኙታል። Another mind blowing project at መገናኛ አከባቢ pic.twitter.com/u8K1E9nJgn — Takele Uma Banti (@TakeleUma) May 13, 2020 የብዙሀን ትራንስፖርት ተርሚናሉ የተሽከርካሪ ማቆሚያና የመንገደኞች መተላለፊያ ድልድይ እንዲሁም ባለ ስምንት ወለል ህንፃም ያካተተ ነው ተብሏል።ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው የተርሚናሉ ግንባታ በተለይ በአካባቢውን የሚታየውን መጨናነቅ በመቀነስ በኩልና የህዝብ ትራንስፖርትን በማዘመን በኩል የጎላ ድርሻ ይኖረዋል። 1/2 …. መገናኛና አከባቢ pic.twitter.com/rb5sCToRBX — Takele Uma Banti (@TakeleUma) May 13, 2020 1/3….. መገናኛና አከባቢ pic.twitter.com/9HJh4ar8Rc — Takele Uma Banti (@TakeleUma) May 13, 2020   1/4 … መገናኛና አከባቢ pic.twitter.com/4fGV4Ngu7L — Takele Uma Banti (@TakeleUma) May 13, 2020
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ስልጣንን ያለ ምርጫና ከህግ ውጪ በሁከትና በብጥብጥ ካልሰጣችሁን ሀገር አተራምሳለሁ የሚለውን ማንኛውንም ሀይል አንታገስም – ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ

ሕወሓትን ከጨረባ ምርጫሽ ታቀቢ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሰሞኑን በየሚዲያው ስለምርጫና ሕገመንግስታዊ ቀውስ የሚናገሩ ፖለቲከኞች አርፈው እንዲቀመጡ አስጠንቅቀዋል። ስልጣንን ያለ ምርጫና ከህግ ውጪ በሁከትና በብጥብጥ ካልሰጣችሁን ሀገር አተራምሳለሁ የሚለውን ማንኛውንም ሀይል አንታገስም ብለዋል፡፡ – ለሕወሓት እንደነገሯት በህገ መንግስቱና በህገ መንግስታዊ ሥርዓቱ ካልሆነ በስተቀር የጨረባ ምርጫ ለማድረግ በሚነሱት ላይ ወሳኝ እርምጃ ለመውሰድ ይገደዳል ብለዋል፡፡ ያለምርጫ ስልጣን የሚከፋፈልበት፣ ስልጣን እንደ ድግስ ትሩፋት የሚታደልበት ሕጋዊ አካሔድ የለም። የኮቪድ ወረርሽኝ እስኪወገድና ቀጣዩ ምርጫ እስከሚካሔድ የብልጽግና ፓርቲ ሐገር የማስተዳደር ኃላፊነት አለበት ብለዋል። – በየሚዲያው ቀርበው የሴራ ትንተና ለሚሰጡና ሕጋዊ ሳይሆን ፖለቲካዊ መፍትሔን እንደ አማራጭ ለሚናገሩ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ፖለቲከኞች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከህጋዊ መንገድ ውጪ ስልጣን ለመያዝ የሚንቀሳቀሱ ናቸው ያሏቸውን አስጠንቅቀዋል።ለዚህም መንግስታቸው ዝግጁ እንደሆነ ተናግረዋል። #MinilikSalsawi ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የሰጡት መግለጫ VIDEO  
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኮቪድ86 እና የኮቪድ97 ያልተቀደሰ ጋብቻ

ተቃዋሚ ነን ባዮች የከሰሩ ፖለቲከኞች ሕገ መንግስታዊ ቀውስ ለመፍጠር መንግስትን ጠልፎ በመጣል ሰላምና ደሕንነትን ለማደፍረስ ኮቪድ 19ን ሰበብ አድርጎ በአቋራጭ ስልጣን ለመያዝ እየተራወጡ ይገኛሉ የኮቪድ86 እና የኮቪድ97 ያልተቀደሰ ጋብቻ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ያልተቀደሰ ጋብቻ ፣ አደርባይነት፣ አስመሳይነት፣ ሴራ፣ የአቋራጭ ሳቦታጅ ወዘተ በተደጋጋሚ ስለሚደራረብ በክሕደት የተሞላና ወረት የደለለው ነው። ተቃዋሚ ነን ባዮች የከሰሩ ፖለቲከኞች ሕገ መንግስታዊ ቀውስ ለመፍጠር መንግስትን ጠልፎ በመጣል ሰላምና ደሕንነትን ለማደፍረስ እየተራወጡ ይገኛሉ ኮቪድ 19ን ሰበብ አድርጎ በአቋራጭ ስልጣን ለመያዝ ያሰፈሰፉት የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች በጋራ ሀገር መምራት ይቅርና ተስማምተው አንዲት ስራ ለመስራት የሚያስችላቸው አሰራር፣ ባህልም ሆነ የስነ ልቦና ዝግጁነት የላቸውም። የጋራ ግንዛቤን መፍጠር አለመቻል፣ ግትርነትና የስልጣን ጥመኝነት ዋነኛ ችግሮቻቸው ናቸው። በሽግ ግር መንግስት ስም የስልጣን ጥምን ብቻ ለማርካት የሚደረግ ሩጫ በፍጹም አይሳካም። ሕዝቡም ተቃዋሚዎች ቢወቅጣቸው እንቦጭ ስለሆኑ ሕዝቡ አይፈልጋቸውም። መንግስት ከመስከረም በኃላ ለሚከሰተው ችግር አራት አማራጮች እስካቀረበ ድረስ በአማራጮቹ ዙሪያ ተወያይቶ መፍትሔ ከማምጣት ይልቅ የኛ ሽግ ግር መንግስት ካልሆነ የሚል ግትርነት ተቀባይነት የለውም። #MinilikSalsawi
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የጸጥታ አስከባሪዎች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሽፋን በዜጎች ላይ ጥቃት እየፈጸሙ መሆኑን የጥቃቱ ሰለባ ተናገረች።

የጸጥታ አስከባሪዎች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሽፋን በዜጎች ላይ ጥቃት እየፈጸሙ መሆኑን የጥቃቱ ሰለባ ተናገረች። የጥቃቱ ሰለባዋ በትዊተር ገጿ እንዳሰፈረችው የፋሲካ እለት ወታደሮች ድብደባ እንደፈጸሙባትና ለሚመለከተው ባለስልጣንም ብታመለክት «የማውቀውቅልሽ ነገር የለም» ብለው ጃሮዬ ላይ ስልኩን ዘጋው። ስትል ጽፋለች ሙሉ ታሪኩን እነሆ – ————————————— የፋሲካ ዕለት ሁሌ እንደምናደርገው ከእቶቼ ጋር walk አድርገን እየተመለስን ልክ ቅ/ማርያም ጋር ስንደርስ በመኪና ያሉ ወታደሮች”እናንተ ተራራቁ” ብለው ተቆጡን። እኛም ድንግጥ ብለን “ውይ እሺ! ግን እኮ ከአንድ ቤት ነው የወጣነው” አልናቸው።   ይህን እዳልናቸው በሚያስደነግጥ ፍጥነት ከመኪናቸው ዘለው ወርደው እየሮጡ ወደ እኛ መጡ የምር ሊመክሩን የመጡ ነበር የመሰለኝ! (በትህትና ማናገርም ያበሳጫል?   “እንዴ፣ ምን ልታደርገ ነው ስለው” አንዱ በጥፊ ሌላው በርጊጫ ሌላው ደሞ በዱላ ተረባረብብኝ! ታናናሽ እህቶቼ ደጋግመው ለመኗቸው! ግን ለእነሱ እንኳን አልራሩም፤ እነሱንም መቱዋቸው!   የሚሆነውን ማመን አልቻልኩም። ያለምንኩዋቸው ልመና አልነበረም! ይሄ ሁሉ ሲሆን በአካባቢው የሚያልፉ ሰዎች ነበሩ። ልክ የቀረፃ ትእይንት እንደሚያይ ሰው ገልመጥ እያደረጉ ከማለፍ ያለፈ አንድም እንኳን እባካችሁ ያለ ሰው አልነበረም።   ተከታታይ ዱላዎች እግሬ ላይ አረፉብኝ ። ጆሮዬ ላይ በሃይል ተመታሁ። እንደዛ ደብድበው ጥለውን ሲሄዱ ከህመሜ ባለፈ በዚህች ሀገር ላይ ጠባቂ አልባ መሆኔ፣ እንደፈለጉ እንዲያደርጉ የሚተዋቸው ህግ እንዳለ አስቤ ይበልጥ አለቀስኩ።   የተመታሁበት ቦታ እስከዛሬ ያመኛል። በእልህ እና በዱላው ምክንያት ሁለት ቀን በስርዓት እንቅልፍ አላገኘሁም። ከዚህ ሁሉ በላይ ግን ሃይ ባይ እንደሌላቸው ማመናቸው ይበልጥ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

መንግስት የአምስት ወራት አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሊያውጅ ይችላል ተባለ

መንግስት የአምስት ወራት አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሊያውጅ ይችላል ተባለ ።   መንግስት የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል የአምስት ወራት አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሊያውጅ ይችላል ተባለ ። ሰሞኑን ከፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች ጋር ሲመክሩ የሰነበቱት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ከፓርቲያቸውን አመራሮች ስብሰባ ተቀምጠዋል። የምክክሩና የስብሰባው ዋናው ዓላማ በቀጣይነት በሕገመንግስቱ ምእራፍ 11 አንቀፅ 93 ንዑስ አንቀጽ 1/ሀ መሰረት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ መሆኑ ተሰምቷል። ሰሞኑን ከፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች ጋር የተገናኙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጥልቀት የተወያዩት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዙሪያ መሆኑ መረጃዎች ጠቁመዋል።የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተከትሎም ሃገራዊ ምርጫውን የማራዘም ሀሳብም አለው ተብሏል፡፡ #MinilikSalsawi
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ዳር ያልደረሰ ምርምር ልክ እንደተጠናቀቀና ወደ ምርት እንደሚገባ አስመስሎ መናገሩ ጥፋት ነው።

እንደ ዜጋ በመንግስት ስም በሕዝብ ላይ የሚረጩ አዘናጊና ሐሰተኛ ፕሮፓጋንዳዎችን ልንቃወምና ልናከሽፍ ይገባል። አትጨባበጥ የተባለውን ሕዝብ ሲያጨባብጥ የዋለው የመንግስት ባለስልጣናት ውዥንብር መፍጠርና ድንቁርና አንድ ሊባል ይገባል። ለኮሮና መድሐኒት ተገኝቷልና የምርምር ሒደቱ ተጠናቆ ወደ ምርት ለመግባት ዝግጅት እየተደረገ ነው መግለጫ ልሰጥ ነው ሲሉ የመንግስት ባለስልጣናት ለሚዲያ መናገራቸው ምን ያህል ለዜጎች ደሕንነት ንዝሕላል እንደሆኑ ያሳያል። የመንግስት ባለስልጣናትን መግለጫ ተከትሎ አትጨባበጥ ሲባል የከረመው ሕዝብ በመተቃቀፍ ሲደሰት ዋለ። የመድኋኒት ምርምርና ግኝት አስቸጋሪና ጊዜ የሚወስድ ወሬው ሁሉ ባዶ ነው።ዳር ያልደረሰ ምርምር ልክ እንደተጠናቀቀና ወደ ምርት እንደሚገባ አስመስሎ መንግስት መናገሩ ጥፋት ነው። የመንግስት ባለስልጣናት ድንቁርና አንድ ሊባል ይገባል። እንደ ዜጋ በመንግስት ስም በሕዝብ ላይ የሚረጩ አዘናጊና ሐሰተኛ ፕሮፓጋንዳዎችን ልንቃወምና ልናከሽፍ ይገባል። የኮሮና ቫይረስን ለመከላከልና ለመዋጋት ራሳችንና ሕብረተሰቡን ከበሽታው ለመታደግ የጠሰተንን የጤና መመሪያዎች በመተግበር ከቤት ባለመውጣት እና ንፅሕናችንን በመጠበቅ ልንተገብረው ይገባል። አንዘናጋ። የባሕል መድሐኒት ተገኘ ብለን አንዘናጋ። ገና ምርምር ላይ ስለሆነ ጊዜ ይወስዳል ሲል መንግስት አሳውቋል። ስለዚህ ሳንዘናጋ ከኮሮና ቫይረስ ራሳችንን እንጠብቅ። ኮሮናን በጋራ እንከላከል። አንዘናጋ ።#MinilikSalsawi
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የአማራ ክልል ባለስልጣናትን ማመን ቀብሮ ነው።

የአማራ ክልል ባለስልጣናትን ማመን ቀብሮ ነው። ከአማራ ክልል የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ሕዝቡን ሆን ብሎ በሁለት መንገድ ለመግደልና ለማሰር በክልሉ ባለስልጣናት ዘመቻ ተጀምሯል። የተረፈውን የክልሉን ሕዝብ ደግሞ ሞራሉን በመግደል ለማዳከም የታቀደ ይመስላል። በአማራ ክልል ባለስልጣናቱ በኮሮኖ ቫይረስ ዙሪያ ራሳቸዉ ያወጡትን ደንብ እየጣሱ መሆናቸዉን ነዋሪዎች ለጀርመን ድምጽ ተናግረዋል።ይህ ማለት ደግሞ እጅግ አደገኛና የሕዝብን ሕይወት በጅምላ ለማጥፋት ሆን ተብሎ የታቀደ ሴራ እንዳለ ከበቂ በላይ ጠቋሚ መረጃ ነው። ሌላኛውና ሁለተኛው ደግሞ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ያወጣው መግለጫ ነው። የጎንደር ከተማ አስተዳደር ሊበሏት ያሰቧትን አሞራ ጅግራ ናት ይሏታል እንደሚባለው ከሕወሓት በወረሰው የሴራና የተንኮል ፖለቲካ ልምድ የተቃኘ የጠለፋ እና የፍጅት መግለጫ አውጥቷል። የከተማው አስተዳደር መረጃ ሕግ ለማስከበር ሳይሆን ንጹሃንን ለመጥለፍ ሆን ተብሎ የሚጀመር ዘመቻ እንዳለ ሌላኛው ጠቋሚ መረጃ ነው። የክልሉን ባለስልጣናት ማመን ቀብሮ ነው። ሕዝቡ የግፋቸው ግፍ ጣራ ከነካ ባለስልጣናት ተንኮልና ሴራ ራሱን ሊጠብቅ ይገባል። #MinilikSalsawi
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመቶዎች የሚቆጠሩ ታማሚዎችንና ሞትን ከማስተናገዳችን በፊትያስፈልገናል።

አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመቶዎች የሚቆጠሩ ታማሚዎችንና ሞትን ከማስተናገዳችን በፊትያስፈልገናል። በየቦታው የምናያቸው የሕዝብ እንቅስቃሴዎች ለኮሮና ቫይረስ መስፋፋት አስጊ መሆናቸው እንደተጠበቀ ሆኖ መንግስት በመጭው ሳምንታት በመቶዎች የሚቆጠሩ የኮሮና ታማሚዎች እንደሚኖሩን እየተናገረ መሆኑ እየተሰማ ባለበት በዚህ እጅግ አደገኛ በሆነ ወረርሽን ለመጠቃት በተዘጋጀንበት አደገኛ ወቅት ላይ በሕገመንግስቱ አንቀፅ 93 ንዑስ አንቀጽ 1/ሀ መሰረት መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሊያውጅ ይገባል። በመቶዎች የሚቆጠሩ ታማሚዎችንና ሞትን ከማስተናገዳችን በፊት የዜጎችን ደሕንነትና ሰላም የመጠበቅ ኃላፊነት የመንግስት ግዴታ ነው። NB : ኮሮናቫይረስ በኢትዮጵያ በ11 ሰዎች ላይ የተገኘ ቢሆንም በቀጣዮቹ ቀናት በመቶዎች ሊያድግ ስለሚችል ሁሉም ሰው በተረጋጋ ሁኔታ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጥሪ አቅርበዋል። ሕገመንግስቱ አንቀፅ 93 ንዑስ አንቀጽ 1/ ሀ …………… የሕዝብን ጤንነት አደጋ ላይ የሚጥል በሽታ ሲከሰት የፌዴራሉ መንግስት የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመደንገግ ስልጣን አለው ። ……… ለክልሎችም በንዑስ አንቀጽ 1/ለ ላይ ይህ ስልጣን ተሰጥቷቸዋል።MinilikSalsawi
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በዳባትና በጎንደር ከፋኖ ጋር መዋጋቱን የአማራ ክልል አመነ !

በዳባትና በጎንደር ከፋኖ ጋር መዋጋቱን የአማራ ክልል አመነ ! አብን በበኩሉ መንግስት ሕግ አስከብራለሁ ብሎ በሚንቀሳቀስበት ማንኛውም ሁኔታ ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ እንዲያደርግ እና የዜጎች ሰብዓዊ መብት በጠበቀ መልኩ እንዲሆን ጠይቋል።አስተያየት ሰጪዎች የአማራ ክልልን ድርጊት አውግዘው የኦሮሚያ ክልል በወለጋ ለተከሰተው ግጭት የእርቅ ኮሚቴ አቋቁሞ ችግሮቹን ለመፍታት ሲለሳለስ አዴፓ ብልጽግና በፋኖ ላይ ጦር መስበቁን ኮንነውታል። በዳባትና በጎንደር ለተከሰተው ግጭት የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የእምነት ክሕደት ቃሉን በመግለጫ ያስነበበ ሲሆን ፋኖን በሁለት በመክፈል አንዱን ሲወነጅል ሌላኛውን የሕዝብ የሰላም ጓድ ሲል አሞካሽቶታል። የአማራ ብልጽግና ፓርቲ መግለጫ በአሁኑ ወቅት እየተከሰተ ያለው ጉዳይ እጅግ አስቸጋሪ እየሆነ ነው፡፡ ፋኖ ቁሜለታለሁ ከሚለው አላማና ስነምግባር ውጭ በሆነ መንገድ በፋኖ ስም ያልተገቡ ስራዎች እየተሰሩ ነው፡፡ ብሎ በትላንቱ እለት ለሞትና ቁስለት የተዳረጉት የራሳችን የጸጥታ አካለት ናቸው፡፡ ጥቃቱ የደረሰውም የፖሊስ አባላቱ የህዝብን ሰላም ለማረጋገጥ ሲንቀሳቀሱ እንጅ፤ በፋኖ ስም እንደሚነግዱት አንዳንድ ግለሰቦች ለዝርፊያ ተሰማርተው አልነበረም፡፡ለህዝብ ሰላም ሲሉ አግባብ ያልሆነ መስዋትነት ከፈሉ፡፡ እጅግ በጣም ያማል ብሏል በመግለጫውብሏል፡፡ ፋኖ ቆሜለታለሁ ከሚለው የአማራን ህዝብ ሰላም የማስጠበቅ ስራ በተቃራኒ የቆሙትን አካለት ማስተካከል ካልተቻለው፤ ይሄን ጉዳይ ህዝብና መንግስት፤እንዲሁም ለሰላም የቆሙት የፋኖ አባላት በጋር የማስተካከል ኃላፊነት አለባቸው ብለን እናምናለን፡፡ ይሄን ማድረግ ካልተቻለ ግን፤ክልላችን የጉልበተኞች መፈንጫ ወደመሆን ያመራል፡፡ መንግስትና ህዝብ ደግሞ ይህ እንዲሆን በጭራሽ የሚፈቅዱ አይሆንም፡፡ አቶ ተፈራ ወንድማገኝ የሰሜን ሸዋ አስተዳዳሪ በበኩላቸውየክልሉን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል በተለያዬ ጊዜ የተለያዬ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከሁለት ሳምንት በፊት ለስብሰባ ኢትዮጵያ የመጣ የአሜሪካ የጦር መኮንን የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ መሆኑ እየታወቀ ስብሰባውን ተሳትፎ መሔዱ ተሰማ

– አምባሳደሩ ለጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አሳውቀዋል ተብሏል። አሜሪካዊው የጦር መኮንን ከከፍተኛ የኢትዮጵያ የጦር አዛዦች ጋር ተገናኝቷል። የኢትዮጵያ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጉዳዩን ደብቆት እንዳልሰማ አልፏል። ኮሮና ቫይረስ ተሸክሞ ሸራተን አዲስ በስብሰባ ላይ የተሳተፈው የአሜሪካ የጦር መኮንን ከ42 የአፍሪካ የጦር አዛዦች ጋር ተገናኝቷል ። እ ኤ አ ከፌብሯሪ 18-21, 2020 በኢትዮጵያ ተካሂዶ በነበረው የአፍሪካ ምድር ጦር ኋይል የጦር መኮንኖች ስብሰባ ላይ ተሳትፎ የነበረ አንድ ስሙ ያልተገለጸ የአሜሪካ የባሕር ኋይል የጦር መኮንን የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ መሆኑ እየታወቀ ስብሰባውን ተሳትፎ መሔዱ ተሰማ :: ስብሰባውን በሚካፈልበት ወቅት የኮሮናቫይረስ ምልክቶች ይታዩበት እንደነበርና በኋላም የቫይረሱ ተጠቂ መሆኑ ታውቋል። The U.S. ambassador to Ethiopia told the government that an American Marine visiting the country in February showed symptoms of the coronavirus while there and later tested positive, after staying at a hotel at the same time as Secretary of State Michael Pompeo, people familiar with the matter said. …. The Marine, whose identity hasn’t been released, stayed at the Sheraton Hotel in Addis Ababa for the African Land Forces summit that took place on Feb. 18-21. He showed symptoms while there, the people said. He later tested positive for the virus and is now getting treatment in the U.S. ይህንን ጉዳይ በወቅቱ አምባሳደሩ ለጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሪፖርት ቢያደርጉም
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የካራ ማራ ድል 42ኛ ዓመት – የካራማራን ድል ስናነሳ ጄኔራል ካሳዬ ጨመዳን አንዘነጋም ።

የሶማሊያው መሪ ዚያድ ባሬ ” ታላቋ ሶማሊያ”ን እመሰርታለሁ በሚል ቅዠት ኢትዮጵያን በመውረሩ ህዝቡ ለሀገሩ ዳር ድንበር ዘብ እንዲቆም ጓድ ሊቀመንበር መንግሥቱ ኃ/ማርያም ሚያዝያ 4 ቀን 1969 ዓ.ም በቴሌቭዥን መስኮት ቀርበው ጥሪ አስተላለፉ። “… ታፍራና ተከብራ የኖረችው ኢትዮጵያ ተደፍራለች። … ለብዙ ሺህ አመታት አስከብሮን የኖረው አኩሪ ታሪካችን በዚህ አብዮታዊ አዲስ ትውልድ ጊዜ መጉደፍ የለበትም። አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያዊት! የኢትዮጵያ ሕዝብ! ለክብርህንና ነፃነትህን ለመድፈር አገርህን ለመቁረስ የተጀመረው ጣልቃ ገብነትና ወረራ ከመለዮ ለባሹ ጋር ተሰልፈህ ለመደምሰስ የምትዘጋጅበት ጊዜ አሁን ነው። ተነስ! ታጠቅ! እናሸንፋለን!” ከዚህ ጥሪ በኋላ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዳር እስከ ዳር ገንፍሎ ተነስቶ በ3 ወር ግዜ ውስጥ ታጠቅ ተብሎ በተሰየመው ማሰልጠኛ ቦታ ሰልጥኖ ከኩባ፣ በሶቪየት ሕብረት እና ምስራቅ ጀርመን አንዲሁም የመን ጋር በጋራ በመሆን ትልቁን የካራ ማራ ድል የተጎናፀፉ። የካራማራን ድል ስናነሳ ብሄራዊ ጀግናችንን ጄኔራል ካሳዬ ጨመዳን አንዘነጋም ። Image may contain: 1 person, textከምሥራቅ ጦር ግምባር ጀምሮ ኤርትራ ከምፅዋ እስከ ከረን፤ ናቅፋ ድረስ በስፋት የሚወራላቸው ብርጋዲየር ጄኔራል ካሳዬ ጨመዳ በካራማራ ጦርነት ባደረጉት ታላቅ ጀብዱ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጀግና ሜዳይ ተሸላሚ ናቸው ። በሰራዊቱ ዘንድ ባላቸው ተቀባይነት በተለይም እርሳቸው የሚመሯቸው የ16ኛ ሰንጥቅ ሜካናይዝድ ብርጌድ አባሎች ጄኔራል ካሳዬ ጨመዳን በአመራራቸው ስኬት ከመውደዳቸው የተነሳ ” ካሣዬ ይሙት ” ብለው እንደሚምሉ የሚነገርላቸው ሰው ናቸው ። እናም በአንድ ወቅት ፡ አብዛኛዎቹ የደርግ ጄኔራሎች ህወሃት ደርግን አላሸነፈም ይላሉና እርሶስ ይህን በተመለከተ ምን ይላሉ በማለት
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከሶማሊያ ጋር በመዋጋት የሐገራችንን ሉዓላዊነት ያስከበሩልን ጀግና አባቶቻችንን ማስታወስ ደርግን መናፈቅ አይደለም።

ከዚያድ ባሬ መራሹ የሶማሊያ ወራሪ ኃይል ጋር በነበረን ተጋድሎ ወሳኝ ድል ላስመዘገብንበት የካራማራ ድል በዓል እንኳን አደረሳችሁ።- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ………………… – ድንበራቸውን በደማቸው ያስከበሩ የኢትዮጵያ ልጆች ታሪክ አይረሳቸውም !!! – ከሶማሊያ ጋር በመዋጋት የሐገራችንን ሉዓላዊነት ያስከበሩልን ጀግና አባቶቻችንን ማስታወስ ደርግን መናፈቅ አይደለም። – የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ለካራማራ ድል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ። ካራማራ – የኦጋዴን ጦርነት የዛሬ 42 ዓመት የካቲት 26/1970 ዓ.ም. ነበር የተጠናቀቀው።ኦጋዴን ሠፍሮ የሽምቅ ውጊያ ያካሂድ የነበረው የምዕራብ ሶማሌ ነፃ አውጭ ግንባር የኢትዮጵያ ጦር ላይ ጥቃት ሠነዘረ። የጦርነቱ መባቻ ተደርጎ የሚቆጠረውም ይህ ጥቃት ነበር። በመቀጠል የዚያድ ባሬ ጦር በሶቪዬት ኅብረት የጦር መሣሪያ ታግዞ ወደ አጋዴን ገሰገሰ። የዚያድ ባሬ መንግሥት ወራራውን አጠናክሮ በጅግጅጋ በኩል ደንበር አልፎ ገብቶ ብዙ ጥፋት አደረሰ። የንፁሃን ዜጎች ሕይወት ተቀጠፈ። አልፎም ወደ ሐረር ገሰገሰ። ይሄኔ ነው የኢትዮጵያ ክተት የታወጀው። ሐረር ላይ 40 ሺህ ገደማ የኢትዮጵያ ጦር ኃይል ጠበቀው። ተጨማሪ 10 ሺህ የኩባ ጦረኞች ከኢትዮጵያ ጎን ነበሩ። የኢትዮጵያ ጦር የዚያድ ባሬን ጦር አሳዶ ከመሬቱ አስወጣ። የመጨረሻው ውጊያ የነበረው ካራማራ ላይ ነበር። ጦርነቱ ካራማራ ተራራ ላይ ሲያበቃ ኦጋዴን ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ ተያዘች። በካራማራ ጦርነት በርካቶች ተሰውተዋል። ክብር በሐገራቸውን ዳር ድንበር ለማስከበር ለተሰዉ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት ይሁን !!! (Minilik Salsawi) …………………………………………………………. የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ለካራማራ ድል በዓል
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አዲሱ የንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት ሹመት እያነጋገረ ነው።

አዲሱ የንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት ሹመት እያነጋገረ ነው። አቶ አቢ ሳኖ የኦሮምያ ኢንተርናሽናል ባንክ ፕሬዝዳንት በቅርቡ አምባሳደር ተደርገው የተሾሙትን ባጫ ጊኒን ተክተው የንግድ ፕሬዝዳንት ሆነው ተሹመዋል። አምባሳደር ሆነው የተሾሙት የቀድሞው ፕሬዚደንት አቶ ባጫ ጊኒ ወደ ንግድ ባንክ ሲመጡ የኦሮምያ ኢንተርናሽናል ባንክ ፕሬዝዳንት እንደነበሩ ይታወሳል። ፖለቲከኞች ተረኝነቱ ቀጥሏል ቢሉም ሿሚ አካሎች አቶ አቢ ሳኖ የተሾሙት ባላቸው የባንኪንግ እውቀት ነው ሲሉ ይከራከራሉ። የንግድ ባንክ ሰራተኞች በበኩላቸው ባንኩን ለመምራት የሚችሉ ልምድና እውቀት ያላቸው ሰራተኞች በውስጣችን እያሉ ከደጅ ማምጣት አግባብ አይደለም ሲሉ ይናገራሉ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ፖለቲከኞች በሐገራችን ላይ ስርዓት አልበኝነትን በማስፈን ሰላም እየነሳችሁን ስለሆነ ከድርጊታቹህ ተቆጠቡ።

ፖለቲከኞች በሐገራችን ላይ ስርዓት አልበኝነትን በማስፈን ሰላም እየነሳችሁን ስለሆነ ከድርጊታቹህ ተቆጠቡ።ዝምታን የመረጡ ሐገር ወዳድና ቅን ዜጎች ዝምታቸውን ሊሰብሩ ይገባል። ወጣቱ በሚማገድበት እሳት ፖለቲከኞች መሞቃቸውን ሊያቆሙ ይገባል። ከሰሜን ጫፍ እስከ ደቡብ፤ ከምስራቅ ጫፍ እስከ ምእራብ አንድ ጊዜ በብሔር ሌላ ጊዜ በሐይማኖት ጦርነትንና ግጭትን በመደገስ ለቦዘኔዎች ገንዘብ በመርጫትና በፈጠራ ፕሮፓጋንዳ በመደለል የደሐውን ልጅ ለሞት ማገዶ በማድረግ ረገድ ለስልጣን ጥማታቸው ሲሉ ግንባር ቀደም ሚናውን እየተጫወቱ የሚገኙት ፖለቲከኞች ናቸው። ፖለቲከኞቹ በሐገራችን የለውጥ ጭላንጭል መጥቷል ተስፋ አለ በተባለበት ወቅት የመንግስትን መዋቅርና ቅጥረኞችን እንዲሁን በየጉሮኖው ያሰለጠኗቸውን ገዳዮችንና በጥባጮችን በማሰማራት የወጣቱን ደም ደመ ከልብ ከማድረግ ባለፈ ባለፉት ሁለት አመታት ፊታቸውን ወደ ልማት መልሰው ለወጣቱ አንድም መልካም ነገር ካለማድረጋቸውም በላይ ይብሱኑ ትውልዱ በትምሕርት እንዳይደረጅ በየከፍተኛ ትምሕርት ተቋማቱ ብጥብጥ በማስነሳት ወጣቱን ከትምሕርት ገበታው በግድያና በሁከት አፈናቅለውታል። ወደ መሬት ሕዝብ መሐል ሲወረድ ሕዝቡ በሰላም ሰርቶ መኖርን እንደሚፈልቅ ምስክር አያሻውም። ሆኖም ፖለቲከኞች ከሌሎች አከባቢዎች የተደራጁ የሁከት ቡድኖችን ሰርጎ በማስገባት የሕዝቡን ሰላም በማደፍረስ በገዛ ሐገሩ ተዘዋውሮ የመስራት ሕልውናውን በማደፍረስ ለመፈናቀልና ለሞት ዳርገውታል።በተለያየ መንገድ የሰበሰቡትን ገንዘብ እየዘረፉና ለግጭት እያዋሉት እርስ በእርሳቸው እየተናከሱ መርዛቸውን ወደ ሕዝብ በመርጨት የደም ፖለቲካ በሽታቸውን በማስፋፋት ሐገርን ለውድቀት የሚዳርጉት ምረጡን የሚሉ ፖለቲከኞች ናቸው። ፖለቲከኞቹ በሐይማኖቶች መሐል ጣልቃ በመግባት የሕዝብን የማምለክ መብት በመጋፋት፣ በመከፋፈል፣ ብጥብጥ በማደራጀት፣ ቤተክርስቲያንና መስጂዶችን በማቃጠል በሕዝብ መሐል መተማመን እንዳይኖር የሐሰት ትርክቶችንና መረጃዎችን በማሰራጫት የሐገርን ሰላምና የሕዝብን
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ለጋራ ጥቅማችን ብሎ ለራሱ ከሚጠቀምብን ያድነን !!!

ለጋራ ጥቅማችን ብሎ ለራሱ ከሚጠቀምብን ያድነን፡፡ ከሃዲዎች የዕጣ-ፈንታቸዉን ያገኛሉ:: የሳንቲሙ ገፅ ምን ዓይነት ነው? ዘውድ? ጎፈር? ወይም በሠያፍ የቆመ? መፈተሽ አለበት፡፡ተነስ ሲሉት የሚነሳ፣ ተኛ ሲሉት የሚተኛ … ዞሮ ዞሮ ወዶ-ገባ ያሉትን መፈፀም ግዴታው ነው፡፡ ወዶ-ገባ ዝርያው ብዙ ነው፡፡ የፖለቲካ ወዶ-ገባ አለ፡፡ ፖለቲካው ምንም ይሁን ምንም ለጥቅሜ እገባበታለሁ ይላል፡፡ የኢኮኖሚ ወዶ-ገባ አለ፡፡ ኢኮኖሚው ምንም ይሁን ምን ሆዴን እሞላበታለሁ ይላል፡፡ የማህበራዊ ወዶ-ገባ አለ፡፡ ከማናቸውም ማህበራዊ ቀውስ እኔ ጥቅሜን ካካበትኩ ያሉኝን አደርጋለሁ ባይ ነው፡፡ ብልህ ሰው የውሾቹን ዓይነት ዕጣ-ፈንታ ያስተውላል፡፡ አበሻ፤ አብዶም ሠግዶም ውሉን አይስትም የሚል አባባል አለው፡፡ ይሄንንም ልብ-ልንበል፤ የህግ-ወዶ-ገባም አለ፡፡ በፍትሕ ሽፋን ጥቅሙን የማያጋብስ፡፡ አገርን የሚያጠፋ ማንኛውም ጥፋት ጥፋት ነው፡፡ ሚሥማርም አቀበልን ድንጋይ ያው ነው፡፡ በወገናዊነት ላንድ ቡድን መጠቀሚያ አመቻቸንም፣ በሙስና ውስጥ ተዘፈቅንም፤ ዞሮ ዞሮ አገርና ህዝብ በድለናል፡፡ እገሌ አድርግ ብሎኝ ነው እንጂ እኔ በራሴ አላደርገውም ነበር ማለት የኋላ ኋላ ከተጠያቂነት አያድንም፡፡ በሥርዓቱም ማሳሰብ በግልና በቡድን ከሠራነውና አንዱን የእናት ልጅ፣ አንዱን የእንጀራ ልጅ አድርገን ካጠፋነው ጥፋት ተጠያቂነት አያድንም፡፡ ሰው ሰውን መበዝበዙ ነው ሀቁ፡፡ ፊት ለፊቱም ግልባጩም ያው ነው እንደ ማለት ነው፡፡ስለዚህ ሥርዓት ሰበብ አይሆንም፡፡ ዕውነቱ ሰው ሰውን መበዝበዙ ነው፡፡ ሊበራል፣ ኒዮ ሊበራል፣ አብዮታዊ፣ ኮሙኒስታዊ፣ ፋሽስታዊ፣ ቦናፓርቲዝማዊ፣ ልማታዊ፣ ሉአላዊ፣ ፀረ-ሽብራዊ፣ ዲሞክራሲያዊ፣ ኢጋዳዊ፣ … ሁሉም የሰውና ሰው ተቃርኖና ፍጭት መልኮች ናቸው፡፡ ዋናው ከህዝብና ከሀገር ጥቅም አኳያ ምን ይመስላሉ ተብሎ መመርመር ያለባቸው ናቸው፡፡ የሰውና
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ከስልጣን እንዲነሱ የፊርማ ማሰባሰብ እየተደረገ ነው።

    ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ከስልጣን እንዲነሱ የፊርማ ማሰባሰብ እየተደረገ ነው። በኮሮናቫይረስ መስፋፋት ተከትሎ በዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ላይ አለም አቀፍ ተቃውሞ እየቀረበ ነው። ቴዎድሮስ አድሃኖም ቦታውን መስራት ለሚችሉ ሰዎች እንዲለቅ ከፍተኛ ግፊት እየተደረገ ሲሆን በዓለም ዙሪያ ፊርማዎች ተሰብስበዋል ወደ 500,000 ያህል ፊርማ ደርሷል። ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም አለም አቀፍ የንግድ ወኪል ወይንስ የጤና አለቃ ናቸው የሚል ጥያቄ ያስነሱት የዓለም ማሕበረሰቦች ከሕዝብ ጤና ደሕንነት በላይ አለም አቀፍ ኢኮኖሚንና ንግድን አስበልጠዋል ሲሉ ይተቻሉ። Call for the resignation of Tedros Adhanom Ghebreyesus, WHO Director General Are you the @WHO or world trade organization ? You put trade and economy above the safety and #health of people! #Coronavirus #China #World #WHO #Trade pic.twitter.com/9ECnwMi3Ui — Minilik Salsawi 💚 💛 ❤ (@miniliksalsawi) February 8, 2020
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከሪፍት ቫሊ ኮሌጅና ከአንድ ብሔር ብቻ መንግስታዊ የስራ ቅጥር ለመፈጸም የሚደረገው ሩጫ እየተተቸ ነው

ለማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ ክትትል ጀማሪ ኦፊሰርች ከአንድ የግል ዩንቨርስቲና ከአንድ ብሄር ብቻ ቅጥር ለመፈጸም መዘጋጀቱ አነጋጋሪ ሆኗል:: የከተማው ገቢወች ቢሮ ለስራ ቅጥር ባወጣው ማስታወቂያ ላይ ለፈተና የተመረጣችሁ ብሎ የለጠፈውን ዝርዝር ተመልከቱ:: ሀሉም በሚባል መልኩ ሪፍት ቫሊ ከተባለ የግል ኮሌጅ የመጡ የአንድ ብሄረሰብ አባላት ናቸው:: ለምን ብሎ የሚጠይቅ የለም ወይ? 1) ሌሎች የግል ዩኒቨርሲቲዎችስ? 2) በጥራታቸው የተመሰከረላቸው በአህጉር ደረጃ ከፊት ተሰላፊ ከሆኑት እንደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ካሉ ተቋሞች የተመረቁት ልጆችስ የት ገቡ? ማስታወቂያውን አልሰሙም ነበር? 3) ተቀጣሪወችስ በብዛት ከአንድ ብሄረሰብ ለምን ሆኑ? 4) ሀገሪቱ አሁን እየተመራችበት ካለው ፖለቲካ አስተሳሰብ አንፃር እነዚህ ከአንድ ብሄረሰብ የወጡ ተቀጣሪ ወጣቶች የአዲስ አበባን ህዝብ በቅንነት እና ከፖለቲካ ነፃ በመሆን እንዴት ሊያገለግሉ ይችላሉ? እንደዚህ አይነት የተግማማ ስራ መጋለጥ መተቸት አለበት:: መቆምም አለበት:: አልሰማሁም ደሞም እኔ ቀጣሪ አይደለሁም ማለቱ የማይቀር ቢሆንም ኦሮሞ ከሚገባው በላይ የመንግስት ቦታ ከተሰጠው ስራየን በ24 ሰዓት ውስጥ እለቃለሁ ሲል ቃል ለገባው ጠቅላይ ሚንስትር በጊዜ ንገሩት:: የአዲስ አበባ የገቢወች ቢሮ ስራ ቅጥር ሁኔታ ( የአዲስ አበባ ገቢዎች ባለስልጣን ይህንን ትችት ካየ በኋላ በፌስቡክ ገጹ የለጠፈውን ዝርዝር አንስቶታል )   No photo description available. No photo description available. No photo description available. No photo description available. No photo description available. No photo description available. No photo description available. No photo description available. No photo description available. No photo description available. No photo description available. No photo description available. No photo description available. No photo description available. No photo description available. No photo description available. No photo description available. No photo description available. See More : Lists 
Posted in Amharic News, Ethiopian News

60 የሰቆቃና የለቅሶ ቀናቶች ! …. 2 ወራት ያልተፈታው እገታ !

60 የሰቆቃና የለቅሶ ቀናቶች ! …. 2 ወራት ያልተፈታው እገታ ! እያወራን ያለነው ስለ ዜጎች ደሕንነትና ስለ ሰብዓዊ መብት እንጂ ስለ ፖለቲካ አይደለም። ተማሪዎቹ የት ናቸው የሁሉም ጥያቄ ነው። የደምቢዶሎ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ከታገቱ ሁለት ወር ሞላቸው። ከወላጆች ለቅሶና ከተማሪዎች ሰቆቃ እንግልት እንዲሁም ከመግለጫና ከተስፋ በስተቀር ምንም የታየ አዲስ መፍትሔ የለም። የመንግስት ግዴለሽነት በሕዝብ ጫና ከላላ በኋላም ከፕሮፓጋንዳ ውጪ ምንም ተግባራዊ ፍንጭ የተጨበጠ ውጤት አልታየም። እያወራን ያለነው ስለ ዜጎች ደሕንነትና ስለ ሰብዓዊ መብት እንጂ ስለ ፖለቲካ አይደለም። የታገቱ ተማሪዎችን የማፈላለጉ ስራ ከቄለም ወለጋ ባለፈ እስከ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ድረስ በመዝለቅ በመፈለግ ላይ መሆኑን ሰራዊቱ ምን አልባት የጠፉትን ልጆች ወደ ድንበር እና ወደ ጎረቤት አገሮች የማሸሽ አዝማማያ ሊኖር ይችላል በሚል ጥርጣሬ አሰሳ እያከናወነ እንደሚገኝ መከላከያ ሰራዊቱን ጠቅሶ አዲስ ማለዳ አስነብቦናል። ይህ የሚያሳየው መንግስት ምንም መረጃ እንዳሌለው ወይንም ሆን ተብሎ የሚድበሰበስ መረጃ በመንግስት መዋቅር ውስጥ እንዳለ አመላካች ነው። ከደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ጠፍተዋል የተባሉትን የተማሪዎች ዝርዝር በመውሰድ ተማሪዎቹ እስከ አሁን ያሉበት ባለመታወቁ እና የተማሪዎች ቤተሰብም መጥፋታቸውን በማመልከቱ ፍለጋው ተጠናክሮ መቀጠሉ ተሰምቷል። ባለፉት ሁለት ወራት መንግስት ምንም አይነት ስራ አለመስራቱን በግልፅ እያየን ነው። ተማሪዎቹ የት ናቸው የሁሉም ጥያቄ ነው። #MinilikSalsawi
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የታከለ ኡማና የእስክንድር ነጋ ትንቅንቅ እና የባልደርሱ ቁማርተኞች በፈረንሳይ ለጋሲዮን አከባቢ

የታከለ ኡማና የእስክንድር ነጋ ትንቅንቅ እና የባልደርሱ ቁማርተኞች በፈረንሳይ ለጋሲዮን አከባቢ – ምንሊክ ሳልሳዊ ታከለ ኡማ እስክንድር ነጋ ተወልዶ ባደገበት ፈረንሳይ አከባቢ በመዝመት ቆሞ የቀረውን የመንገድ ስራ ፕሮጀክት ማስጀመሩ ከተሰማ በኋላ የፖለቲካው ቁማሩ ጦፏል። በእርግጥ ሕዝቡ በመጭው ምርጫ ድምፁን ለማን እንደሚሰጥ ቢያውቀውም ታከለ ኡማ የፈረንሳይ ለጋሲዮንን ድምፅ ለብልጽግና ፓርቲ ለማግኘት የመንገድ ስራ ፕሮጀክቱን ተመላልሶ እያስተገበረው ነው። የመንገድ ስራ ፕሮጀክቱን ማስጀመሩ ቀና የልማት ስራ ቢሆንም ታከለ ፈረንሳይ አከባቢ የዘመተው የእስክንድር ነጋን ተቀባይነት ለማሳጣት ነው የሚሉ በርካቶች ናቸው። በእስክንድር ነጋ ጉያ ስር ሆነው ፖለቲካን መደራደሪያና መጠቀሚያ ያደረጉት ቡድኖች እንዳሉ አከባቢው ላይ የሚኖሩ ሰዎች ይናገራሉ።በባልደርሱ ውስጥ እውነተኛ ታጋዮች እንዳሉ ሁሉ ባልደርሱን ጠልፎ ለመጣል ከታከለ ኡማ ጋር በምስጢር የሚደራደሩ ቁማርተኞችም እንዳሉ የፈረንሳይ ወጣቶች ይናገራሉ። ድርድራቸው ቦታና ብድር ማግኘትን ይጨምራል። ለረዥም አመታት የመንገድ ስራው ፕሮጀክት እንዲቀጥል ጥያቄ ሲያቀርቡ ሰሚ አጥተው እንደነበር የሚናገሩት ነዋሪዎቹ የእስክንድር ነጋ የአከባቢው ተወላጅ ሆኖ ወደ ተቃዋሚነት መግባቱና አዲስ አበባ ፖለቲካ ላይ ተፅእኖ መፍጠሩ እንደጠቀማቸው ያብራራሉ። እስክንድር ነጋ ባልደርሱን መስርቶ ባይንቀሳቀስ ኖር የሚያስታውሰን አልነበረም ሲሉ የፈረንሳይ ለጋሲዮን ነዋሪዎች ይገረማሉ። እንደእኔ እስክንድርም ታከለም ፖለቲካቸውን የማራመድ መብት ቢኖራቸውም ሕዝብን ከለላ አድርጎ የፖለቲካ ቁማር መጫወት ግን አፀያፊ ተግባር ነው። #MinilikSalsawi
Posted in Amharic News, Ethiopian News

መንግስታዊ ህገወጥነት ምን ሊያመጣ እንደሚችል እናጢን !!!

መንግስታዊ ህገወጥነት ምን ሊያመጣ እንደሚችል እናጢን !!! አፉን ያለልክ የሚከፍት የማንም ሰው ዕጣ-ፈንታ የአድማጩ ሰለባ ይሆናል !!! ( ምንሊክ ሳልሳዊ )   የምናስባቸውንም የምንጠረጥራቸውንም ጉዳዮች ሁሉ አስቀድመን በተግባር እናረጋግጥ፡፡ በማናቸውም መልኩ በወሬ አንፈታ! ከመፎከርም ከማውራትም በተግባር ምን እናድርግ? ማለት ተመራጭ ነው!! መረጃ መስጠት እንዳለ ሁሉ አሳሳች መረጃ መስጠትም አለ፤ አስቦ መጓዝ ይሄኔ ነው!በሁሉም ወገን የወሬ ናዳ አለ፡፡ ያ ወሬ እውነትም ይሁን ውሸት ህዝቡን ይፈታዋል፡፡በምንም ተአምር አትታለሉ፤ በማናቸውም መልኩ በወሬ አንፈታ!   የቤት-ሥራችንን ጠንቅቀን በመስራትና ጉዳያችንን በማወቅ ነው ለውጥ ለማምጣት የምንችለው፡፡ከሁሉም በላይ እብሪት አገርንና ህዝብን ይጐዳል፡፡ ከማንም በላይ ነኝ እና አምባገነንነት የእብሪት ልጆች ናቸው፡፡ ንቀት፣ ሰው-ጤፉነት፣ ሁሉን አውቃለሁ ባይነት፣ ቆይ-አሳይሃለሁ – ባይነት፤ ብቆጣም እመታሻለሁ ብትቆጪም እመታሻለሁ ማለት፤ከልክ ያለፈ ውዳሴና ማሞካሸትም ከጥቅሙ ጉዳቱ ነው የሚያመዝነው፡፡ ወረራ ዘረፋ የግልጽ ሽብር የትም አያደርስም ቀን የመጣ እለት ውርደት ራሱ አግጥጦ ይወጣል::ተወዳሹ እስኪታዘበን ድረስ ብናሳቅለው ለማንም የማይበጅ ተግባር እንደፈጸምን አደባባዮች ይመሰክራሉ፡፡   መንግስታዊ ህገወጥነት ምን ሊያመጣ እንደሚችል እናጢን፡፡ “እዛም ቤት እሳት አለ” የሚለውን ተረት ከልቦናችን አንለይ፡፡ ከቶውንም እኔ አውቃለሁን ስንፈክር ሌላውም ያውቃልን አንርሳ፡፡ ባደባንበት ሊደባብን እንደሚችል፣ ደባ ራሱን ስለት ድጉሱን መሆኑን፣ ሥራ ለሰሪው እሾክ ላጣሪው እንደሚሆን አንዘንጋ፡፡አፉን ያለልክ የሚከፍት የማንም ሰው ዕጣ-ፈንታ የአድማጩ ሰለባ ይሆናል:: የሚለውን መዘንጋት የለብንም:: የህዝቦችን አመኔታ ለማግኘት መደማመጥ መከባበር መተባበር ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን መዘንጋት የለብንም:: ( ምንሊክ ሳልሳዊ )
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ፌዴራል ፖሊስ የሰጠውን መረጃ ያፈነው መንግስት ዝምታውን መስበር አለበት።

መረጃውን ይፋ ለማድረግ ከአቅሙ በላይ የሆነበት የፌድራል ፖሊስ ኮሚሽን የታገቱ ተማሪዎችን በተመለከተ ያለውን መረጃ ለጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት አስገብተናል ብሏል። መረጃው የከፋ ነገር ስላለው ነው ለበላይ አካል እንዳስተላለፈ የፌዴራል ፖሊስ የጠቆመው። መረጃው ቀላልና ግልፅ ቢሆን ኖሮ የፌዴራል ፖሊስ እንደተለመደው ለሚዲያዎች ይፋ ያደርገው እንደነበርም ተሰምቷል። ጉዳዩንም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያስተላለፈው በታገቱ ተማሪዎች ላይ የተቃጣ ከባድ አደጋ እንዳለ አመላካች ነው። ጉዳዩ አሳሳቢ ነው። የታገቱት ተማሪዎች ሁለት ወር ሊሞላቸው ነው። መንግስት ተለቀዋል ያላቸው ተማሪዎች ለመለቀቃቸው ምንም ፍንጭ የለም። የፌደራል ፖሊስ ስለታገቱት ተማሪዎች ሙሉ መረጃ ለጠ/ሚ/ፅ/ቤት ሰጥቻለሁ መረጃው በአንድ ማዕከል ይውጣ ስለተባለ ምንም ማለት አልችልም ብሏል።መረጃው የከፋ ነገር አለው ብሏል። የፌደራል ፖሊስ ስለታገቱት ተማሪዎች ሙሉ መረጃ ለጠ/ሚ/ፅ/ቤት ሰጥቻለሁ መረጃው በአንድ ማዕከል ይውጣ ስለተባለ ምንም ማለት አልችልም. መረጃው የከፋ ነገር አለው. #Ethiopia #BringBackOurStudents pic.twitter.com/CajjeBqrHT — Minilik Salsawi 💚 💛 ❤ (@miniliksalsawi) January 24, 2020 Image may contain: 9 people, including ጉዱ ካሳ, people smiling, text አደገኛ መንግስታዊ ሽብርተኝነት!! የታገቱ ተማሪዎችን ወላጆች ማስፈራራት ?? …. የፖለቲካ ገረዶቹ የአማራ ክልል ባለስልጣናት የታገቱ ተማሪዎችን ወላጆች ማስፈራራታቸውን ስንሰማ አፈርን። ተማሪዎቹ መታገታቸው ሳያንስ የንጉሱ ጥላሁን ሐሰተኛ መረጃ ሳያንስ ወላጆችን ማስፈራራት ትልቅ ወንጀል ነው። የአማራ ክልል ባለስልጣናት «ጉዳዩን ለፖለቲካ መጠቀሚያ አድራጋችሁታል» በሚል ማስፈራሪያ እያደረጉብን ነው ሲሉ በደምቢዶሎ የታገቱ ተማሪዎች ወላጆች አምርረው ተናግረዋል። በቅርቡ ያየናቸውን የታገቱ ተማሪዎችና የሞጣውን የመስጂድ ቃጠሎ ጨምሮ በተደጋጋሚ የክልሉ ባለስልጣናት በሕዝብ ላይ ክሕደት ፈጽመዋል። ተማሪዎቹ የሚገኙበትን ሁኔታ ለመጠየቅ እና የክልሉ መንግስት
Posted in Amharic News, Ethiopian News

መጭው እና አጣብቂኙ ከባድ ነው፡፡ ያደሩበት ጭቃ ከጭድ ይሞቃል ::

መጭው እና አጣብቂኙ ከባድ ነው፡፡ ያደሩበት ጭቃ ከጭድ ይሞቃል :: ብሶት ሁሉ የፈጠራ፣ ጩኸት ሁሉ የሁከት፣ ሥጋት ሁሉ የትርምስ፤ማለትን እናቁም:: ለህዝባችን የሚበጀው ማንኛው መንገድ ነው? ማለት በጐ ነገር ነው፡፡ህዝብ በኢኮኖሚ ሲጐሳቆል፣ በፖለቲካ በደል ሲሰማውና በማህበራዊ ህይወቱ ያልተረጋጋ ከሆነ ደግ አደለም፡፡ በጥንቱ ማርክሳዊ አካሄድ ፖለቲካ ማለት የተጠራቀመው የኢኮኖሚ ይዘት ነፀብራቅ/መገለጫ እንደማለት ነው፡፡ በግድ አራምደዋለሁ ካሉ አንገት መቀጨት፣ መሰበር፣ መውደቅ፣ አልጋ ላይ መቅረት ይከተላል ማለት ነው፡፡ ለማደግ አቅጣጫ ያስፈልጋል፡፡ ከመዓቱ ለማምለጥ መፍጠንም ያስፈልጋል፡፡ አቅጣጫ ማወቅ ብቻ ሳይሆን መሮጥና መፍጠን ያስፈልጋል ስንል ግን፣ ከምን አቅም? በምን ነፃነት? በምን ፍትሐዊ እርምጃ? በምን ዓይነት ቢሮክራሲያዊ ተቋም? በምን ዓይነት እርስበርስ መተማመን? በምን ዓይነት የገዢ ተገዢ ግንኙነት? ብሎ መጠየቅ ያባት ነው፡፡ የአስተዳደር ነገር መቼም ዋና ጉዳይ ነው፡፡ ኢኮኖሚያችን በኑሮ ውድነቱ መነጽር ሲታይ ዛሬ አሳሳቢ ነው፡፡ የሁሉም ነገር ዘዴው ተገኝቷል እንዴት እንደምንኖር መላው ከመጥፋቱ በስተቀር ፡፡ለፍቶ ለፍቶ፣ ዳክሮ ዳክሮ ኑሮ ጠብ አልል ያለው ሰው ከምሬት ሊወጣ አይችልም፡፡እምዬ ኢትዮጵያ ሥራሽ ብዙ ፍራንክሽ ትንሽ አለ አሉ አንድ ሠራተኛ! በእርግጥ በሊቀ – ሊቃውንት አስተሳሰብና ስሌት ከአምስት አመት በኋላ ሠንጠረዡ ከፍ ይላል፤ በ2021 ዓ.ም አያሌ ፕሮጄክቶች ስለሚጠናቀቁ የተለየ ዓለም ይታያል ወዘተ ይባላል፡፡ ችግሩ ህዝባችን ሰብል በጥር ይታፈሳል ቢሉት ሆዴን እስከዚያ ለማን ላበድረው አለ፤ የሚባለው ዓይነት ችግር ውስጥ ይገባል፡፡ አጣብቂኙ ከባድ ነው፡፡ ያለፈው ዘመን መሪ የወረቀቱ ገብቶኛል፡፡ የገበያውን፣ የመሬት ያለውን ጉዳይ አስረዱኝ አሉ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የምርጫ ቦርድ አካሔድ ማንን ለመጥቀም ይሆን ?

የምርጫ ቦርድ አካሔድ ማንን ለመጥቀም ይሆን ?   ሕግ ይከበራል ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው። ምርጫ ቦርድ ከቀኑ አይዘልም ያለው የግንቦቱ ምርጫ ለነሐሴ ተላልፏል ተብለን ነበር ። አሁን ደግሞ የነሐሴው ምርጫ ወደ ጥቅምትና ሕዳር 2013 ሊዘል ይችላል። ይህቺ አካሔድ ማንን ለመጥቀም ይሆን ???   ሐገራዊ ጠቅላላ ምርጫ የሚካሔድበት ቀን አልተቆረጠለትም የሚል አለማማጅ ፕሮፓጋንዳ ከምርጫ ቦርድ በኩል ተለቃለች።ሕግ እየጣሱ በግልጽ የምርጫ ቅስቀሳ ያደረጉ ፓርቲዎችና ግለሰቦች ከሕግ አግባብ መጠየቅ ሲኖርበት ገና ምርመራ አለመጀመሩ የቦርዱን ንዝሕላልነት ያሳያል። የምርጫውን ክራይቴሪያ ያላሟሉ ግለሰቦች ዶክመንታቸውን አስጨርሰው እስከሚመጡ ምርጫ የለም እየተባለን መሆኑን ስንቶቻችን ተገንዝበናል ???   የሐገሪቱ ሕገ መንግስት በሚያዘው መሰረት ምርጫው መፈጸም ሲገባው በቀነ ቀጠሮ መንዘላዘል ከሕግ አንፃር የሚያስነሳው ውዝግብ ማን ሊፈታው ይችላል የሚለው እንደተጠበቀ ሆኖ ምርጫ ቦርዱ ለተወሰኑ አካላት ጥቅም ሲል በውይይት ሽፋን የሕዝብን መብትና ሕግን እየደፈጠጠ ነው። የምርጫ ቦርድ አካሔድ ማንን ለመጥቀም ይሆን ? ልብ ያለው ልብ ይበል !!! #MinilikSalsawi    
Posted in Amharic News, Ethiopian News

መንግስት ሕግ ለማስከበር ስርዓት አልበኞችን ለማስወገድ በቅድሚያ የራሱ መዋቅር ላይ እርምጃ መውሰድ አለበት።

መንግስት ሕግ ለማስከበር ስርዓት አልበኞችን ለማስወገድ በቅድሚያ የራሱ መዋቅር ላይ እርምጃ መውሰድ አለበት። የመንግስት ዝምታ ወንጀለኞቹን እያበረታታ ሲሆን በጦር ሰራዊቱና በፖሊሱ ውስጥ ስርዓት አልበኝነትን እንዳያስፋፋ ስጋት አለ። መንግስት መዋቅሮቹን ስላዝረከረከ አቅመ ቢስ ሆኗል። መንግስት ተቋማቱንና መዋቅሮቹን ቢያጠነክር የዜጎችን ሰላምና ደሕንነት ማረጋገጥ አያቅተውም። የሐይማኖት ተቋማትን ከሐረርጌ እስከ ጎጃም ሞጣ እያቃጠሉ ያሉት እኮ በመንግስት መዋቅር ውስጥ የፀጥታና የደሕንነት ተቋማትን የሚመሩ የመንግስት መዋቅር ውስጥ ያሉ ባለስልጣናትና አዛዦቻቸው እነጃዋርና የመቀሌ ከበርቴዎች ሕወሓቶች ናቸው። ዱርዬዎችን በገንዘብ ከመግዛት አንስቶ ከባድ ሽብር የሚፈጽሙትን የሚያደራጁ የሚመሩ እቅድ የሚነድፉ ወዘተ እነማን ይህን ጥፋት እንደሚፈጽሙ መንግስት በቂ የደሕንነት መረጃዎች አሉት። የሕዝብን ሰላም እና ደሕንነት ማረጋገጥ የሚቻለው ለወታደራዊ መኮንኖችና ለማይረቡ የዩንቨርስቲ መምሕራኖች የማእረግ እድገት በመስጠት አይደለም። የመንግስት መዋቅር በአወናባጆችና በሰላም አደፍራሾች የተሞላ ነው። መንግስት በራሱ ላይ እሳት ለኩሶ እየተለበለበ ነው።ማጥፋት እየቻለ ስንፍና አቅመቢስ አድርጎታል። መፍትሔው መዋቅሩን መቀየርና በጠንካራ መሰረት ላይ ተቋማትን መገንባት ብቻ ነው። #MinilikSalsawi
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሕዳሴው ግድብ የዲሲ ስብሰባ በስድስት ነጥቦች ላይ ከስምምነት ደረሰ፤ ስምምነቱ ለኢትዮጵያ አይበጅም ተብሏል።

የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስቴር ባወጣው ዝርዝር መሰረት ኢትዮጵያ ግድቡን በሐምሌና ነሐሴ በዓመት ሁለት ጊዜ ትሞላለች። ለዓስር ወር ውሐ በግድቡ ሳይሞላ ለግብጽ ይለቀቃል ማለት ነው። የመንግስት መገናኛ ብዙሃን በስፋት የውይይቱን በሰላም መጠናቀቅ ቢዘግቡም የሆነው ግን በተቃራኒ በመሆኑ የግድቡ የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት ኢትዮጵያን የሚጎዳ ስምምነት እንዳይፀድቅ የገለጹት ስጋታቸው እውን መሆኑ እየታየ ነው። አስተያየት ሰጪዎች የስምምነቱ ዝርዝር በባለሙያዎች ማብራሪያ እንዲሰጥበት እየጠየቁ ነው። Joint Statement of Egypt, Ethiopia, Sudan, the United States and the World Bank BY – U.S. Department of the Treasury Washington, DC – The Ministers of Foreign Affairs and Water Resources of Egypt, Ethiopia and Sudan and their delegations met with the Secretary of the Treasury and the President of the World Bank, participating as observers, in Washington, D.C. on January 13-15, 2020.  The Ministers noted the progress achieved in the four technical meetings among the Ministers of Water Resources and their two prior meetings in Washington D.C. and the outcomes of those meetings and their joint commitment to reach a comprehensive, cooperative, adaptive, sustainable, and mutually beneficial agreement on the filling and operation of the Grand Ethiopian Renaissance Dam. Toward that end, the Ministers noted the following points, recognizing that all points are subject to final agreement: The filling of the
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ትራምፕ የኢትዮጵያን የግብጽንና የሱዳንን ሚኒስትሮች በቢሯቸው አነጋገሩ

የአሜሪካኑ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኢትዮጵያን የግብጽንና የሱዳንን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮችና የውሃ ሃብት ልማት ሚኒስትሮችን በቢሯቸው ተቀብለው ማነጋገራቸው ተሰምቷል።ቀጣዩ ድርድርና ውይይት ወደ ደቡብ አፍሪካ ሊዞር ይችላል የሚሉ ዘገባዎች ከግብጽ እየተሰሙ ነው። Minilik Salsawi Image የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው እንግሊዘኛ ስለማይናገሩ የውይይቱን ጉዳዮች የሚመሩትና የሚያስረዱት የውሃ ሚኒስትሩ ዶክተር ስለሺ ናቸው ሲል አንድ የግብጽ ሚዲያ ጽፏል።የግብጹ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር በዲሲ የሚካሄደው ውይይት እስካሁን ድረስ ምንም አይነት ውጤት እንዳላመጣ ፍንጭ ሰጥተዋል። ትራምፕ ተወያዮቹ በደቡብ ኣፍሪካ ሽምግልና እንዲወያዩ ሀሳብ መስጠታቸው ተሰምቷል ተብሏል።የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ቢሮ እንዳለው ትራምፕ በውይይቱ ዙሪያ የራሳቸውን ሀሳብ የሰጡ ሲሆን ውይይቱ የተሳካና የተመጣጠነ ውጤት እንዲኖረው በተለይ ኢትዮጵያ የግብጽን መብቶችን በተመለከተ መለሳለስ እንዳለባት መክረዋል። Breaking: #America says to #Egypt and #Ethiopia go South Africa… — Egyptian local News (@RenaissanceDam) January 15, 2020 ግብጽ ከትላንት ጀምራ በሃገሯ የተለያዩ የጦር ልምምዶችን እንዲሁም የተለያዩ የጦር ትሪቶችንና የጦር ቤዞችን በማስመረቅ ኋያልነቷን በማሳየት ጫና ለመፍጠር እየሞከርች መሆኑን ከሃገሪቱ ሚዲያዎች ዘገባ ታዝበናል። ምንሊክ ሳልሳዊ pic.twitter.com/k7ZedGblxl — Egyptian local News (@RenaissanceDam) January 15, 2020 Image
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከእገታው የተለቀቁት ተማሪዎች በመንግሥት እጅ ናቸው ማለት ምን ማለት ነው ???

ከእገታው የተለቀቁት ተማሪዎች በመንግሥት እጅ ናቸው ማለት ምን ማለት ነው ??? … መንግስት ወዴት እያመራ ነው ??? የመንግስት ባለስልጣናት መቀባጠርና ማደናገር አሁንም ቀጥሏል። የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ እንዳለው የኦሮሚያ ክልል የአስተዳደር እና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ ከእገታው የተለቀቁት ተማሪዎች አሁን በመንግሥት እጅ መሆናቸውን ተናግረዋል። እገታውን የሚያጫውተው የመንግስት መዋቅር ነው ስንል ከምንም ተነስተን አይደለም። ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ሰው ንጉሱ ጥላሁን ጀምሮ የኦሮሚያና አማራ ክልል ባለስልጣናት ሳይናበቡ የሚናገሩት ነገር ሁሉ መንግስት በተማሪዎች እገታ ላይ የራሱ ሚና እንዳለው በቂ ምስክር ነው። መንግስት ተማሪዎቹን ሆን ብሎ አጀንዳ ለመፍጠር አግቷል ወይንም አግቶ በወለጋ ለሚያካሂደው ጦርነት እንደ ሽፋን እየተጠቀመባቸው ነው።ከታች በምድርና ከላይ በአየር ኃይል ጦርነት በኦነግ ወታሮች ላይ የከፈተው መንግስት የሚፈልገው ግብ ላይ እስኪደርስ ተማሪዎቹን እንደ ካርድ እየተጠቀመባቸው አስመስሎበታል። ከእገታ ተለቀቁ የተባሉ ተማሪዎችን ዛሬም እንዳላገኙ ቤተሰቦቻቸው እየተናገሩ ነው።ታጋቾቹ በመንግስት እጅ ከሆኑ ተሐድሶ ተሰጥቷቸው የሚለቀቁም ከሆነ መንግስት በሚዲያዎቹ በግልጽ መስመር ማሳወቅ ሲኖርበት የተማሪዎቹን ወላጆች በስጋት ማኖር ሕዝብን ከሚያስተዳድር አካል አይጠበቅም። #MinilikSalsawi ከእገታው የተለቀቁት ተማሪዎች በመንግሥት እጅ ናቸው ማለት ምን ማለት ነው ??? … መንግስት ወዴት እያመራ ነው ??? #BringBackOurStudents #ReleaseThem #የታገቱትይለቀቁ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ብአዴን/አዴፓ በብልጽግና ስም ተሸፋፍኖ የራሱን ወንጀል በሕወሓት እየደበቀ ሊኖር ይፈልጋል።

ብአዴን/አዴፓ በብልጽግና ስም ተሸፋፍኖ የራሱን ወንጀል በሕወሓት እየደበቀ ሊኖር ይፈልጋል። ገና ፖለቲካን ያልባነነው አማራ ክልል ላይ በመንደርተኝነት እየተደራጀ ያለው የፖለቲካ አሽከሩ ብአዴን/አዴፓ ለክልሉም ሆነ ለክልሉ ነዋሪ አንዳችም ነገር በተግባር ሳይሰራ በለውጥ ስም በወሬ ብቻ ራሱን ማኮፈስ ይዟል። የክልሉን ባለሐብቶች ገንዘብ እየሰበሰበ የባለሐብቶችን ሕገወጥ ንግድ በመመሳጠር እየደገፈ ለክልሉ ድሕነትን እንጂ እድገትን አላመጣም። የሰኔ 15 2011 ጉድ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ሁከትና ሽብር በክልሉ ላለመፈጸሙ ምን ዋስትና አለ ? የሞጣው አይነት ሃይማኖት ላይ የተቃጣ ጥቃት በድጋሚ ላለመፈጸሙ ምን አይነት ዋስትና አለ ? የክልሉ ገዢ ፓርቲ ሰዎችና ተቋማት ላይ ከመጠቋቆሙ በፊት መረጃና ማስረጃ ካለው ሰዎቹንና ተቋማቱን ለፍርድ ለምን አያቀርብም ? ለሕዝብስ ለምን ይፋ አያደርግም ? ይህ መልስ ያልተገኘለት የፓርቲው የሌሎችን ስም ማጥፋት በራሱ መንግስታዊ ወንጀል ነው። በአማራ ክልል የሚገኙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ላይ ሽብር ለመፈጸም ሴራ ከማቀድና ለመተግበር ከመሮጡ በፊት ለሕዝብ የሚበጁና ከፖለቲካ አሽከርነቱ ነጻ የሚያወጡ ተግባራዊ ስራዎች ቢሰራ የተመረጠ ይሆናል።የክልሉ ፖለቲከኞችና ባለሐብቶች ለፖለቲካ ፍጆታ እና ለሕገወጥ ሸቀጦች ማራገፊያ ሲሉ የሚፈጽሙትን ሕገወጥ ድርጊት ሊያቆሙ ይገባል። ምርጫው እስካልተጭበረበረ ድረስ አማራ ክልል ላይ ብአዴን/አዴፓ አያሸንፍም። ይህንንም ስለሚያውቅ የተቃዋሚ ድርጅቶች ላይ ሽብር ለመፍጠር እቅድ ነድፎ እየተንቀሳቀሰ ነው። ይህንን እቅዱን በጨረፍታ በብልጽግና ፓርቲ መሪ ሃሳብ ላይ ክልሉን ጠቅሶ ይፋ አድርጓል። የሰለጠነ ፖለቲካ ትርጉም ያልገባው ብአዴን/አዴፓ በራሱ የማይተማመንና ሆዳም አመራሮች የተሞሉበት ስለሆነ ባለፉት ሶስት አስርተ አመታት ይህ ነው የሚባል የሰራው
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ወደ ራሱ የሚጎትትህ በራሱ ቆሞ መሄድ ስለማይችል ነዉ።

የኦሮሞን ደደብ ፖለቲከኛ ስተች የኦሮሞ ጥላቻ ያለበት የምትል ታፔላ ለጥፎ ከሌላዉ ሊያላጋ ይሞክራል….ህወሓትን ስተች የትግራይን ህዝብ ሰደበ ይሉሐል…ብልፅግና አካሄዱ ትክክል አይመስለም ስትል ዶ/ር ዐቢይ ጋር ወስዶ ያላትምሀል….አህመዲን ጀበል ለምን እንዲህ አለ ስትል ለሙስሊም ጥላቻ ያለሁ ይላል….ዘመድኩን በቀለ ልክ ነዉ ስትል የመስቀል ጦርነት ሊያነሳ ነዉ ብሎ ያጉረጠርጣል…እስክንድር ለባላደራዉ ስትል የኦሮሞ እና የእስላም ጥላቻ ቅብርጥሴ እያለ ዉገረዉ ለማለት ድንጋይ ያቃብላል።. ከፍረጃ ይቅደም አጃ😂 ሺ ፈሳም አንድ ጎማ አይነፋም!! የነተበ ጭንቅላት ተሸክሞ ሲንቀዋለል የሚዞር ከወሸላ ቀዳዳ የጠበበች ጭንቅላት ይዞ የሚሽከረከር መንጋ በሞላበት ሀገር ራስን ችሎ መቆም ለፍረጃ ይዳርግሃል። የራሱን የLogic ፍልስፍና ይዞ የመጣዉን ሶቅራጠስን ሄምሎክ መርዝ አጠጥተዉ ከገደሉት በሗላ አለማችን ብዙ ጊዜያቶችን ካሳለፈች ሗላ ሶቅራጠስን ስፈትሹት ዛሬ አቴናውያን የሚኮሩበት ፈላስፋ ሆነላቸዉ። ያነ እኮ ገለዉታል። በዚች ሀገር Context የራሱ የጠበበ አስተሳሰብ ዉስጥ ካልዶለተ እንቅልፍ አይወስደዉም። ወደ ራሱ የሚጎትትህ በራሱ ቆሞ መሄድ ስለማይችል ነዉ። እምቢ ስትለዉ ስም ለጥፎ ፈርጆ ልጠልፍህ ይሞክራል። ከእባብ በላይ ተንኮለኛ ሆኖ ያፈጥብሃል። ሃያ ገፅ ብትፅፍ ሁለት መስመር መዞ ሲያብጠለጥል ይዉላል። ሃያ ደቂቃ ብታወራ የሁለት ሰከንዷን ቀንጭቦ የሃያ ሰአት ዶክመንተሪ ሊሰራ ሲጋጋጥ ታየዋለህ። ቢያንስ እንደ ፈረንጆቹ Word by word Line by Line አንብቦ አይረዳም እሱ ሀሳቡ መጥቶ የሚያቀረሽበት ቅርሻቱ ላይ ነዉ ትኩረቱ። የኦሮሞን ደደብ ፖለቲከኛ ስተች የኦሮሞ ጥላቻ ያለበት የምትል ታፔላ ለጥፎ ከሌላዉ ሊያላጋ ይሞክራል….ህወሓትን ስተች የትግራይን ህዝብ ሰደበ ይሉሐል…ብልፅግና አካሄዱ ትክክል
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ዩንቨርስቲዎች ውስጥ ያለው አለመረጋጋትና ግድያ በነማን እንደሚመራ መንግስት በቂ መረጃ አለው።

ዩንቨርስቲዎች ውስጥ ያለው አለመረጋጋትና ግድያ በነማን እንደሚመራ መንግስት በቂ መረጃ አለው። መፍትሔውም በእጁ አለ ! Minilik Salsawi ከበቂም በላይ እጅግ የሚያስደነግጥ መረጃና ማስረጃ በእጁ አለው። ጥቂት በሕዝብ ላይ ቁማር የሚጫወቱ የመንግስት መዋቅር ባለስልጣናት፣ ፖለቲከኞችና በየጉሮኖው ዩንቨርስቲዎችን ያቋቋሙ ባለሐብቶች፣ የቀድሞ ጥቅማቸው የተገፈፈባቸው ግለሰቦች እና በገንዘብ የተደለሉ የዩንቨርስቲ መምሕራንና አስተዳዳሪዎች በዩንቨርስቲ ውስጥ ለሚነሱ ችግሮች ተጠያቂ ወንጀለኞች እንደሆኑ መንግስት በቂ መረጃና ማስረጃ በእጁ አለ። የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እና የፌዴራል ፖሊስ እንዲሁም አቃቢ ሕግ ጥቂት የመንግስት መዋቅር ለግጭት የሚያውሉ ከፍተኛ ባለስልጣናትን ወንጀል ለመሸፈን ሲሉ የባለሐብቶችን ገበና ላለማጋለጥ ሲሉ የሐገሪቷን ሰላም እያደፈረሱ የደሐውን ልጅ ደም በየመንገዱ እንዲፈስ እያደረጉ ከመሆኑም በላይ ትውልዱን እየገደሉ ነው። ይህ አትኩሮት የተነፈገው ትኩሳት እንዲበርድ ሁሉም መስራት ሲገባው የሕግ የበላይነትን በመደፍጠጥ ሌላ ጥፋቶች እንዲስፋፉና ዩንቨርስቲዎች እንዲዘጉ እየተደረገ ነው። በተማሪዎች ግድያና በዩንቨርስቲ ሰላም መደፍረስ ላይ የሚሰሩ ፖለቲከኞችና ባለሐብቶች ከነተባባሪዎቻቸው መንግስት ይፋ ያድርግ ። መንግስት በአስቸኳይ ወንጀለኞችን ለሕዝብ ይፋ ማድረግ አለበት። #MinilikSalsawi
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ከ3ኛ ፎቅ ተማሪ ተወርውሮ መገደሉን ተከትሉ ላልተወሰነ ጊዜ ተዘጋ

ለድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ ዩኒቨርሲቲያችን ሰኞ ታህሳስ 20/2012 ዓ/ም ሊጀመር የነበረው ትምህርት ባጋጠመን ወቅታዊ ችግር ምክንያት በዩኒቨርሲቲያችን ትምህርት ማስቀጠል የሚያስችል ሁኔታ አለመኖሩን ተረድቷል:: ስለሆነም የመማር ማስተማር ሂደቱ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቋረጥ የዩኒቨርሲቲ ሴኔት ወስኗል:: ስለሆነም ዩኒቨርሲቲው ከታህሳስ 20/2012 ዓ/ም በኋላ ምንም አይነት አገልግሎት የማይሰጥ መሆኑን እየገለጽን የተማሪዎችን የመልሶ መቀበያ ጊዜ ወደ ፊት በሚዲያ የሚገልጽ መሆኑን ወስኗል:: Image ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የ3ኛ አመት ተማሪ ከ3ኛ ፎቅ ህንፃው ተወርውሮ በመሞቱ እስከሚቀጥለው ድረስ ተጨማሪ ማስተማሪያ የመማር ማስተማር ሂደቱን አቁሟል ፡፡ ይሁኔ አለማየሁ የ3 ኛ ዓመት የባንክ ተማሪ ነበር።በሁለት ወራት ውስጥ በተመሳሳይ ከፎቅ ተወርውሮ ተማሪ ውስጥ ሲገደል 2ኛ ጊዜ ነው ፡፡ Image Image የሟች ተማሪ አስከሬን በነገው እለት ወደ ወለጋ ጉሊሶ የሚላክ መሆኑ ታውቋል ። ተማሪ ይሁኔ ከሞተ በኋላ በዩንቨርስቲው ውስጥና ውጪ ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል። በርካታ ተማሪዎች ዩንቨርስቲውን ለቀው የወጡ ሲሆን ከፊሎቹ ቀደም ብለው የገብርኤልን አመታዊ ንግስ ለማንገስ ወደ ቁልቢ ተጉዘዋል። #Ethiopia:#DireDawa Univ suspended teaching-learning process until further notice after a 3rd year student was thrown off a 3rd floor of a building to his death. Yihune Alemayehu was a 3rd year Banking student. It's the 2nd time a student is killed in the same univ in two months. pic.twitter.com/7O4nD67zUS — Addis Standard (@addisstandard) December 28, 2019  
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

ከፍተኛ ትችትና ተቃውሞ ያጋጠመው የኢትዮጵያ ታሪክ መማሪያ ሞጁል ላይ ምሁራን ከስምምነት ሊደርሱ አልቻሉም።

አደገኛውና ሕዝብን የሚያጋጨው ሌላ ቁስል የሚፈጥር ቁስሉን በመነካካት ሌላ ቁርሾ የሚሻ የኢትዮጵያ ታሪክ መማሪያ ሞጁል ባሕልን፣ እምነትን፣ የዜግነት ግዴታና የሙያ ክብር ያላገናዘበና ያላከበረ በተወሰኑ ሕዝቦች ላይ ያነጣጠረ ጥላቻ የተሞላበት መሆኑ ምሁራን ይናገራሉ። በሃሰት ታሪክ እና በሞያው እውቀት በሌላቸው ካድሬዎች የተዘጋጅ ነው:: የፈጠራ ታሪክን ጥላቻ የተሞላበት የታሪክ ማስረጃ የሌላቸውን ታሪኮች ለከፍተኛ ትምሕርት ተቋማት መማሪያነት ማዘጋጀት ወንጀል ነው።ሌላ ቁስል የሚፈጥር ወይም ቁስሉን በመነካካት ሌላ ቁርሾ የሚሻ የትናንቱን ጉዳት በእርቅና በይቅርታ ከማስቀረት ይልቅ የበለጠ ጥርስ መነካከስን የሚያበረታታ ባለመስማማትና በትችት የተበተነውን ውይይት በስምምነት ጸደቀ የሚል ሰፊ ፕሮፓጋንዳ መንግስት ሊሰራበት ተዘጋጅቷል። አዲሱ የታሪክ ትምህርት የማስተማሪያ ሞጁል/ሰነድ የኃላ ቁስልን ያልተወ፣ የሚያጋጭ ፣ መልካም የታሪክ ጎንን የማያስተምር ፣ ለፖለቲካ አጀንዳና የግለሰቦችን ፍላጎት የተጻፈ ፣ ሚዛናዊነት የጎደለው፣ ታሪክን ለ አገር ግንባታ ለመጠቀም ያልፈለገ፣ አብሮነትን የጨፈለቀ ፣ ትውልድን የማያፈራ ፣ ከታሪክ እየተማረ ጠንካራ አገር መፍጠር የማያስችል ወዘተ የሚል ትችት በምሁራን ተሰንዝሮበታል። ባሕልን፣ እምነትን፣ የዜግነት ግዴታና የሙያ ክብር ያላገናዘበና ያላከበረ በተወሰኑ ሕዝቦች ላይ ያነጣጠረ ጥላቻ የተሞላበት መሆኑ ምሁራን ይናገራሉ።#MinilikSalsawi
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የደሕንነት ተቋሙ በሐገር ውስጥ ለሚፈጸሙ ጥቃቶች ቅድመ ጥንቃቄና መከላከል ባለማድረጉ ተጠያቂ ነው።

(ምንሊክ ሳልሳዊ) የደሕንነት ተቋሙ በሐገር ውስጥ ለሚፈጸሙ ጥቃቶች ቅድመ ጥንቃቄና መከላከል ባለማድረጉ ተጠያቂ ነው። መንግስት የደሕንነት ተቋማቱን ለመፈተሽ ፈቃደኛ አይደለም፤ ወይም ሆን ተብሎ የሚሰራ ሴራ አለ።   የደሕንነት ተቋሙ ድክመት አግጥጦ እያየነው ነው።ችግሩ ሕዝብ ጋር አይደለም። ችግሩ የሐይማኖት ተቋማት ጋር አይደለም፣ ችግሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር አይደለም፣ ችግሩ ወደ ሌሎች የምንጠቁምባቸው አካላት ጋር አይደለም፤ ችግሩም መፍትሔውም የመንግስት መዋቅሮች የደሕንነት ተቋሙና መንግስት ጋር ነው።   የደሕንነት ተቋሙን ስም በመቀየር ብቻ የሕገር ሰላምን ማረጋገጥ አይቻልም።የሐገራችን የደሕንነት ተቋም ይሁን በስሩ ያሉት በየክልሎቹ የሚገኙት የጸጥታና የደሕንነት ክፍሎች ጥቃት ከተፈጸመ በኋላ ጉዳት ከደረሰ በኋላ ሲዝቱና ሲፎክሩ ሕዝብ ሰብስበው ዘራፍ ሲሉ እያየን ነው። ይህ የሚያሳየው የደሕንነት መስሪያ ቤቱን ዝርክርክነትና የጥቃት ቅድመ ጥንቃቄ አለማድረግን ንዝሕላልነት ነው።ንፁሀን ዜጎችን ከማፈን ወጭ ስራ የለውም። ኢትዮጵያ ውስጥ የ ISIS አባሎችን ያዝኩኝ ብሎ መግለጫ ሲሰጥ ሳቄ ነዉ የመጣው ምክንያቱም ተያዙ የተባሉት ንፁሀን ነበሩ መክሰሻ መረጃ ሲያጡ በገንዘብ ዝውውር በሚል ቀይረው ክስ አመጡላቸው ሁሉም በአሁን ሰአት ከስር ተፈተዋል!   በተደጋጋሚ መንግስት የደሕንነት መስሪያ ቤቱን እንዲፈጽህ ብንጮኸም ሰሚ አልተገኘም። መንግስት ሆን ብሎ ጥቃት ያስፈጸመ እስኪመስል ድረስ በሐገርና በሕዝብ ላይ ጥቃቶች በተደጋጋሚ እየደረሱ ነው። ይህ ጉዳይ በጣም አሳሳቢ ነው።አንድ የደሕንነት ተቋም በአንድ አገር ውስጥ የሚደርሱ ጥቃቶችን እና ችግሮችን ሳይተገበሩ በፊት ቀድሞ የማስወገድና የሐገርና የሕዝብን ደሕንነት የመጠበቅ ግዴታ አለበት። መንግስት የደሕንነት ተቋማቱን የመፈተሽና የማስተካከል ግዴታ አለበት። #MinilikSalsawi  
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሃገራዊ ምርጫው ከአንድ እስከ ሁለት አመት ሊራዘምና የሽግግር ኮሚሽን ሊቋቋም እንደሚገባ ኢዴፓ አስታወቀ

ምርጫው እንዲራዘም ኢዴፓ ጠየቀ – ኢዴፓ ሐገራዊ ለውጡ ከሽፏል ብሏል፡፡ ቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ እንዲራዘም የኢዴፓ ብሔራዊ ምክር ቤት በመግለጫው ጠይቋል። አክራሪ ኃይሎች በተጠናከሩበት፣ ማሕበራዊ ሚዲያና ሌሎችም መገናኛዎች ከፍተኛ ቅራኔ በሚያስተላልፉበት እንዲሁም የፖለቲካ ሽግግር ባልተደረገበት ወቅት ቀጣዩ ምርጫ ለኢትዮጵያ ጉዳት እንጅ ጥቅም አይኖረው ሲል የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ብሔራዊ ምክር ቤት በመግለጫው አትቷል። የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ምክር ቤት በሃገሪቷ ወቅታዊ ሁኔታ አስመልከቶ ጋዜጣዊ ሰጥቷል፡፡በመግለጫውም ኢህአዴግ ህዝቡ የሰጠውን ሁለተኛ እድል እንዳልተጠቀመበት ነው ያስታወቀው፡፡ገዢው ፓርቲ የለውጡ አካል መሆን ሲገባው ራሱ መሪና ባለቤት መሆኑ፤ ኢህአዴግ እኔ አውቅላችኋለሁ ከሚል አስተሳሰቡ እንዳልተላቀቀ ማሳያ ነው ብሏል፡፡በህዝብ ጥያቄ መነሻነት የመጣው ለውጥ ፍኖተ ካርታ ያስፈልገዋል ብለን በተደጋጋሚ ሃሳብ ብንሰጥም የሰማን የለም ያለው ኢዴፓ፤ አሁንም በዚህ የለውጥ ጉዞ መዳረሻችን የት እንደሚሆን አይታወቅም ነው ያለው፡፡ራሱን የለውጥ ሃይል ብሎ የሚጠራው አካል በሃገሪቷ በየጊዜው የሚነሱ ግጭቶችን ማስቆምና መቆጣጣር እንዳልቻለም ገልጿል፡፡ በኢህአዴግ ውስጥ ያለው የስልጣን ሽኩቻና መከፋፈል ሃገሪቷን ወደ አላስፈላጊ መንገድ እየመራት እንደሆነም ተናግሯል፡፡ ምክር ቤቱ በአሁኑ ወቅት መንግስትም ሆነ ሕዝብ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችል መዋቅርና ሞራል የላቸውም ብሏል። በዚህ ዓመት የሚካሄደው ምርጫ ከአንድ ዓመት እስከ ሁለት ዓመት ለሚደርስ ጊዜ በማራዘም ሁሉን አቀፍ የእርቅና የሽግግር መንግስት በአጭር ጊዜ እንዲቋቋም ጠይቋል። ላለፉት 18 ወራት በአገራችን ሲካሄድ የነበረውና በህዝብ ውስጥ ከፍተኛ የለውጥ ተስፋ ፈጥሮ የነበረው “የለውጥ ሂደት” በሚያሳዝን ሁኔታ ወደ መክሸፍ ደረጃ መቃረቡን የኢዴፓ ምክር ቤት ገልጿል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በብሄራዊ የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት ላይ ዘለፋ መሰንዘራቸው የውሃ፣ መስኖና ኤሌከትሪክ ሚኒስትሩ ክደዋል።

ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ክደዋል። ኢትዮጵያ ተስማማችም አልተስማማችም የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት ስጋት እውን ይሆናል። በአሜሪካና አለም ባንክ ጫና አብዛኛው ጉዳዮች ላይ ሀገራቱ መስማማታቸው ታውቋል።የሕዳሴው ግድብ ጉዳይ በግብጽ አሸናፊነት ሊጠናቀቅ እንደሚችል ፍንጮች ከሚኒስትሩ መግለጫ ታይተዋል። የሕዳሴው ግድብ ድርድር ኢትዮጵያን እየጎዳ ነው ባሉ በብሄራዊ የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት ላይ ዘለፋ መሰንዘራቸው የውሃ፣ መስኖና ኤሌከትሪክ ሚኒስትሩ ክደዋል።አለም ባንክና አሜሪካ ኢትዮጵያን ዲፕሎማሲያዊ ጫና እንዳደረጉባት ታውቋል። የዓባይ ውሀ ተፈጥሯዊ ፍሰቱ በድርቅ ወይም በሌላ ምክን ያት ቢዛባ ግብፅ ማግኘት ይገባኛል የምትለውን የውሀ መጠን እንዳይነካ ሽፋን የሚሰጥ መመሪያ ይዘጋጃል የሚል ያስገቡት ነጥብ አሁን የኢትዮጵያን ተደራዳሪዎችና ባለሙያዎች እያወዛገበ ነው።የሕዳሴው ግድብ ድርድር እየተመራበት ያለው መንገድ የኢትዮጵያን ጥቅም እየጎዳ በመሆኑ ሊቆም ይገባል ተባለ:: የውሀ መስኖና ኤነርጂ ሚኒስትሩ በጉዳዩ ላይ ከብሄራዊ የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት ጋር መግባባት አቅቷቸው የቴክኒክ ቡድኑ አባላት ላይ ዘለፋ በመሰንዘራቸው ስብሰባው ረግጠው የወጡ ሙያተኞች መኖራቸው ተሰምቷል። ውይይቱን የኢትዮጵያንም ጥቅም በሚጠብቅ መልኩ ማስቀጠል ከተቻለ መልካም : ካልሆነ ግን የሶስትዮሽ ውይይቱን ኢትዮጵያ ያለምንም ተጨማሪ እርምጃ ማቆም አለባት ነው ያሉት የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት። በቀጣዩ የፈረንጆቹ ጥር 8 እና 9 ቀን 2020 በአዲስ አበባ በሚካሄደው ስብሰባ ከስምምነት ይደረስባቸዋል ተብሎ ይታመናል ያሉት ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ፥ ካልተስማሙ የግድቡን ውሃ አሞላልና አስተዳደር የሚያካሄድበትን ህግ አንቀጽ 10 በስምምነት ይተገበራል ብለዋል። አንቀጽ 10 የሚተገበር ከሆነ የምንወስደውን አማራጭ መንግስትን አማክረን እንወስናለን ነው ያሉት ሚኒስትሩ። #MinilikSalsawi የበለጠ መረጃ እነዚህን ሊንኮች
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሕወሓት የኢሕአዴግ ወራሽ መሆኗን የሚገልጽ ደብዳቤ ለምርጫ ቦርድ ልታስገባ ነው ተባለ

ሕወሓት የኢሕአዴግ ወራሽ መሆኗን የሚገልጽ ደብዳቤ ለምርጫ ቦርድ ልታስገባ ነው ተባለ። በዶክተር አብይ አሕመድ መሪነት የተቋቋመው የብልጽግና ፓርቲ ኢሕአዴግን ይተካል ተብሎ ሲጠበቅ ሕወሓት በውሕዱ አዲስ ፓርቲ ውስጥ ላለመሳተፍ በመፈለጓ መገንጠሏ ይታወቃል ። ኢሕአዴግ መፍረስ የለበትም የምትለው ሕወሓት የኢሕአዴግ ወራሽ መሆኗን እንዲታወቅላት ለምርጫ ቦርድ ደብዳቤ ልታስገባ መሆኑን የመቀሌ ምንጮች ገልጸዋል። ሕወሓት የፌዴራል ኃይሎች የምትላቸውንና ከዚህ ቀደም ከኢሕ አዴግ የተሰናበቱ አመራሮችን በመያዝ ኢሕ አዴግን ከሞተበት አንስቼ እውን አደርገዋለው ብላ መዛቷ ይታወቃል። የትግራይ ክልል በጀትን ለጥላቻ ዘመቻ፣ በስብሰባና በአበል ክፍያ የጨረሰችው ሕወሓት በድክመቷና በሞቷ ላይ ከባድ ኪሳራ እየደረሰባት መሆኑን ምንጮቹ ይናገራሉ። የመቀሌ ምንጮቻችን እንዳሉት የሕወሓት አመራሮች ተጨማሪ ገንዘቦችን ወደ ውጪ ሐገር በማሸሽ ላይ ሲሆኑ በውጪ የሚኖሩ ሕገወጥ የገንዘብ አዘዋዋሪዎችን በመጠቀም እንደሚያሸሹም ታውቋል። ካሁን ቀደም ከሐገር የዘረፉት አልበቃ ብሏቸው ተጨማሪ ዘረፋዎችን የሚያካሂዱት የሕወሓት አመራሮች በመሐል አገር ከፍተኛ የዶላር ግዢ በጥቁር ገበያ እየፈጸሙ መሆኑ ቢታወቅም የመንግስት ዝምታ አሳሳቢ መሆኑን ምንጮቹ ይገልጻሉ። ስልጣናቸውን በማጣታቸው የሚቆጩት ሕወሓቶች በስብሰባ ብቻ ጊዜያቸውን እንደሚያጠፉ ይታወቃል። #MinilikSalsawi
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የቻይናው አምባሳደር ተጠርተው ማብራሪያ ሊጠየቁ ይገባል !

ቻይና ትግራይና የፌዴራሉ ሕገ መንግስት ? የቻይናው አምባሳደር ተጠርተው ማብራሪያ ሊጠየቁ ይገባል ! የኢፌዲሪ ሕገ–መንግሥት የፌድራል መንግሥትን ሥልጣንና ተግባር በወሰነበት አንቀጽ 51 (4) የውጭ ግንኙነትን ስትራቴጂና ፖሊሲ ማውጣትና ማስፈጸም የፌድራል መንግሥቱ ሥልጣን መሆኑን በግልጽ ይደነግጋል። የቻይና መንግስት ከኢትዮጵያ መንግስት እውቅናና ፈቃድ ውጪ ለፌዴራሉ መንግስት የውጪ ጉዳይና ኢንቨስትመት ቢሮ ሳታሳውቅ ባለስልጣናቷን ወደ ትግራይ ክልል ለመላክ አይሮፕላን ማሳፈሯ የሃገር ሉዓላዊነትን ከመድፈር ተለይቶ አይታይም። የኢትዮጵያ መንግስት ከኤርፖርት የመለሳቸው የቻይና ባለስልጣናት የመንግስትን አሰራር በመጣስ ወደ መቀሌ ሊያቀኑ የነበሩ መሆኑ በውስጥ ጉዳያችን ንትርክ ተከትሎ ያሳዩን ንቀት ነው። ወደ ሆንግኮንግም ሆነ ታይዋን ለመሔድ የሚፈልጉ የሃገራት ባለስልጣናት የቻይናን ፈቃድ እንደሚጠይቁ ሁሉ ቻይናም ወደ ማንኛውም የኢትዮጵያ ክልሎች ለመሔድ የፌዴራሉን መንግስት ፈቃድ መጠየቅ ነበረባት፤ በባለስልጣናቱ ላይ የተወሰደው እርምጃ ተገቢ ቢሆንም አምባሳደሯ ግን ማብራሪያ ሊሰጡ ግድ ይላል። ጉዳዩ እንዲህ ነው  – 9 አባላት የያዘ ከአንዲት የቻይና ግዛት የተላከ ልኡክ ትላንት ማታ በ 1 ሰዓቱ የአየር በረራ ለስራ ጉዳይ ወደ መቐለ ለመብረር ፍተሻ ጨርሰው ለመብረር ሲዘጋጁ ድንገት ‘ከውጭ ጉዳይ ነው የታዘዝነው’ ባሉ የአየር መንገዱ ሰዎች ትእዛዝ መሰረት ቦሌ ኤርፖርት ላይ ወደ መቐለ እንዳይጓዙ መከልከላቸውና አ.አ እንዳደሩ ታውቋል። በመሀከላቸው ከቻይና ኤምባሲ ዲፕሎማት ከልኡኩ ጋር ቢኖርም የጉዞአቸው ምክንያት ለማብራራት ቢሞክሩም ”እኛም ታዘን ነው የምናውቀው ነገር የለም” የሚል መልስ ተሰጥቶዋቸዋል። ኤምባሲው ትላንት አመሻሽ በስልክ ደውሎ ለውጭ ጉዳይ ከፍተኛ ሀላፊዎች ቅሬታውን ገልጿል ተብሏል። ቀደም ሲል
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኑሮ ውድነቱ የኤክሳይዝ ታክስ ጭማሪው ከፀደቀ በኋላ ይንራል መባሉ ህዝቡን አሳስቦታል።

የኑሮ ውድነቱ የኤክሳይዝ ታክስ ጭማሪው ከፀደቀ በኋላ ይንራል መባሉ ህዝቡን አሳስቦታል። የተመቻቸው በሕዝብ ገንዘብ ፖለቲካውን እየለጠጡ የህዝብን ሰላም ያናጋሉ። ይህም ያልበቃቸው የመንግስት ፖለቲከኞች በሕዝብ ላይ ተጨማሪ የኑሮ ውድነት አደጋ ደቅነዋል። በጀቶች ሁሉ እየሞተ ያለውን ኢኮኖሚ ከመደጎም ይልቅ ለፖለቲካ ድጎማ መዋሉ ችግሩ እንዲወሳሰብ አድርጎታል። ቅንጦት በሚል የማጭበርበሪያ ቃል የታጀበው አዋጅ የሕዝብን ፍላጎት ያላገናዘበና ያልተጠና ሲሆን በ አበዳሪ አለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ጫና የሚተገበር አደገኛ አካሔድ ነው። ስኳርና ዘይት የኤክሳይዝ ታክስ ጭማሪው ከፀደቀ የዋጋ ጭማሪ ይደረግባቸዋል ። መንግስት በሃገር ውስጥ በሚመረቱና ከውጪ በሚገቡ የተመረጡ ምርቶች ላይ ተጨማሪ ታክስ ጥሏል። ….. በ100 ብር ይሸጥ የነበረ 1 ሊትር ዘይት 140 ብር …. 45 ይሸጥ የነበረው 1 ኪሎ ስኳር 52 ብር ……. 12 ብር የሚሸጥ ለስላሳ 15 ብር ይገባል፤10 ብር የነበረ 1 ሊትር የታሸገ ውሃ 11.50 ብር ……. 15 ብር የነበረው ቢራ 19.50 …. ሸቶዎች፣ የቁንጅና እና መኳኳያ ምርቶች … ዋጋው በእጥፍ ይጨምራል … ሂዩማን ሄር፣ ቅንድብ፣ የእንስሳት ጸጉር እና የመሳሰሉት…. ( https://mereja.com/amharic/v2/184297 ይመልከቱ) መንግስት የራሱን ገቢ ለማሳደግ በሚሮጥበት ወቅት የሕዝብን ፍላጎት መለካት አልቻለም። ይህ ታክስ የሐገር ውስጥ አምራቾችን ያበረታታል ቢባልም የሃገር ውስጥ ምርቶች የሕዝቡን የፍላጎት ኮታ ምን ያህል ያሟላል የሚለውና የጥሬ እቃ ምንጮችን ታክስ አስመልክቶ የሚነሱ ጥያቄዎችን መመለስ አልቻለም። የሐገር ውስጥ አምራቾች ምርቶቻቸውን ለመስራት ከውጪ የሚያስገቡት ጥሬ እቃ ላይ መንግስት የሚያስከፍለው ታክስ ቢሰላ እንዲሁም
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የአሜሪካ ኮንግረስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከስልጣን የማስወገድ ውሳኔን ደገፈ

የአሜሪካ ኮንግረስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከስልጣን የማስወገድ ውሳኔን ደገፈ ፕሬዝዳንቱ ሁለት ክሶች ቀርበውባቸው ከስልጣናቸው እንዲነሱ የቀረበውን ሐሳብ የኮንግረሱ አባላት በአብላጫ አጽድቀውታል ። impeachment ማለት በስልጣን ላይ ያለ ፕሬዝዳንት ጥፋት እጥፍተሀል ተብሎ 435 አባለት ባሉት በተወካዮች ምክርቤቱ (House of Representatives /congress) ክስ ሲቀርብበት ማለት ነው።በአሜሪካን ህገመንግስት በስልጣን ላይ ያለን ፕሬዚዳንት የመክሰስ ብቸኛ ስልጣን ያለው የተወካዮች ምክርቤት (House of Representatives ) ብቻ ነው።ፕሬዚዳንቱ ይከሰስ የሚለውን በምክርቤቱ ለመወስን ደግሞ ቢያንስ 216 የተወካዮች ምክርቤት አባላትን ድምጽ ማግኝት ይኖርበታል የተወካዮች ምክርቤት (House of Representatives )ዛሬ ትራምፕን በሁለት ወንጀል ከሶታል አንደኛው ስልጣንን ያለአግባብ መጠቀም ( abuse of power) ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የተወካዮች ምክርቤት ሰራውን በትክክል እንዳይሰራ በማወክ ወይም እንቅፋት በመሆን (obstruction of Congress) ናቸው።ፕሬዝዳንቱ የተከሰሰበት ወንጀል 100 አባላት ላሉት ለሕግ መወሰኛ ምክር ቤት (senate) ቀርቦ ክሱ ይሰማል። በህግ መወሰኛው ምክርቤት ካሉት ከመቶ ሴናተሮች 75ቱ ፕሬዚዳንቱ በተከሰሰበት ክስ ጥፋተኛ ነው ብለው ድምጽ ከሰጡ ፕሬዚዳንቱ ከስልጣን ይወርዳል ማለት ነው።በአሜሪካን ሀገር በ230 አመት ታሪክ ፕሬዚዳንት ከሆኑት 45 ፕሬዝዳንቶች 3 ፕሬዝዳንት ብቻ ናቸው በተወካዮች ምክርቤት (House of Representatives ) ክስ ቀርቦባቸው ጉዳያቸውን ለመጨረሻ ጊዜ ለመወሰን ወደ ሕግ መወሰኛ ምክር ቤት (senate) የተላከው አንደኛው ፕሬዝዳንት Andrew Johnson በ1868 ሌላው ፕሬዝዳንት Bill Clinton in 1998 ሶስተኛው ደግሞ  አሁን በስልጣን ላይ ያለው ፕሬዝዳንት Donald John Trump ናቸው በJuly 1974 ፕሬዝዳንት Nixon በተወካዮች ምክርቤት
Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

የንግድ ባንክ የውጭ ምንዛሬ ተመን አንድ ዶላር ወደ 32.22 የኢትዮጵያ ብር ደርሷል፡፡

በዛሬው የንግድ ባንክ የውጭ ምንዛሬ ተመን አንድ ዶላር ወደ 32.22 የኢትዮጵያ ብር ይመነዘራል። በአንድ ወር ውስጥ ብቻ ከነበረበት 29 ብር አካባቢ ወደ 32.22 ደርሷል፡፡ ይህም ማለት ወደ አስር ፐርሰንት አካባቢ ጨምሯል ማለት ነው፡፡ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ገበያው የመሪነቱን ሚና እየተጫወት መሄዱን እና የውጭ ምንዛሬ ገበያው ነጻ ለመሆን እየተንደረደረ ለመሆኑ አንዱ ማሳያ መንገድ ነው፡፡ በአንድ ወቅት ጎረቤት አገር ኬንያ ከፍተኛ የሆነ የዶላር እጥረት ሲያጋጥማት አንድ መላ ዘየደች። የዶላር ገበያውን ነጻ አደረገቸው፡፡ ወዲያው መንግሰት በገበያው ሃይል ላይ የተንተራሰ የውጭ ምንዛሬ ተመን መተገበር ጀመረ፡፡ በዚህ ጊዜ በመንግስት ጡንቻ ስር ሆነው ተፈላጊውን የዶላር ምንጭ ማምጣት ያልቻሉት የገበያ ትስስሮች ነጻ ሆነው በገበያው ላይ መሰረታቸውን ሲጥሉ ቀስ በቀስ በፍላጎቱና በአቅርቦት መካከል ሚዛን መፍጠር ጀመሩ፡፡ በአሁን ወቅት ለኬንያ ኢኮኖሚ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ተፈላጊውን ምርታማነት አያሳጣቸውም፡፡ እንደውም በባንክ ያለውና በጥቁር ገበያው ያለው የምንዛሬ ተመን ተመሳሳይ ነው፡፡ በተቃራኒው ኢትዮጵያ ላይ በውጭ ምንዛሬ እጥረት አያሌ ኢንቨስትመንቶች ሲቆሙና መጨረስ ባለባችው ሰዓት አልቀው ወደ ማምረት አግልገሎት እንዳይገቡ ጋሬጣ ሆኖባቸው ቆይቷል፡፡ በታቀደላቸው የጉዜ ሰሌዳ ስራ አጥነትን ይፈታሉ የተባሉ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች ሲባክኑ ይስተዋላል። እንደ አገር የግብርና ምርት ላይ እንደተመሰረተ ምጣኔ ሀብት የዶላር ተመን ጭማሬው እንደ አገር የወጪ ንግድ ገቢያውን፤ ብሎም የንግድ ሚዛኑንና ጠቅላላ የክፍያ ሚዛኑን ሊያንገዳግደው ይችላል። በመሆኑም ለጊዜውም ቢሆን የማክሮ ኢኮኖሞ ኢምባላንስ ሊፈጥር ይችላል። ይሁን እንጂ ችግሩ ጊዜአዊ ነው። መንግሰት ይህን የገበያ
Posted in Ethiopian News

ኢትዮጵያ የምታመጥቀው ሳተላይት ለሐሳቡ ጠንሳሽና የህዋ ሳይንስ ተመራማሪ በዶ/ር ለገሰ ወትሮ ስም እንድትሰየም ተጠየቀ

ኢትዮጵያ የምታመጥቀው ሳተላይት ሃሳብ ጠንሳሽ የነበሩትና የተረሱት የህዋ ሳይንስ ተመራማሪ በአርሲ ስሬ ወረዳ በ1942 ዓ.ም ነበር የተወለዱት ዶ/ር ለገሰ ወትሮ የመጀመሪያና የሁለተኛ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ከዚያም ከሼፊልድ ዩናይት በድጋሚ በፊዚክስ ሁለተኛ ዲግሪ ከከሎምቢያ ስቴት ዩንቨርሲቲ በአስትሮኖሚ/አስትሮፊዚክስ ደግሞ ሶስተኛ ዲግሪያቸውን ያገኙት ዶ/ር ለገሰ ወትሮ ወደሃገራቸው ተመልሰው ለ40 ዓመታት ያህል በመምህርነትና በተመራማሪነት በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ አገልግለዋል ኢትዮጵያዊው አስትሮ ፊዚስት ዶ/ር ለገሰ ወትሮ በሃገራችን ታሪክ ብቸኛው የህዋ ሳይንስ ተመራማሪ የነበሩ ሰው ናቸው ። ከሶስት አመታት በፊት ከዚህ አለም በሞት የተለዩት ዶ/ር ለገሰ ወትሮ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ መስራች የነበሩም ሰው ናቸው። በህዋው ሳይንስ ዘርፍ ለሃገራችን ቀዳሚ የነበሩት የኚህ ምሁር ባለቤት ዛሬ በታዲያስ አዲስ የራዲዮ ፕሮግራም ቀርበው ሲናገሩ እንደሰማናቸው, ባለቤታቸው ሃገራችን በህዋው ሳይንስ ዘርፍ ተሳታፊ እንድትሆን ሳተላይት የማምጠቁን ሃሳብ ቀድመው ያስጀመሩና ለተግባራዊነቱ እስከእለተ ሞታቸው ይሰሩ የነበሩ ሰው ቢሆኑም አርብ እለት ትመጥቃለች ተብሎ ከሚታሰበው ሳተላይት ጋር ተያይዞ ስማቸው ሲነሳ አለመስማታቸው ቅሬታን እንደፈጠረባቸው ተናግረው አርብ እለት የምትመጥቀው ሳተላይት በባለቤታቸው ስም እንዲሰይምላቸው ጠይቀዋል ።  በዚሁ ፕሮግራም ላይ ቀርባ ቅሬታዋን የገለፀችው የዶ/ር ለገሰ ወትሮ የ11 አመት ልጅም እንደተናገረችው ሃገራችን በህዋው ሳይንስ ቴክኖሎጂ የራሷ የሆነ ሳተላይት እንዲኖራት ሲደክሙ ዘመናቸውን ያሳለፉት የአባቷ ስም መረሳቱ እንዳስከፋት ገልፃ ዶክተር አብይ ቢቻል የሳተላይቷን ስም በአባቷ ስም እንዲሰየም እንዲያደርጉላት ይህ ባይሆን እንኳን ለፈር ቀዳጁ ተመራማሪ አባቷ በይፋ እውቅና እንዲሰጡላት ጠይቃለች። እኛም የኋላው ከሌለ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አቶ ለማ መገርሳ በፓርቲዎች ውህደት ላይ ተቃውሞ እንዳላቸው አስታወቁ።

አቶ ለማ መገርሳ በፓርቲዎች ውህደት ላይ ተቃውሞ እንዳላቸው አስታወቁ። ” መዋሀዱን አልደግፍም : ከመጀመሪያ ጀምሬ ተቃውሜያለሁ ። በስብሰባው ብገኝም ፈፅሞ አልደገፍኩም! መደመር የሚባል ፍልስፍናም አይገባኝም! ” አቶ ለማ መገርሣ ለVOA ከተናገሩት የኢፌዲሪ መከላከያ ሚንስትር እና የኦዲፒ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ለማ መገርሳ መደመርን በሚለው መርህ እንደማይስማሙ እና በፓርቲዎች ውህደት ላይ ተቃውሞ እንዳላቸው አስታወቁ። አቶ ለማ ለአሜሪካ ድምጽ እንደተናገሩት በፓርቲዎች ውህደት ላይ ያላቸውን ቅሬታ ለኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ማስታወቃቸውን ገልፀው ውህደትም መሆን ካለበት እንዲህ በችኮላ መሆን እንደሌለበት ግልጽ አድርገው ተናግረዋል።አቶ ለማ መገርሳ የኢህአዴግ ምክር ቤት የፓርቲዎችን ውህደት ባፀደቀ ጊዜ የምክር ቤት ስብሰባ ላይ ተገኝተው እንደነበር ገለፀው ስለሂደቱ ግን አሁን ማብራራት አልፈልግም ብለዋል፡፡ አቶ ለማ መደመርን የተቃወሙበትን ምክንያት እንደዚህ ያስረዳሉ፡
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የምግብ መመረዝ አልተከሰተም – ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ

Image may contain: 6 people, people smiling, people standing and suit የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በፍሬህወት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል።ኢንጂነር ታከለ በስፍራው የተገኙት በትናንትናው እለት በተማሪዎች ላይ የማስመለስና የሳል ምልክት ታይቷል መባሉን ተከትሎ ነው። በምልከታቸውም የሆስፒታል የምርመራ ውጤትን ጠቅሰው በተማሪዎች ላይ ከምግብ ጋር የተያያዘ ችግር አለመከሰቱን አስታውቀዋል።የምግብ መመረዝ አለመከሰቱን ያነሱት ከንቲባው በትምህርት ቤቶች የሚደረገው የምገባ ፕሮግራም በተጠናከረና ተቋማዊ በሆነ መልኩ ይቀጥላል ብለዋል። አያይዘውም ፕሮግራሙ በሕግ ደረጃ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አዋጅ ሆኖ ይፀድቃል ማለታቸውን ከምክትል ከንቲባው የፌስ ቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። ዛሬ ጠዋት በፍሬህወት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ላይ ደረሰ የተባለውን ሁኔታ ተመልክቻለው። ከምግብ ጋር የተያያዘ ችግር የለም። የሆስፒታል ምርመራ ውጤቱም የሚያሳየው እውነት የምግብ መመረዝ አይደለም። ለማንኛውም የምገባ ፕሮግራም በተጠናከረና ተቋማዊ በሆነ መልኩ ይቀጥላል:: በሕግ ደረጃም በከተማችን ምክር ቤት አዋጅ ሆኖ ይፀድቃል። ተማሪዎች እና ቤተሰቦች፤ ከተማ አስተዳደራችን የትምህርትን ሥራ አንዱ እና ቁልፍ የልማት ሥራችን እንደሆነ እንደገና እርግጠኛ ሆኜ አረጋግጥላችኋለሁ። Source – Takele Uma Banti Image may contain: 5 people, people smiling, people standing
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በአሜሪካ ብሄራዊ የፕሬስ ክለብ ንግግር እንዲያደርግ ተጋበዘ።

Ethiopian Journalist To Discuss Press Freedom ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በአሜሪካ ብሄራዊ የፕሬስ ክለብ ንግግር እንዲያደርግ ተጋበዘ። ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በኢትዮጵያ እና በዓለም ስላለው የፕሬስ ነጻነት ዙሪያ ንግግር እንዲያደርግ ለዲሴምበር 9/2019 ቀጠሮ ተይዞለታል። https://pbs.twimg.com/media/DgFLuZfXkAAV8xY?format=jpg&name=small Eskinder Nega, an Ethiopian journalist who has been imprisoned repeatedly for his reporting, will talk about press freedom in his country and around the world at the National Press Club on Dec. 9. The event is jointly sponsored by the club and its nonprofit journalism institute. ተጨማሪ መረጃ ፦ https://www.press.org/newsroom/ethiopian-journalist-discuss-press-freedom
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አዲስ አበባ ላይ ባልደራሱ የቀድሞውን ቅንጅት ይተካ ይሆን ???

አዲስ አበባ ላይ ባልደራሱ የቀድሞውን ቅንጅት ይተካ ይሆን ??? ( ምንሊክ ሳልሳዊ ) ራሱን ባለአደራ ቦርድ ብሎ የሚጠራው ስብስብ ወደ ፖለቲካ ድርጅትነት እንዲቀየር የዲያስፖራው ጫና መጀመሩን ሰምተናል። ዲሲ የሚገኘው የአንድነት ኃይሉ የፖለቲካ ተፅእኖ በመፍጠር ደረጃ የተሳካለት ስብስብ ነው። ወደ ፖለቲካው አለም ከመጣ እስክንድር ነጋ አዲስ አበቤውን፣ የዲያስፖራውን ኃይል ይዞ ከኢዜማ ጋር አዲስ አበባን ሊቆጣጠር ይችላል። እንደኔ ከፖለቲከኝነት ይልቅ ባልደራሱ በሲቪክ ማሕበርነት ራሱን ቢያሳድግ ለጨቋኞች ትልቅ አደጋ ቢሆን የተመረጠ ይሆናል። ምርጫውን ከገዢው ፓርቲ ውጪ ኃይሎች ሊያሸንፉ ይችላሉ በሚል የ አዲስ አበባ ከተማ ጥቅሞችና አስፈላጊ ገቢዎች ወደ ፌዴራሉና ኦሮሚያ ክልል እየዞሩ ነው። ይህ ሕወሓት በዘጠና ሰባት ምርጫ የወሰደው የድንጋጤ እርምጃ ነበር፤ አሁን እየተደገመ ነው። ገዢው ፓርቲ ከልብ መደናበሩንና መደንገጡን እያየን ነው። የባልደራሱም እርምጃ ፈርና ሕግን የተከተለ በመኦኑ አሸናፊነቱን ከጅምሩ ያረጋገጠበት ነው። በአንድ ብሔር አቀንቃኝነትና በኃይማኖት ጉዳዮች ባልደራሱ በጽንፈኛ ብሔርተኞች በፈጠራ ስሙ እንዳይጠፋ ጠንካራ ስራዎች ሊሰራ ይገባል። ቀደም ባሉ ጊዜያት የፖለቲካ ፓርቲዎችን ሲበጠብጡ፣ ሲያፈርሱና ሲያስደንሱ የነበሩ የደሕንነት ቅጥረኞችን ከመሐሉ ጎትቶ አውጥቶ ቢያስወግድ የተሻለ ነው። ( ምንሊክ ሳልሳዊ )
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሲዳማ : ኢሕአዴግ ነሳ ፤ ኢሕአዴግ ሰጠ ፤ የኢሕአዴግ ስም የተባረከ ይሁን !

ኢሕአዴግ ነሳ ፤ ኢሕአዴግ ሰጠ ፤ የኢሕአዴግ ስም የተባረከ ይሁን ! (ምንሊክ ሳልሳዊ) የሲዳማ ክልልነት እንደ አዲስ ነገር ሲራገብ ማየት ይገርማል። በተለይ የኦሮሞ ጽንፈኞችና የሕወሓት ካድሬዎች ወንጀላቸውን ለመደበቅ ይመስል ግንባር ቀደም አጨብጫቢዎች ሆነዋል።ታሪክን ለምናውቅ ክልልነት ለሲዳማ ሲያንሰው ነው። ከክልልነት በላይም ጠቅላይ ግዛት የነበረ ነው። ትላንት መብቱን የገፈፉት አካላት ዛሬ ላይ ዋና የደስታ አራጋቢ ሆነው ማየት ግርምትን ይፈጥራል። ሲዳማ ሰፊ ክፍለ ሐገር ነበር ፤ ኢሕአዴግ መጣና ዞን አደረገው ፤ ቆራርሶም ለኦሮሚያ ክልል ሰጠው ፤ ከሻሸመኔ እስከ ዋደራ ሲዳማ በዙሪያው ተቆራርሶ በመለስ ዜናዊ ቡራኬ ለኦሮሚያ ክልልነት ተሰጠ። ሕወሓቶች ላለፉት ሐያ አመታት የሲዳማን ክልልነት ጥያቄ አፍነው ዛሬ ከአራት ኪሎ ከተባረሩ በኋላ ሲዳማ ክልል ሲሆን ያለነሱ ቀዋጭ ጠፋ። ሕወሓት በስልጣን ዘመኑ ስለክልልነት ሲነሳ የሲዳማን ሕዝብ እኮ ሲገርፍና ሲያሳድድ ነበር። የኦሮሞ ጽንፈኞችም ቢሆኑ የሲዳማን ሕዝብ ለራሳቸው የነገ ፖለቲካ ፍጆታ መጠቀሚያ ለማድረግ ፍላጎት ስላደረባቸው እያጨበጨቡ ነው። አልገባቸውም እንጂ ነገ ላይ የወሰን ጥያቄዎች ለከፍተኛ ደም መፋሰስ ይዳርጋሉ። የኦሮሚያ ክልል የመጀመሪያው አጨብጫቢ ቢሆንም ነገ ለሚነሳው ችግር ግን መልስ ለመስጠት እንደማይችል ያሳብቅበታል። ፖለቲካው በደንብ ይታወቃል ጽንፈኛ የኦሮሞ ብሔርተኞች እያጨበጨቡ ያሉት ለነገ የሲዳማ ጥያቄዎች እንዳይነሱ ቀብድ መሆኑ ነው። በሲዳማና በኦሮሚያ ክልሎች መካከል ሰፊና የማይበርድ የወሰን ግጭቶች መነሳታቸው ውሎ አድሮ እናየዋለን።መንግስት ባልተጠና ፖሊሲ ወደ ፖለቲካ ኪሳራ ሲገባ በተደጋጋሚ እየተመለከትን ነው። ሲዳማዎች የመብትና የወሰን ጥያቄ እንዳያነሱ ከፍተኛ የሆነ ብጥብጥና ግጭት በ አዲሱ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በአርባምንጭ የመከላከያ ሰራዊት ያሰረውን አክቲቪስት ሊፈታው እና በከተማዋ ወጣቶች ላይ የሚያደርሰውን ወከባ እና ሕገወጥነት ሊያቆም ይገባል።

በአርባምንጭ የመከላከያ ሰራዊት ያሰረውን አክቲቪስት ሊፈታው እና በከተማዋ ወጣቶች ላይ የሚያደርሰውን ወከባ እና ሕገወጥነት ሊያቆም ይገባል። ፍትህ ለዳዊት ዋሲሁን !!! ዳዊት ዋሲሁን ካሳ በመከላከያ ሰራዊት አባላት በጥይት ስለተመታ ወጣት በገፁ ላይ አስፍሯል ይህን በፃፈ ማግስት ከጥዋቱ 4:00 አካባቢ በመከላከያ ሰራዊት አባላት ታስሯል። የዳዊትን መታሰር ስዩም ተሾመ በሰማ ሰዓት ወደዞን አስተዳደሪ አቶ ብራሃኑ ዘውዴ ጋ በመደወል የተፈጠረው ነገር ጠየኩት ማታ ከፃፈው ፁሁፍ ጋር በተያያዘ እንደያዙት እና ለፃፈው ፁፈም ይቅርታ ጠይቆ ፁፉንም አስተካክሎ ተግባብተው እንደተለቀቀ ተነገረኝ። ዳዊት የፃፈውን ፁሁፈ እውነታ ለማጣራት በጥይት ተመታ ወደተባለው ወጣት አርባምንጭ ሆስፒታል አመራው በጥይት የተመታውም ወጣት ዳዊት የፃፈውን ፁሁፍ እውነት እንደሆነ አረጋገጠልኝ ወጣቱን በጥይት የመቱት የከተማ ፖሊስ ወይንም ልዩ ሀይል ሳይሆን የመከላከያ ሰራዊት አባላት እንደሆኑ ነገረኝ የራጅ ውጤቱም በጥይት ስለመመታቱ ያረጋግጣል ይህንን መረጃ ሁሉ በቪዲኦ ቀረፅኩት ለማስረጃነት ይሆን ዘንድ ከታች አስቀምጨዋለው። በተጨማሪ በዳዊት ገፅ ላይ የሰፈረው የማስተካከያ ፁፍ በዳዊት እንዳልተፃፈ እንዲሁም ስልኩን ወስደውበት የFB password አስገድደው በመውስድ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እንደፃፉት ለማወቅ ችያለዉ። ታድያ ለምን የመከላከያ ሰራዊት ዳዊትን ሊያስር ቻለ እንደ እኔ እይታ ከሆነ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ዳዊትን ሊያስር የቻለው በሰራዊቱ አባላት የተፈጠረውን ስህተት ለመሸፈን እና እራሱን ከተጠያቂነት ለማዳን ነው። ዳዊት እስካሁን ታስሮ ነው ያለው ከቤተሰቡ ወጪ ማንም እንዳያገኘው ተከልክሏል ምግብም በሰአቱ እያደኘ አይደለም። ከታሰረ 24 ሰዓት ያለፈው ሲሆን እስካሁን ፈርድ ቤት አልቀረበም ወደ ጣብያም አልተወሰደም ህግ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በአዋሽ ከተማ የመከላከያ ጦር መኪኖች ተቃጥለዋል- የአዋሽ አዲስ አበባ መንገድ ተዘግተዋል።

Image may contain: sky and outdoorበአፋር መከላከያ ዜጎችን መግደሉን እንደቀጠለ ነው! ዛሬ በአፋር ክልል በዞን ሶስት ብሬጌድ ላይ የሚገኘው መከላከያ ንፁሃን የአፋር ወጣቶችን ገድለዋል። በአፋጣኝ ገዳዮች ለህግ ልቀርቡ ይገባል። አካባቢው ከኮንትባንዲስቶች አሁንም አልጠራም።ብርጌድ ጣቢያ ደግሞ የጦር ሐይል ዋና የኮንትሮባንድ ምሽግ ነው። መንግስት ይህን ሐይል ከቦታው ልያነሳ ይገባል። የትናንቱ የመከላከያ ጦስ በዛሬው እለት በአፋር አዋሽ ለዚህ ችግር ተጠያቂው ራሱ የብርጌድ መከላከያ ሠራዊት ነው። በአደባባይ ትናንት ወጣቶች በጥይት እሩምታ ረፍርፎ በመግደሉ በዛሬ በአዋሽ ከተማ የመከላከያ ጦር መኪኖች ተቃጥለዋል። ስለሟች ዜጎች ገዳዪች ላይ የተወሰደ እርምጃ ባለመኖሩ ምክንያት የአዋሽ አዲስ አበባ መንገድ ተዘግተዋል። አዋሽ በሐዘንም በእሳትም እየተቃጠለች ነው።አሁንም ሌላ ጥፋት ከማድረሱ በፊት ታዳጊ ወጣቶችን የገደሉ የመከላከያ ሠራዊት አባላት በህግ ይቅረቡ! የክልሉ መንግስት አፋጣኝ የሠላም መረጋጋት ሥራ መስራት አለበት። Image may contain: fire, outdoor and food በአፋር ብርጌድ በሚገኘው አጥፊ መከላከያ ጦር የተገደለው ወንድማችን ሁሴን አባህአባ አላህ ይዘንለት። ለቤተሰቡ መፅናናትን ተመኘሁ። በአፋጣኝ በወጣቶቹን የገደሉ የጦር አባላትን በህግ ይጠየቁ። በቀጠናው የኮንትሮባንድ ንግድ ተሰማርተው የነበረው ጦር ስቀየር አሁን የብርጌዱ ክፍለጦር ቀርተዋል። በአስቸኳይ ክልሉ ይህ ጦር ከቦታው እንዲቀየር የማድረጉ ሥራ መስራት አለበት። ዳግም ዜጎች በመከላከያ ጥይት እንዳይሞቱ ሐላፊነቱን ልወጣ ይገባል። በወንድሞቻችን ሞት በእጁ አዝኛለሁ። ሐዘናችሁ ሐዘናችን ነውና ለመላው ቤተሰቡ ሶብሩን ይስጣችሁ። የተሻለም ይተካላችሁ ብያላው። አሎ ያዮ – Allo Yayo Abu Hisham Image may contain: one or more people and outdoor Image may contain: fire, car and outdoor
Posted in Amharic News, Ethiopian News

መፈንቅለ መንግስት -> ጥቃት -> ግጭት -> ህገ መንግስትን በኃይል መናድ ->… ነገ ደግሞ ክሱ ይቀየር አይቀየር አናውቅም።

መፈንቅለ መንግስት -> ጥቃት -> ግጭት -> ህገ መንግስትን በኃይል መናድ ->… ነገ ደግሞ ክሱ ይቀየር አይቀየር አናውቅም። የክስ አክሮባት ……… በሕወሓት ከሚቀናበሩ ክሶች ነጻ ወጣን ስንል በኦሕዴድና ብአዴን ወደ ሚቀናበሩ የሐሰት ክሶች ዘልቀን ገብተናል። እጅግ በጣም የሚያስቀይመው ነገር ቢኖር ንጹሃን ባልዋሉበት ወንጀል የሚለቅመው መንግስት ድንቁርና ነው። ወንጀለኛ ተብለው የተፈረጁ ዋስትና በሚያስከለክል በከባድ የሕግ አንቀጽ ተከሳቹሃል የተባሉ በቀበሌ መታወቂያ ዋስ መለቀቃቸው የመንግስትን ስም አጥፊነትና ዋሾነት በገሃድ ያሳየ ነው። ኢሕአዴግ በራሱ የውስጥ ሽኩቻ የበላቸውን አመራሮቹንና የጦር ጄኔራሎቹን በተቃዋሚዎቹና በንፁሃን ላይ ማላከኩ ልማዱ ነው። ያላሸበሩትን አሸበሩ ብሎ መክሰስ ለኢሕአዴግ አዲስ አይደለም። ሕገ መንግስት ተናደ ብሎ መወንጀልም ለኢሕአዴግ የተለመደ የስም ማጥፊያው ስልቱ ነው። በባህርዳርና አዲስ አበባ ከአማራ ክልል አመራሮችና ከእነ ጀኔራል ሰዓረ መኮንን ግድያ ጋር በተያያዘ በወንጀል ድርጊቱ “እጃቸው አለበት” በሚል የተጠረጠሩ 13 ግለሰቦች ክስ ተመሰረተባቸው። የጀኔራል ሰዓረ ጥበቃ የነበረው አስር አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ፣ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ /አብን/ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ክርስቲያን ታደለን ጨምሮ 13ቱም ተከሳሾች በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበው ክሱ ተነቦላቸዋል። https://mereja.com/amharic/v2/172566 ዓቃቤ ህግ በተከሳሾቹ ላይ “ህገ መንግስትን በኃይል ለመናድ ተንቀሳቅሰዋል” በሚል ክስ መስርቶባቸዋል። እጅግ አሳዛኝና አሳፋሪ ሲሆን በ አደባባይ ዜጎችን የገደሉና ያስገሉ በነጻነት እየዞሩ ሕጋዊ የሆኑ የፖለቲካ እና የጦር ሰዎችን ሰብስቦ ማሰር የሕግ የበላይነትን ይደፈጥጣል።#MinilikSalsawi
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በፖለቲካ ውሳኔ ክልልነቱ የተረጋገጠውና ለይስሙላ ድምጽ የሚሰጥበት በመንግስት ጥፋት የሕዝብ ገንዘብ የባከነበት የሲዳማው ሪፍረንደም

(ምንሊክ ሳልሳዊ) – በፖለቲካ ውሳኔ ክልልነቱ የተረጋገጠውና ለይስሙላ ድምጽ የሚሰጥበት በመንግስት ጥፋት የሕዝብ ገንዘብ የባከነበት የሲዳማው ሪፍረንደም – ድምፅ የሚሰጠዉ ሕዝብ ከምንም በላይ ሰላሙ እንዳይታጎል አበክሮ እየተማፀነ ነዉ። ሲዳማ ጠቅላይ ግዛት ነው፤ ሲዳማ ክፍለ ሃገርም ነው፤ ሲዳማ ትልቅ ሕዝብ ነው፤ ሲዳማ በጠባብነት ብልቃጥ ውስጥ የማትከተው ኢትዮጵያዊ ሕዝብ ነው፤ እንደዛሬው በገዢዎቹ ሳይቆራረስ ሲዳማ ትልቅ አገር ነበር፤ ስለ ሲዳማ ብዙ ብዙ ማለት ይቻላል። ካለሪፍረንደም ክልል ማድረግ እየተቻለ ፤ ካለሪፍረንደም ራሱን እንዲያስተዳድር ማድረግ እየተቻለ፤ ብዙ ብዙ ነገር ማድረግ እየተቻለ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ አውጥቶ ሪፍረንደም ማካሔድ መንግስት ምን ያህል የፖለቲካ ድድብና እንደተጠናወተው ያሳያል። ባለፈው ጊዜ የተከሰተው ግጭትም የመንግስት ንዝሕላልነት ውጤት ነው።በቀላሉ ሊፈቱ የሚችሉ ጉዳዮችን አስፍቶ በማስኬድ ግጭት መፍጠር የመንግስት አካሔድ መሆኑ በየክልሉ እያየን ነው። ለሪፍረንደም የወጣው ገንዘብ ለሲዳማ ሕዝብ ሆስፒታል፣ ትምሕርት ቤት አሊያም ሌላ ተመራጭ የሆነ የልማት ተቋም ይገነባል። ይህ ለሪፍረንደም የወጣው ገንዘብ ስራ አጥ ወጣቶችን ወደ ስራ ለማስገባት ይችላል። ሕዝቡ በራሱ ክልልነቱን ካረጋገጠ ቆይቷል፤ ይህንን መንግስትም እያወቀ ሪፍረንደም ማድረጉ ከብክነት ውጪ ምንም አይፈይድም። የሕዝብ ገንዘብ የባከነበት የሲዳማው ሪፍረንደም ዞሮ ዞሮ ውጤቱ የሲዳማ ክልልነትን አያስቀረውም። መንግስት ባልተጠና ፖሊሲ ወደ ፖለቲካ ኪሳራ ሲገባ በተደጋጋሚ እየተመለከትን ነው።ድምፅ የሚሰጠዉ ሕዝብ ከምንም በላይ ሰላሙ እንዳይታጎል አበክሮ እየተማፀነ ነዉ። #MinilikSalsawi
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኢትዮጵያ 4 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ የጦር ጄቶች ሂሊኮፕተሮች ፣ ድሮኖችና የኒውክሊየር አረር መሸከም የሚችሉ ሚሳኤሎችን ከፈረንሳይ በብድር ለመግዛት ጥያቄ አቀረበች

Le point የተባለ የፈረንሳይ ታዋቂ የዜና ማእከል ዶ/ር አብይ አህመድ በሐምሌ 15 እ.ኤ.አ ከፈረንሳይ ሀገር የ $4 ቢልዮን ዶላር ጦር መሳርያ ግዢ ትዕዛዝ ሰነድ ይፋ አድርገዋል።(ሰነዱን ከታች ያገኙታል) ጠቅላይ ሚኒስተሩ 12 ራፋልና ሚራዥ የሚባሉ የጦር ጀቶች ፣ 18 ዘመናዊ ሄለኮፕተር ፣ 2 አንቶኖቮች ፣ 10 ድሮን ፣ 1ራዳር ፣ 30 M51 የተባሉ 6000ኪ.ሜ መምዘግዘግ ሚችሉ ኒውክሌር አረር ተሸካሚ ሚሳኤሎች እና 10 UAVs electronics Jaming የራድዮ ሞገድ መጥለፊያ device የያዘ ዝርዘር ሰነድ መሆኑን ታውቃል ። ይህን ተከትሎም ኢትዮጵያ በቀጣይ በአፍሪካ የዘመናዊና በቴክኖሎጂ የታገዘ ጦር ይኖራታል ማለት ነው። ኢትዮጵያ የፈረንሳይ ስሪት የሆኑ ተዋጊ ጀቶች፣ ሄሊኮፕተሮች፣ ድሮኖች እንዲሁም የኒውክሊየር አረር መሸከም የሚችሉ ሚሳኤሎችን ለማግኘት ፕሬዝደንት ማክሮንን እንደጠየቀች አንድ የፈረንሳይ ሚድያ ዘግቧል! Le Point የተባለው ሚድያ ባወጣው ዘገባ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ጥያቄውን ለፈረንሳዩ መሪ ያቀረቡት ሀምሌ 15 ቀን ሲሆን ዋናው አላማም “የኢትዮጵያን አየር ሀይል ለማዘመን” ታስቦ ነው። ሶስት ገፅ ባለው የጥያቄው ዶክመንት መሰረትም ኢትዮጵያ ከፈረንሳይ በብድር ለማግኘት ጥያቄ ያቀረበችው 12 ተዋጊ ጀቶች (ራፋሌ እና ሚራዥ የተባሉ)፣ 18 ሄሊኮፕተሮች፣ የኤርባስ ምርት የሆኑ ሁለት የጦር ማጓጓዣ አውሮፕላኖች፣ አስር ድሮኖች፣ ኤሌክትሮኒክ የሬድዮ ሞገድ መዝጊያ መሳርያ እና የኒውክሊየር አረር መሸከም የሚችሉ ሰላሳ M51 ሚሳኤሎችን ነው ተብሏል። እነዚህ ሚሳኤሎች ስድስት ሺህ ኪ/ሜ መጓዝ የሚችሉ ናቸው የተባለ ሲሆን የዚህ ሚሳኤል ግዥ ላይፈፀም ይችላል የሚል ግምት አለ። ምክንያቱ ደግሞ ሁለቱ ሀገራት
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ዛሬ ባደረገው ስብሰባ የኢህአዴግን ውህደት በአብላጫ ድምፅ አፀደቀ።

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ዛሬ ባደረገው ስብሰባ የኢህአዴግን ውህደት በአብላጫ ድምፅ ፣ በ 6 ተቃውሞ አፀደቀ። የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በአብላጫ ድምፅ ሪፎርሙን ተቀብሏል። ለዉጡም ከግማሽ መንገድ በላይ ሄዷል :: የኢህአዴግ ውህደት በሦስቱ አባል ድርጅቶች ድጋፍና በህወሓት ተቃውሞ ፀድቋል። በእርግጥ ህወሓት ውህደቱን ሙሉ ለሙሉ አልተቃወመም። ከዚያ ይልቅ ውህደቱን አስመልክቶ ከማዕከላዊ ኮሚቴ ጋር ተመካክሮ እንደሚወስን በመግለፅ ተጨማሪ ቀናት እንዲሰጡት ጠይቋል። በዚህ መሠረት የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ለህወሓት የ3 ቀናት ግዜ ገደብ ሰጥቶታል። በውህደቱ ላይ የተስማሙት አባልና አጋር ድርጅቶች ግን ከነገ ጀምሮ በአዲሱ ፓርቲ ፕሮግራም ላይ መወያየት ይጀምራሉ። #MinilikSalsawi —————————————————————————————————————- ETV NEWS : የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በቀረበለት የውህደት ዝርዝር ጥናት ላይ ተወያይቶ በአብላጭ ድምፅ ከስምምነት መድረሱን አስታወቀ:: ኮሚቴው በውህደቱ ማዕቀፍ ውሰጥ ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገቡ ዋና ዋና ጉዳዮችን በስፋት እንስቶ መወያየየቱንም የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ ፍቃዱ ተሰማ በተለይ ለኢትቪ ተናግረዋል:: በዚህም ህብረ ብሔራዊ ፌደራሊዝም ተጠናክሮ በሚቀጥልበትና የራስ አስተዳደር በሚጎለብትበት ሁኔታ ላይ ኮሚቴው በዛሬው ስብሰባው ትኩረት ሰጥቶ በዝርዝር መወያየቱንም ገልፀዋል:: የቋንቋ ብዝሃነት ፣ የብሔር እና ሀገራዊ ማንነትን ሚዛኑን በጠበቀ መልክ እንዲጠናከር የሚሉት ጉዳዮችም በመድረኩ ላይ ምክክር ተደርጎባቸዋል ብለዋል አቶ ፍቃዱ:: በመጨረሻም የውህደቱን ጥናት ኮሚቴው በ6 ተቃውሞ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል:: በነገው ዕለትም ለወደ ፊቱ ውህድ ፓርቲ በተቀረፀው ረቂቅ ፕሮግራም ላይ እንደሚወያይ አቶ ፍቃድ ተሰማ ለኢቲቪ ተናግረዋል::
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ለሐገር ሰላም እያንዳንዳችን የዜግነት ግዴታችንን ልንወጣ ይገባል።

(ምንሊክ ሳልሳዊ) ለሐገር ሰላም እያንዳንዳችን የዜግነት ግዴታችንን ልንወጣ ይገባል። ሰላም ካለ ፍትሕ አለ። ሰላም ካለ የመኖርና የመስራት ሕልውና አለ። ሰላም ካለ አንድነትና መከባበር አለ። ሰላም ካለ የምንፈልገው ነገር ሁሉ አለ። ሰይጣን ካልሆነ በስተቀር ማንም ሰላምን አይጠላም።ሰላም የሁሉም ጉዳይ ነው።ህግ የማስከበሩና ስርዓት አልበኝነትን በማስቆም ሰላምን የማስፈኑ ጉዳይ የሁላችንም ነው። ሰላማችንን እየነሳን የሚገኘው የፖለቲከኞች እኩይ ምግባርና የሴራ ፖለቲካቸው ነው። በሕዝብ መሐል ቁርሾ የሚፈጥሩት በግል ጥቅም አይናቸው የታወረና በዘር ፖለቲካ መክበር የሚፈልጉ አካላት ናቸው። ሕዝብ ላለፉት አመታቶች ተከባብሮና ተፈቃቅሮ ኖሯል። ይህ የሕዝብ ሰላም መደፍረስ ፖለቲከኞችና ተከታዮቻቸው የሚፈጥሩት መድረክ እስከዛሬ ታይቶ ምንም ለውጥ አላመጣም። ይብሱኑ የመንግስት አካላት የሰላም መድረክ ባሉ ማግስት ከፍተኛ እልቂት መከሰት የተለመደ ነገር ሆኗል። ሰላምና ነጻነት ያለው በሕዝብ እጅ ነው። ፖለቲከኞች በሕዝብ እጅ ያለውን ነጻነትና ሰላም ለመንጠቅ የሚጠቀሙበት መንገድ ሁሉ ለሰቆቃና ለሽብር ዳርጎናል።ፖለቲከኞች ስልጣናቸውንና ጥቅማቸውን ላለማጣት የሚሔዱበት መንገድ በሕዝብ ላይ አደጋ እያስከተለ ነው። ስለዚህ ሕዝቡ ሰላሙንና ነጻነቱን ከፈለገ የፖለቲከኞችን ወከባ ወደ ጎን በመተው በለመደው የባሕሉና የመከባበር ዘዴው ተጠቅሞ ሰላሙን የማስከበር ግዴታ አለበት።ከአሁን በፊት ችግሮች ሲያጋጥሙ በእርቅና በሌሎች መንገዶች ይፈታ የነበረው ህዝብ ጥፋቶች ሲፈፀሙ በዝምታ ከማለፍ ይልቅ ሊያስቆም፣ ዝምታውን ሊሰብር ይገባል። ወጣቶች፣ አክቲቪስቶችና ምሁራን ቆም ብለዉ ሊያስቡ እንደሚገባና መንግስትም ነፃነቱን ከሰጣቸው አካላት ጋር ተመካክሮ ሊሰራ ይገባል። መንግስት ሕግና ስርዓትን ማስፈን ከቻለና ጠንካራ የሰላም መፍትሔ እርምጃዎችን በሰላም አደፍራሾች ላይ ከወሰደ ሕብረተሰቡ ሰላሙን ላለመነጠቅ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ወላጆች ፈርመውበታል በዩንቨርስቲዎች አስተማማኝ ሰላም ለማስፈን በቂ ነው የተባለለት የከፍተኛ ትምሕርት ተቋማትና የተማሪዎች ውል ምን ዋጠው???

አፈጻጸም ላይ ሿ ሿ !! ተገኖ የተወራለት የሳይንስና ከፍተኛ ትምሕርት ሚኒስቴር የተማሪዎችና የወላጆች ፊርማ የሰፈረበት ውል የት ገባ ???   ወላጆች ፈርመውበታል በዩንቨርስቲዎች አስተማማኝ ሰላም ለማስፈን በቂ ነው የተባለለት የከፍተኛ ትምሕርት ተቋማትና የተማሪዎች ውል ምን ዋጠው??? የተዘጋጀው ለፕሮፓጋንዳ ነው ወይንስ ተማሪውን ለማስፈራራት ብቻ ??? በቂ አጥኚና መፍትሔ የሚያስቀምጡ ኤክስፐርቶች የሌሉት መንግስት የሕዝብን ሃብት ከማባከን ውጪ አንድም የረባ ስራ መስራት አልቻለም። ፊርማው ሳይደርቅ ዩንቨርስቲዎች አኬልዳማ ሆነዋል።   መጀመሪያ የአስተሳሰብ ልህቀት ላይ አልተሰራም። በመቀጠል ተማሪዎችን ወዳልተፈለገ ነገር የሚመሩ ነገሮች በመለየት የማስተካከያ እርምጃ  አልተወሰደም። የመንግስት በጀት በሰላም ኮንፈረንስና በስብሰባ ባክኗል።ተጠያቂነትንና ሐላፊነትን በሕግ የበላይነት አጣምሮ ያላሰፈነ መንግስት ከኪሳራ ውጪ ምንም አይፈይድም።   ተማሪዎችን በጥሩ ስነ ምግባር አንፀው ያላሳደጉ የሁለተኛ ደረጃ መምሕራንም ለዚህ ግጭት የራሳቸው ድርሻና ተጠያቂነት አለባቸው። ወላጆችም ልጆቻቸውን የመሩበት የ አስተዳደግ ዘይቤ ራሱን የቻለ ተፅእኖ ፈጥሯል። መንግስት በተለይ በፖለቲካው መስክ የሚከተለው አሻጥርና ሕገወጥ የፖለቲካ አካሔድ ከባድ አደጋን ከፊታችን ደቅኗል። በነዚህና በመንግስት ስንፍና ሕጎችና ደንቦች መመሪያዎች በተግባር ሊተረጎሙ ባለመቻላቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤሩም ያዘጋጀው ውል ሿ ሿ ተሰርቷል። #MinilikSalsawi
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ግብጽ በዲፕሎማሲው መስክ የምታደርገው ግፊት አሸናፊነት የሕዳሴውን ግድብ ገደል እንዳይከተው ያሰጋል።

ግብጽ በዲፕሎማሲው መስክ የምታደርገው ግፊት አሸናፊነት የሕዳሴውን ግድብ ገደል እንዳይከተው ያሰጋል። በዋሽንግተን የተደረገው የሕዳሴውን ግድብ የተመለከተው ድርድር እና መግለጫ የሚያመላክተው ነገር ቢኖር ግብጻ በዲፕሎማሲውና በፖለቲካው ረገድ አለም አቀፍ ጫና እና ተሰሚነቷን ነው። መጀመሪያ ይህ ስብሰባ በአንድ የኃያላን አገር ፕሬዝዳንት አትኩሮት አግኝቶ ዲሲ ላይ ድርድር እንዲደረግና መግለጫ እንዲወጣ የዲፕሎማሲውን ስራ እንዲሰራ ያደረገችው ግብፅ ናት።በዚህ ድርድር ላይ ለወደፊቱ በሚደረጉ ውይይቶች ድርድሮችና ንግ ግሮች ላይ ጫና ሊያሳድሩ የሚችሉ አሜሪካና ዓለም ባንክን የመሳሰሉ ሶስተኛ ወገኖች በግብጽ ጫናና ፍላጎት በታዛቢነት መመረጣቸው ለኢትዮጵያ ጥንካሬ ትልቅ አደጋ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል። ሁለተኛ ደረጃ ግብጽ የቀደሙትንና በኢትዮጵያ ተቀባይነት ያጡትን ስምምነቶች ተግባራዊ እንዲደረጉ ግፊት በማድረግ አሜሪካና ዓለም ባንክ ታዛቢ እንዲሆኑ ያደረገችው ጫና ተቀባይነት አግኝቷል። ኢትዮጵያ ማንም ሶስተኛ ወገን በ አደራዳሪነትም ሆነ በታዛቢነት አልቀበልም ያለችውን አቋሟን እንድትቀይር በግብጽ ግፊት አሜሪካ ጫና አሳድራለች። ትናንት ከተካሄደው መርሃ ግብር ቀደም ብሎ የግብጽ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ሳሚህ ሽኩሪ ከፕሬዝደንት ትራምፕ ከፍተኛ አማካሪ ጃሬድ ኩሽነር ጋር ውይይት ማድረጋቸውን የግብጽ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ቢሮ አስታውቋል። ግብፆች ብዙ ነገሮችን ጮክ አድርገው ቀውስ እንዳለ አድርገው ስለሚያወሩና ስለሚያስወሩ ወዳጅ አገሮች ይህ ያሳስባቸዋል።ይህ የሚያሳየው ምን ያሕል የዲፕሎማሲ ስራ በግብፅ መሰራቱን ነው። የኢትዮጵያ መንግስት በዲፕሎማሲው በኩል ከግብፅ የበለጠ ጉዳዩን በማጮህ ግብፆችን መቅበር እየቻለ የሔደበት አካሔድ ለሕዳሴ ግድቡ መሞት ትልቅ ስጋት ሆኗል። ካሁን በፊት ኢትዮጵያ አልስማማም እያለች የሔደችበት መንገድ በነትራምፕ ጫና የመስመር ለውጥ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በመንግስት ጥፋት የሕዝብ ገንዘብ የባከነበት የሲዳማው ሪፍረንደም

በመንግስት ጥፋት የሕዝብ ገንዘብ የባከነበት የሲዳማው ሪፍረንደም ሲዳማ ጠቅላይ ግዛት ነው፤ ሲዳማ ክፍለ ሃገርም ነው፤ ሲዳማ ትልቅ ሕዝብ ነው፤ ሲዳማ በጠባብነት ብልቃጥ ውስጥ የማትከተው ኢትዮጵያዊ ሕዝብ ነው፤ እንደዛሬው በገዢዎቹ ሳይቆራረስ ሲዳማ ትልቅ አገር ነበር፤ ስለ ሲዳማ ብዙ ብዙ ማለት ይቻላል። ካለሪፍረንደም ክልል ማድረግ እየተቻለ ፤ ካለሪፍረንደም ራሱን እንዲያስተዳድር ማድረግ እየተቻለ፤ ብዙ ብዙ ነገር ማድረግ እየተቻለ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ አውጥቶ ሪፍረንደም ማካሔድ መንግስት ምን ያህል የፖለቲካ ድድብና እንደተጠናወተው ያሳያል። ባለፈው ጊዜ የተከሰተው ግጭትም የመንግስት ንዝሕላልነት ውጤት ነው።በቀላሉ ሊፈቱ የሚችሉ ጉዳዮችን አስፍቶ በማስኬድ ግጭት መፍጠር የመንግስት አካሔድ መሆኑ በየክልሉ እያየን ነው። ለሪፍረንደም የወጣው ገንዘብ ለሲዳማ ሕዝብ ሆስፒታል፣ ትምሕርት ቤት አሊያም ሌላ ተመራጭ የሆነ የልማት ተቋም ይገነባል። ይህ ለሪፍረንደም የወጣው ገንዘብ ስራ አጥ ወጣቶችን ወደ ስራ ለማስገባት ይችላል። ሕዝቡ በራሱ ክልልነቱን ካረጋገጠ ቆይቷል፤ ይህንን መንግስትም እያወቀ ሪፍረንደም ማድረጉ ከብክነት ውጪ ምንም አይፈይድም። የሕዝብ ገንዘብ የባከነበት የሲዳማው ሪፍረንደም ዞሮ ዞሮ ውጤቱ የሲዳማ ክልልነትን አያስቀረውም። መንግስት ባልተጠና ፖሊሲ ወደ ፖለቲካ ኪሳራ ሲገባ በተደጋጋሚ እየተመለከትን ነው። #MinilikSalsawi
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንቷ የት ገባች ???

የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንቷ የት ገባች ??? ምንሊክ ሳልሳዊ ስለፍትሕ ነው እያወራን ያለነው። ስለሕግ የበላይነት ነው እየጮኽን ያለነው። ስለሃገርና ሕዝብ መብት ነው እያወራን ያለነው።ይህ ሁሉ ወንጀል ሲፈፀም ከሕግ አንፃር ያለውን ሁኔታ ተከታትላ ለሕዝብ ማሳወቅ የሚገባትና የሕግ የበላይነት እንዲከበር መታገል የሚገባት ኃላፊነት የተጣለባት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንቷ የት ገባች ??? ድምጿን ለምን አጠፋች ??? ሕወሓት ላይ ዘራፍ ስትል የነበረች ከደብረዘይት ወደ መቀሌ ተዋጊ ጀቶች ልካ እነጌታቸው አሰፋን ለማስደብደብ የዛተች የአሜሪካንን የሕግ ገጠመኞች ለኢትዮጵያ እጠቀማለሁ ብላ የፎከረችው ወይዘሮ መዓዛ ምን ይዋጣት ምን ይሰልቅጣት ሳይታወቅ ጠፍታለች። ዝምታዋ ወይ የተረኝነቱ አንድ አካል መሆኗን አሊያም ለሕግ የበላነት መከበር ደንታ ቢስ መሆኗን ያሳያል። ሕግ ሲጣስ፣ ሕግ ሲናድ፣ ሕግ ሲዛባ፣ ሕግ የፖለቲካ መጠቀሚያ ሲሆን፣ ሕግ ንፁሃንን እያሰረ ወንጀለኞችን ሲንከባከብ የሀገሪቱ ትልቁ የሕግ አካል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዝምታ አደገኛ ነው።ይህ ሁሉ መንጋ ድንጋይ፣ አጠናና ስለት ተሸካሚ ጦር በአንድ ግለሰብ መሪነት አገር ሲያምስ፣ ሲገድል፣ ሲያቆስል፣ ንብረት ሲያወድም ዝምታን መምረጧ ኋላፊነቷን በአግባቡ ላለመወጣት ዘገምተኝነት ማሳየቷ ከተጠያቂነት አያድናትም። #MinilikSalsawi ምንሊክ ሳልሳዊ Image may contain: 1 person, smiling
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሽግግር መንግስት ለኢትዮጵያ ለምንና እንዴት ? አቶ ፋሲካ በለጠ እና አቶ እያሱ ዓለማየሁ

Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ባዶ በርሜሎች ቆርቆሮዎች

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ባዶ በርሜሎች ቆርቆሮዎች ምንሊክ ሳልሳዊ – ስለግልፅነት እያወራን የበለጠ ሚስጥራዊ የምንሆን ከሆነ ያው መዋሸት ነው፡፡ ዛሬ ያልነውን ነገ ካልደገምነው ያው መዋሸታችን ነው፡፡ ሰውን በሸራ ኳስ እያጫወትን እኛ በካፖርተኒ የምንጫወት ከሆነ ያው ማጭበርበራችን ነው፡፡ በመዋሸት የተገነባ አመኔታ ውሎ አድሮ ያዋርዳል ፤ዋጋም ያስከፍላል።   ያለአቅማችን ጉልበተኛ ነን ማለትም ሆነ ጉልበተኛ ሆነን ምስኪን ኮሳሳ ነን ማለትም ያው መዋሸት ነው፡፡ እያየን አላየንም፣ እየሰማን አልሰማንም፣ እያጠፋን አላጠፋንም ማለትም ያው መቅጠፍ ነው!ያብዬን እከክ ወደ እምዬ ልክክም ያው መዋሸት ነው!ካፈርኩ አይመልሰኝ ማለትም ያው መዋሸት ነው! Image may contain: text አስገድደን የምንፈፅመውም ሆነ ዋሽተን የምናሳምነው፣ አሊያም በገንዘብ የምንደልልው፤ የዘወትሩን ሰው ቢያስጨበጭብልንም የክቱን ሰው ያሳዝናል፡፡ በመዋሸት የተገነባ አመኔታ ከጥርጣሬ የፀዳ አይሆንም፡፡ በየፖለቲካና ኢኮኖሚያዊ ጉዳያችን አንፃር የሌለንን አለን፣ ያለንን የለንም ብለን ከዋሸንና ካሳመንን፤ ተከታያችን ሊደሰትበት፣ አልፎም ሊኮራበት ይችላል፡፡ ያም ሆኖ እንደማናቸውም ነገር ውሸትም ከጥቅም ውጪ የሚሆንበት ጊዜ አለው፡፡   የታረዱና የሞቱ ባሉበት አከባቢ የሄዱ የመንግስት ባለስልጣናት ጥቃት የደረሰባቸውን ተጎጂዎችና ሐዘንተኞች ተፈናቃዮች ሳይጎበኙና ሳያጽናኑ ተመልሰዋል። ለምን ይህን አደረጉ ፧ የጉዟቸው አላማ ፖለቲካቸውን ከኪሳራ ማዳን ብቻ ነው።   ኦዴፓ ስልጣን ከእጄ እንዳይወጣ በሚል ስጋት በየቦታው ስብሰባ እየጠራ ነው።ግጭት ሲሆን ጥቃት፤ ጥቃት ሲሆን ግጭት እያሉ ሕዝብን ለማምታታት የሚሞክሩ አካላት ያሉት በዚያው በጠቅላዩ ጉያ ነው። የታረዱና የሞቱ ዜጎችን በተመለከተ ምንም ዴንታ ያልሰጠውና ተዘዋውሮ ለማጽናናት ያልፈለገው መንግስት በከፍተኛ ባለስልጣናት ተከፋፍሎ ፖለቲካው ከእጁ እንዳይወጣ ስብከቱን ተያይዞታል። (ምንሊክ ሳልሳዊ)
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከጦርነት ኮንፈረንስ ወደ ሰላም ኮንፈረንስ = የወሩ አስቂኝ እና አስገራሚ የኦዴፓ ቀልድ

ወንጀለኞችን ለፍርድ ማቅረብ እንጂ የሰላም ኮንፈረንስና ድግስ መፍትሔ አይሆንም።…..የሰላም ኮንፈረንስ እያሉ የሐገር በጀት በስብሰባና በድግስ ይጨርሳሉ። ከጦርነት ኮንፈረንስ ወደ ሰላም ኮንፈረንስ = የወሩ አስቂኝ እና አስገራሚ የኦዴፓ ቀልድ ……….. Image may contain: 3 people ኦዴፓ ባለስልጣናቱን ወደ ኦሮሚያ ክልል ከተሞች በማሰማራት የሰላም ኮንፈረንስ መጀመሩን በሚዲያዎቹ እያስተጋባ ነው።በባሌ ሮቤ፣ አሰላ፣ ጅማ፣ ሰበታና አዳማ ከተሞች የሚካሔዱት የሰላም ኮንፈረንሶች የፍትሕን ጥያቄ ለመደፍጠጥ ካልሆነ በቀር እንደከዚህ በፊቶቹ የሰላም ኮንፈረንሶች ወሬ ብቻ ሆነው የሚቀሩ መሆናቸው አያጠያይቅም። የሰላም ኮንፈረንሶችንም ሆነ የጦርነት ኮንፈረንሶችን በበላይነት የሚመሩት የክልሉ መዋቅራዊ አካላት መሆናቸው በተግባር እያየነው ስለሆነ በቀጣይነት የሚያመጡት ውጤት የለም። መፍትሔው የመንግስት መዋቅር ውስጥ ያሉ ጽንፈኛ ባለስልጣናት ከሕዝብ ላይ እጃቸውን በማንሳት ለፍርድ መቅረብና በምትካቸው አዲስ መዋቅር ሲገነባ ብቻ ነው። ወንጀለኞችን ለፍርድ ማቅረብ እንጂ የሰላም ኮንፈረንስና ድግስ መፍትሔ አይሆንም። #MinilikSalsawi
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የአሜሪካ መንግስት ዜጎቹ አዲስ አበባና ኦሮሚያ ላይ እንዲጠነቀቁ አሳሰበ።

Security Alert: Impromptu Roadblocks and Large Gatherings የአሜሪካ መንግስት ዜጎቹ አዲስ አበባና ኦሮሚያ ላይ እንዲጠነቀቁ አሳሰበ።   አሜሪካ እንዳስታወቀችው የአዲስ አበባ መግቢያዎችና የኦሮሚያ ከተሞች መንገድ የተዘጋ ሲሆን ከፍተኛ የሆነ የጸጥታ መደፍረስ ስላለ በተለይ በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ዜጎቹ በ አስቸኳይ ወደ መዲናዋ በአይሮፕላን እንዲመጡ አሳስቧል። (ምንሊክ ሳልሳዊ) ዝርዝሩን እነሆ The embassy is monitoring reports of roadblocks preventing safe travel to and from Addis Ababa and Oromia, and large gatherings in parts of the capital. If in Oromia, we advise return to Addis Ababa via air. The U.S. Embassy is monitoring numerous reports of impromptu, private roadblocks preventing safe travel on major roads leading into and out of Addis Ababa and throughout the Oromia region.  Additionally, the Embassy is monitoring reports of large gatherings in the Bole Rwanda and Bole Japan areas of Addis Ababa, which should be avoided. All Chief of Mission personnel of the U.S. Embassy currently in Harar, Dira Dawa, and other cities in Oromia have been advised to return to Addis Ababa using air travel as soon as possible.  If vehicle travel from these locations to Addis Ababa is required, personnel have been advised to shelter in place rather than travel.  Further, Chief of Mission personnel are not
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጃዋርና የአብይ ኦዴፓ ድራማ እየሰሩ ነው።

Image may contain: one or more people, people standing, people walking and outdoor ካልደፈረሰ አይጠራም !!! ( ድራማ ??? ) ጃዋር በመንግስተ ኮማንዶዎች ተከቧል። ኦዴፓና ጃዋር ትኩሳት ለመለካት ያቀናጁት ድራማ እንዳይሆን ያጠራጥረኛል። ሰውየው ሩሲያ መሄዱን ተከትለው የኦሮሞ ጽንፈኞቹና የውሕደቱ ተቃዋሚዎች መፈንቅለ መንግስት አድርገው ይሆን ብሎ ማሰብም ሌላኛው የፖለቲካ ጥርጣሬ ነው።የሰሞኑን ቄሮ የፈጠረን ሽብርና ወከባ ተከትሎ በመንግስት ላይ የሕዝብ እና የፖለቲከኞች ጫና ስለበዛ በጃዋር አከባቢ ያለውን የተከማቸ ኃይል ለማሳየት ጥያቄ ባበዙት ብዙሃን ላይ ፍራቻ ለመልቀቅ የታቀደ ሴራም ሊሆን ይችላል። መጠራጠር ይበጃል፤ የኢትዮጵያ ፖለቲካ በሴራ የተሞላ ነው። ድራማው ቀጥሏል ። መንገድ የመዝጋቱ ሂደት አዲስ አበባ ደረሰ በዚህ ሰዓት ከጀሞ ቁጥር ፪ ወደ አዲስ አበባ ያለው መንገድ ተዘግቶ ሕዝቡ የመንግስት ያለህ እያለ ነው። በካራ በኩል ዞረው ለመግባት የሞከሩትን ደግሞ ፖሊስ አስወርዶ እየፈተሸ ነው። አደገኛ አካሔድ እንዳይሆን ጥንቃቄ ያስፈልጋል ! መንግስት እንደሰማንለት እያደረገ ከሆነ በደንብ ተዘጋጅቷል ማለት ነው ። ለአጀንዳና የሕዝብን አፍ ለማስያዝ ከሆነ ግን በስሜት ለሚደርሱ ጥፋቶች መንግስት ተጠያቂ ነው። Image may contain: one or more people, people standing and outdoor ጠባቂዎች  የጅዋርን ጊቢ ለቃቹ ውጡ ተብለዋል። ጃዋር የድረሱልኝ ጥሪ እያሰማ ነው! ራሱ ፌስቡክ ላይ ፅፏል። የስልክ ንግግሮችንም ይፋ አድርጓል። እንዲህም ሲል ፅፏል ፦ ( ጉዳዩ ለሚመለከተው ሁሉ – በብዛት ወደ መኖሪያዬ እየተሰማራ ያለው የታጠቀ ሀይል ወደኋላ እንዲመለስ በአጽኖት እንጠያቀለን። ማንኛውም ታጥቆ በዚህ ጭለማ ወደግቢ የሚንቀሳቀስ ግለስብም ሆነ ቡድን ላይ ጥበቃው የመከላከል እርምጃ እንደሚወስድ ሊታወቅ ይገባል። ለሚከሰትው ግጭት እና ጉዳት ሙሉ ሀለፊነቱን የሚወስደው ያላንዳች ምክናያት እና ማሳሰቢያ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጃዋር መሐመድ ጠባቂዎቼ ተጠርተዋል ፤ መኖሪያዬ በታጣቂ ኃይሎች ተከቧል አለ ።

ጠባቂዎች ከሰአታት በፊት የጅዋርን ጊቢ ለቃቹ ውጡ ተብለዋል። ጃዋር የድረሱልኝ ጥሪ እያሰማ ነው! ራሱ ፌስቡክ ላይ ፅፏል። የስልክ ንግግሮችንም ይፋ አድርጓል። የጃዋር መሐመድ መኖሪያ ቤት አከባቢ ያለው ሁኔታ ይህን ይመስላል። የኦሮሚያ ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች ከጃዋር ጋር አብረው እንዳሉና ለደህንነቱም ጥበቃ ተገቢ እየተደረገለት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። እንዲህም ሲል ፅፏል ፦ ( ጉዳዩ ለሚመለከተው ሁሉ – በብዛት ወደ መኖሪያዬ እየተሰማራ ያለው የታጠቀ ሀይል ወደኋላ እንዲመለስ በአጽኖት እንጠያቀለን። ማንኛውም ታጥቆ በዚህ ጭለማ ወደግቢ የሚንቀሳቀስ ግለስብም ሆነ ቡድን ላይ ጥበቃው የመከላከል እርምጃ እንደሚወስድ ሊታወቅ ይገባል። ለሚከሰትው ግጭት እና ጉዳት ሙሉ ሀለፊነቱን የሚወስደው ያላንዳች ምክናያት እና ማሳሰቢያ ሀይል ያሰማራው አካል መሆኑን ህዝቡ እንዲያውቅልን እንፈልህጋለን። Jawar Mohammed ) ጃዋር የሚታሰር ከሆነ የእሱን ደጋፊዎች ከሚያስቆጣ ማንኛውም አይነት ፅሁፍና ንግግር እንድትታቀቡ ለማሳሰብ እወዳለሁ። አላስፈላጊ የቃላት ጦርነት በመግጠም ግጭትና ሁከት እንዲቀሰቀስና እንዲባባስ ከማድረግ መቆጠብ አለብን። በተቻለ መጠን ሁኔታውን ለማረጋጋት ብንሞክር የተሻለ ይመስለኛል። #MinilikSalsawi   Image may contain: 1 person, standing and crowdየጃዋር መሐመድ መኖሪያ ቤት አከባቢ ያለው ሁኔታ ይህን ይመስላል። የኦሮሚያ ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች ከጃዋር ጋር አብረው እንዳሉና ለደህንነቱም ጥበቃ ተገቢ እየተደረገለት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከጁቡቲ የተነሱ ታጣቂ ሠርጎ ገብ አሸባሪዎች በአፋር ክልል ጥቃት አደረሱ

Image may contain: 1 person, sittingየኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ የጅቡቲ ጦር የኢትዮጵያን ድንበር ተሻግሮ ጉዳት አድርሷል የሚባለው ወሬ ሐሰት መሆኑን አስታውቋል፡፡ በትናንትናው እለት ከጁቡቲ ሠርጎ ገቦች አሸባሪዎች በአፋር ክልል በአፋምቦ ወረዳ በተኙበት ጨለማን ተገን በማድረግ በአፋር አርብቶ አደሮች በአሸባሪዎች ጥቃት ከደረሰባቸው ህፃናት መካከል ከሞት የተረፉት በርካታ ህፃናት መካከል በአሁኑ በዱቡቲ ሆስፒታል ህክምና እየተሰጣቸው ይገኛል። የሚገርመው ግን ጧቱ ላይ አርብቶ አደሮች መልሱ በማጥቃት በከፈቱት ጦርነት አሸባሪዎች በርካታ የፈረንሳይ ጦር መሳሪያ በመማረክ ከሟቾቹ በርካታ የሠነድ ማስረጃዎችን በቁጥጥራቸው ሥር ሊያደርጉ ችለዋል። አሁን የአፋር ህዝብን እየገደለ የሚገኘው ከጎረቤት አገራት የሚገቡ ሠርጎ ገቦች ናቸው። ከአፄው ዘመነ መንግስት ጀምሮ እስከ ዶክተር አብይ መንግስት ድረስ አፋርን ከበስተጀርባ ሆኖ የራሱን አለማ ለማሳከት እየጨፈጨፈ የሚገኘው የጎረቤት አገራት ፖለቲካ ጠልቃ ገብነት ነው። በዛ ልክ በኮንትሮባንድ ንግድ ላይ የተሰማሩ ከሚኒንስተር እስከጦር አመራር ያሉ የኢትዮጵያ የማአከላዊ መንግስት አመራሮች ሴራና ለሐብት ማካበት የሚደረገው ጥረት ውጤት ነው። ሚስኪኑ የኢሳና አፋር አርብቶ አደሮች ግን ፍዳቸውን እየከፈሉ ነው። ኢሳና አፋር የግጭቱን መንስኤ የሚፈቱበት አኩራ ባህል አሏቸው። ይሁን እንጅ ሰከን ብለው ጉዳዮቻቸውን እንዳይመለከቱ የሚያደርጉ የፖለቲካ ቅብብሎሽ የሚጫወቱ የኮንትሮባንድ ነጋዴዎች ስላሉ አፋርና ኢሳ ዘመን ተሻጋሪ ጠላት እንዲፈራራጁ አድርጎታል። የእምነት ወንድማማቾች ግን በሚያሳዝን ሁኔታ እልቂት በመካከላቸው እየተፈጠረ ይገኛል። የፌዴራል መንግሰት የድራማው አካል ነው። ይህ ባይሆን ኑሮማ በየግዜው የተለያዩ አስረጂ ማስረጃዎች ከጁቡቲም ፣ከሱማሌም ለዶክተር አብይ እየቀረቡለት ከፋርማጆ ጋር በቤተመንግስታቸው ተቃቅፈው በሳቅ በልፈነደቁ ነበር። Image may contain: 1 person, sittingከጁቡቲ መሪ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ለጥቅምት ሁለት ሰልፍ በሕጉ መሰረት የመንግስት አካላት የማሳወቂያ ደብዳቤ ተቀብለዋል ተባለ።

ለጥቅምት 2 የተጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ አስመልክቶ ፤ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእውቅና ደብዳቤ በአዋጅ ቁጥር 3/1983) መሰረት፤ ሰልፉ ለማካሄድ ከታያዘበት ቀን ቀድም ብሎ ከ48 ሰዓታት በፊት በጽሑፍ እና በቃል ፤ ለአ/አ ከተማ አስተዳደር ለሚመለከተው ክፍል የማሳወቂያ ደብዳቤ ገብቷል ። በህጉ መሰረት የአ/አ ከተማ አስተዳደር ጥያቄው በደረሰው በ12 ሰዓት ውስጥ በጽሑፍ ለጠያቂው አካል የማሳወቅ ኃላፊነት በሕግ ተጥሎበታል ። በ12 ሰዓት ውስጥ መልስ ያልሰጠ እንደሆነ ጥያቄው እውቅና እንዳለው በህግ ተቀምጧል ። በዚህም መሰረት ጥያቄው ከቀረበ ከ12 ሰዓት በላይ አልፎታል። ይህም በመሆኑ በዚሁ አዋጅ መሰረት የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ህጋዊ እውቅና እንዳለው በህጉ ተቀምጧል ። በሌላ መረጃ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ለጥቅምት 2 ቀን 2012 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ ጠርቶ የነበረውን የማርሻል አርት የማስ ስፖርት ዝግጅት፤ ለጥቅምት 9 ቀን 2012 ዓ/ም እንደተሸጋገረ እየተነገረ ነው። ከባለ አደራው ምክር ቤት የተገኘ መረጃ Image may contain: outdoor እየተፈፀመ ያለውን አፈና አወግዛለሁ! አንድ ሰልፍ ከመደረጉ ከ48 ሰዓት በፊት ሰልፉን የሚያደርገው አካል በደብዳቤ ለአስተዳደሩ ማሳወቅ አለበት። የአዲስ አበባ ባለ አደራ ምክር ቤት ጥቅምት 2 ለሚደረገው ሰልፍ እወቁልኝ ብሎ ደብዳቤ ያስገባው መስከረም 26 ነው። የሚመለከተው አካል (የከተማ አስተዳደሩ) ደብዳቤው በደረሰው በ12 ሰዓት መልስ መስጠት ነበረበት። በ12 ሰዓት ውስጥ መልስ ካልሰጠ በሕጉ ሰልፉ እንደተፈቀደ ይቆጠራል። የሚመለከተው አካል (አስተዳደሩ) በ12 ሰዓት ውስጥ ሰልፉ መደረግ የለበትም ብሎ መልስ ከሰጠ ምክንያቶቹን መዘርዘር ይኖርበታል። ለምሳሌ ያህል ሰልፉ ይደረግበታል በተባለው ቀን
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ባህር ዳር በተቃውሞ እየተናጠች ነው።

Image may contain: people sitting, tree and outdoorImage may contain: one or more people, crowd and outdoorባህር ዳር በተቃውሞ እየተናጠች ነው። የነጄኔራል ተፈራ ማሞን የክስ ሂደት ለመከታተል በሔዱ የባሕር ዳር ነዋሪዎችና የጸጥታ ኃይሎች መካከል ግጭት ተከስቷል። ፖሊስ ህዝቡን ለመበተን አስለቃሽ ጪስ ተጠቅሟል። የህሊና እስረኞ የሆኑት መሪዎቻችን ይፈቱልን አሁን ላይ ያስፈልጉናል እያሉ ድምፅ ሲያሰሙ መቆየታቸውን ምንጮቻችን ገልፁውልናል – ፖሊስ አስለቃሽ ጭስና ጥይት መተኮሱን ምንጮቻችን የገለፁ ሲሆን እስካሁን በሰው ላይ የደረሰው ጉዳት አልታወቀም። #MinilikSalsawi   Image may contain: sky, tree and outdoor      
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሕዝብን ዝም ለማሰኘትና ፍርሐት ለመልቀቅ የተነደፈው ሽብርና የጥላቻ ዲስኩር ሊቆም ይገባል።

Image may contain: one or more people, people walking, people standing and outdoor ሕዝብን ዝም ለማሰኘትና ፍርሐት ለመልቀቅ የተነደፈው ሽብርና የጥላቻ ዲስኩር ሊቆም ይገባል።(ምንሊክ ሳልሳዊ) Image may contain: one or more people, people standing, people walking and outdoor የሐገርንና የሕዝብን ሰላም እየነሳ ያለው መንግስታዊ መዋቅሩና በጉያው የታቀፋቸው ዘረኞች ናቸው ብለን መጮኽ ከጀመርን ቆየን።መንግስታዊ መዋቅሩ ውስጥ ያሉት የመንግስት ባለስልጣናትና በእቅፎቻቸው ያሉ ዘረኞች ጥላቻ እየነዙ ሰላምን እያደፈረሱ ነው። ይህንንም በሸኖ በአጣዬና ድሬደዋ እያየነው ነው። በሸኖ ከግሸን ደብረ ከርቤ ሐይማኖታዊ በዓል የሚመለሱ ምእመናንና በአጣዬና ድሬደዋ በሰላም የሚኖሩ ነዋሪዎችን በማሸበር ተግባር ላይ የተሰማሩ የመንግስት ሰዎችና የጥላቻ አራማጆች እጃቸውን ከሰላማዊ ሕዝብ ላይ ሊያነሱ ይገባል።ዜጎች በገዛ ሐገራቸው ተዘዋውረው የመኖር መብት እንዳላቸው መንግስት ሊያውቅ ይገባል። Image may contain: car and outdoor ከግሸን ደብረ ከርቤ ክብረ በአል ተመላሾች በአሁኑ ሰአት ሸኖ ላይ ከፊትም ከኃላም መንገድ ተዘግቶባቸው ቆመዋል፤ ከእሬቻ ክብረ በዐል ሲመለሱ ደብረ ብርሃን የታሰሩ ወጣቶች ካልተፈቱ መንገዱን አንክፍትም ተብለዋል፤ደብረብርሃን ላይ የታሰሩት ከወራት በፊት ኬሚሴ እና አጣዬ ላይ ጥቃት እንዲፈፀም ያደረጉ የታጣቂው ኦነግ አመራሮች ናቸው። እነዚህ ሶስት አመራሮች ማደኛ ሲወጣባቸው ተደብቀው ወለጋ ከርመዋል። በቅርቡ ለኢሬቻ በሚል በኬሚሴ በኩል ሲመጡ የኬሚሴ አመራሮች ጠቁመው አስይዘዋቸዋል። Image may contain: sky, outdoor and nature አጣዬ የተፈጠረው ተኩስና አለመረጋጋት አሁንም እንደቀጠለ ነው። ሁኔታዎች ወደከፋ ደረጃ እንዳይደርሱ መንግስት የባለስልጣናቱን የሽብር እጆች በመሰብሰብ መፍትሄ መፈለግ አለበት፤ ችግሩም የመንግስት ልዩ ትኩረት ይሻል። ዛሬ በጠዋቱ ቄሮ ናቸው የተባሉ ኦሮሞ ወጣቶች በአይሱዙ መኪና ተጭነው ወደ ድሬደዋ ሲገቡ የፅጥታ ኃይሉ ሁኔታውን ተከታትሎ ችግሩ ሳይፈጠር ማስቆም ይችል ነበር። በአይሱዙ የገቡት ወጣቶች ደቻቱ ሰፈር ችግር መፍጠር ሲጀምሩ (እንደ ነዋሪዎቹ ከሆነ መደብሮችን
Posted in Amharic News, Ethiopian News