" /> DW Amharic | Mereja.com - Ethiopian Amharic News
Blog Archives

238 ኢትዮጵያዊያን ከሌባኖስ ወደ ሀገራቸው ይመለሳሉ

መንግስት ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲን ትኩረት አድርጎ በመስራቱ  238 ኢትዮጵያዊያን ከሌባኖስ ወደ ሀገራቸው እንደሚመለሱ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ። ሚኒስቴር መስርያ ቤቱ በተለያዩ ወቅታዊና አገራዊ ጉዳዮች ላይ ዛሬ በሰጠዉ መግለጫ ከጥር 6 እስከ 11 ባሉት ተከታታይ ቀናት  238 ኢትዮጵያዊያን ከሌባኖስ ወደ ሀገራቸው ይመለሳሉ።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከእገታ የተለቀቁት ተማሪዎች የት ናቸው?

ከደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ወደ ቤተሰቦቻቸው ሲሄዱ ከታገቱ በኋላ መንግስት መለቀቃቸውን ያስታወቀው ሃያ አንድ ተማሪዎች ወደ ደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ መመለሳቸውን የኦሮሚያ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ከዶይቸ ቬለ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ተናገሩ።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በአፍሪቃ የትምህርት አሰጣጥ ላይ የተማሪዎች ቅሬታ 

አፍሪቃ ውስጥ የሚሰጠው ትምህርት ለስራ ገበያው ብቁ እንደማያደርጋቸው በርካታ አፍሪቃውያን ይወቅሳሉ። በውጭ ሀገራት የትምህርት እድል ያገኙ ተማሪዎች እንደሚሉት አፍሪቃ ውስጥ ትምህርት በነባቤ ቃል እንጂ እምብዛም በተግባር ሲሰጥ አይታይም።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኤክሳይስ ታክስ ረቂቅ አዋጅ ብዥታ ፈጥሯል ተባለ 

መንግስት ረቂቅ ህጉን ሲያዘጋጅ በዘርፉ የሚታዩ በርካታ ችግሮችን የመፍታት ውጥን ይዞ በጥንቃቄ የተሰራ ፣ ገቢን ከመሰብሰብ ባለፈ የሃገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ ለማምጣት አስቦ መሆኑ ሊታወቅ እንደሚገባ የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀው አስታወቀ።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ምርጫ በክረምት፦ ክፋቱ እና ደግነቱ

አዲሱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመስከረም ወር ሥራ እንዲጀምር ይጠበቅበታል። ነባሩ ምክር ቤት ደግሞ የራሱን ዕድሜ ማራዘም አይፈቀድለትም። እንዲያውም የኢትዮጵያ በጀት ዓመት መዝጊያ ሰኔ 30 በመሆኑ ከሐምሌ 1 በኋላ ፓርላማው ሕጋዊ አይደለም እያሉ ‘አሁንም ቢሆን ምርጫው ዘግይቷል’ የሚል መከራከሪያ የሚያቀርቡ ሰዎች አሉ።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የጣና በለስ የስኳር ልማት ፕሮጀክት የገበሬ እርግማን?

ለጣና በለስ የስኳር ፋብሪካዎችና የሸንኮራ አገዳ ልማት በጃዊ ወረዳ ከ50 ሺሕ ሔክታር መሬት ላይ ከ4 ሺሕ በላይ አባወራዎች እንዲነሱ ከተደረገ ስምንት አመታት ተቆጠሩ። በቦታው ከታቀዱ ሶስት ፋብሪካዎች በግንባታ ላይ የሚገኘው አንድ ብቻ ሲሆን ለስኳር የለማ የሸንኮራ አገዳ ተቃጥሏል። ገበሬዎች የተሰጣቸው ምትክ መሬት አመቺ እንዳልሆነ ይናገራሉ...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በቫቲካን የኢትዮጵያ ጳጳሳዊ ኮሌጅ 100ኛ ዓመት ተከበረ

የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን መቀመጫ በሆነችው ቫቲካን የሚገኘው የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተ-ክርስቲያን ጳጳሳዊ ኮሌጅ 100ኛ አመት ተከበረ። ከኢትዮጵያና ከኤርትራ የተጓዙ ጳጳሳት፤ በጣልያን የኢትዮጵያ አምባሳደር ዘነቡ ታደሰና የእምነቱ ተከታዮች ተገኝተዋል። ይኸው የጳጳሳት ማሰልጠኛ ኮሌጅ የተመሠረተው በጎርጎሮሳዊው 1919 ዓ.ም. ነበር...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኢራንና የዩናይትድ ስቴትስ የጠላትነት ቁንፅል ወግ

ክሮከር ጄኔቭ ዉስጥ የኢራኑ ወጣት ጄኔራል ቃሲም ሱሌይማኒይ ከላኳቸዉ የቴሕራን ባለስልጣናት ጋር የአፍቃኒስታኑን አክራሪ ገዢ ፓርቲ ታሊባንን እና አልቃኢዳን በጋራ ለማጥፋት ተስማምተዉ ተመለሱ።የአሜሪካ ጦር በጄኔራል ሱሌማንይ ትዕዛዝ ከኢራን በሚንቆረቆርለት መረጃ እየታገዘ የአልቃኢዳና የታሊባን ስልታዊ ይዞታዎችን ያወድመዉ ያዘ።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

እምነት ተቋማት ጥቃት ላይ ውይይት ተደረገ

የሰላም ሚኒስቴር በሃይማኖት ተቋማትና እየደረሰባቸው በሚገኝ ጉዳት ዙሪያ ውይይት አድርጓል። በውይይቱ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በየጊዜው ባደረጉት የሰላም ጥሪ በተቋማቱ ላይ እየደረሰ ካለው አደጋ በላይ እንዳይደርስ ከፍተኛ ጥረት ማድረጋቸው ተነግራል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኦሮሞ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች አነጋጋሪ ንግግሮች

በቅርቡ ጥምረት የፈጠሩት ሦስቱ የኦሮሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ ፣ የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረንስ ኦፌኮ እና የኦሮሞ ብሄራዊ ፓርቲ ኦብፓ በጋራ እና በተናጥል የምርጫ ዘመቻ ማድረግ ጀመሩ።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የስፖርት ውርርድ መሥፋፋት 

በኢትዮጵያ በስፖርት ጨዋታዎች በተለይም በአውሮጳ ሊጎች ውጤቶች ላይ ያተኮሩ ውርርዶች የሚያካሒዱ ተቋማት እየተስፋፉ ነው። የተቋማቱ መሥፋፋት የተለያዩ ማኅበራዊ እና ኤኮኖሚያዊ ችግሮች ሊያስከትሉ ይችላሉ የሚል ሥጋት እየተሰማ ነው።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የዩንቨርሲቲዎቹ አስተዳደራዊ ርምጃ በተማሪዎች ዕይታ

በኢትዮጵያ ዩንቨርሲቲዎች ከዕዉቀት መገበያያነት ይልቅ ጎራ ለይቶ መጋጨትና ብጥብጥ መፍጠር  እየተለመደ መጥቷል።የሚከሰቱት ግጭቶችም ተምረዉ ሀገር ህዝብና ቤተሰብን ያገለግላሉ ተብለዉ ተስፋ የተጣለባቸዉ ወጣቶች ለሞትና ለአካል ጉዳት እየተዳረጉ ይገኛል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

 የደቡብ ኢትዮጵያ የመንገድ ሥራ መጓተት

የደቡብ ኢትዮጵያ መስተዳድር ርዕሠ ከተማ ሐዋሳን፣ ከዲላ፣ ከይርጋ ጨፌና ከሌሎች የሲዳማ ዞን እና የኦሮሚያ ከተሞች ጋር እንዲያገናኝ የታቀደ ነበር።አጠቃላይ መንገዱ ተሰርቶ ሳያበቃ፣ እስካሁን የተሰራዉ የአስፋልት መንገድ እየፈረሰ ነዉ...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኢራን ባለስቲክ ሚሳይል እና የአባይ ወንዝ ድርድር

የኢራን እና የዩናይትድ ስቴትስ ፍጥጫ የሚሳይል ድብደባ አስከትሏል። ግብፅ፤ ኢትዮጵያ እና ሱዳን በአባይ ወንዝ ጉዳይ አዲስ አበባ ውስጥ በዝግ ያደረጉት ስብሰባ ያለስምምነት ጠናቋል። በኢትዮጵያ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተከሰተው አለመረጋጋት ከመጉላላት እና ከአካል ጉዳት ባሻገር የተማሪዎች ሕይወት እንዲቀጠፍ አድርጓል። አስተያየቶችን አሰባስበናል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

 የባላደራ ምክር ቤት የምርጫ ዕቅድ

አቶ እስክንድር ነጋ ዛሬ እንዳስታወቁት አምና መጋቢት የተመሠረተዉ ምክር ቤት የፊታችን ሰኞ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፓርቲነት እዉቅ እንዲሰጠዉ ይጠይቃል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የአውሮጳ ሕብረት እና የሊቢያው ጦርነት

የአውሮጳ ሕብረት እየተስፋፋ ያለውን ጦርነት ለመግታትና የአሜሪካና ኢራን ፍጥጫ እና ጥቃት ወደባሰ ጦርነት እንዳያድግ ሰሞኑን የሚቻለውን የዲፕሎማሲ ጥረት እያደረገ ነው። በሌላ በኩል ግን በሊቢያ የጀነራል አፍጣር ጦርና በተመድ እውቅና ባለው የትሪፖሊው መንግሥት የገቡበት ጦርነት ግን ሕብረቱን አጣብቂኝ ውስጥ እንደከተተው ነው የሚነገረው።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የጎሮ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ አመራሮች ታሰሩ

በቤኒ ሻንጉል ጉምዝ ክልል ለመንቀሳቀስ ዛሬ ቢሮውን የከፈተው የጎሮ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ የተባለ ክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲ ዛሬ አሶሳ ከተማ ከሚገኘው ጽህፈት ቤቱ አመራሮቹ እንደታሰሩበት አስታወቀ። ዶቸ ቬለ ስለ ጉዳዩ የጠየቃቸው የቤኒ ሻንጉል ጉሙዝ ክልል የጸጥታ እና የሰላም ግንባታ ቢሮ ኃላፊ ግን ምንም  አላውቅም ብለዋል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አራተኛዉ ዙር የዓባይ ግድብ ጉባዔ በአዲስ አበባ 

በሕዳሴው ግድብ ዙሪያ  በግብጽ፤ ሱዳን እና ኢትዮጵያ መካከል የሚደረገው አራተኛ ዙር የሦስትዮሽ ስብሰባ አዲስ አበባ ውስጥ በዝግ ተጀምሯል። የመክፈቻ ሥነ-ስርዓቱ ብቻ ለአጭር ጊዜ ለመገናኛ ብዙኃን ክፍት ነበር። በነገው ዕለት ማምሻው ላይ ስለዝግ ስብሰባው መግለጫ እንደሚሰጥም ከአዘጋጆቹ ጠቁመዋል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሳልሳይ ወያኔ «ሕገ መንግሥት ለማሻሻል እታገላለሁ»

የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ላይ ማሻሻያ ለማድረግ እንደሚታገል ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ዐስታወቀ። በቅርቡ በትግራይ ከተመሰረቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል አንዱ የሆነው ሳልሳይ ወያነ ትግራይ (ሳወት) አመራሩን መርጦ ፕሮግራሙንም ያጸደቀው ባለፈው ቅዳሜ እና እሁድ ባደረገው የመጀመሪያ ድርጅታዊ ጉባኤው ነው።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ

እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ ዉድ የዶቼ ቬለ ተከታታዮች! በዓል እንዴት ነዉ? ለሃገራችን ኢትዮጵያ ሰላም፤ ፍቅር፤ መተሳሰብን ያብዛልን! በዓሉ የመተሳሰብ የሰላም እና የፍቅር ይሁን።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ማሕሌት ፈቃዱና ስራዎቿ

ተለያዩ ታሪኮች አንድ ወይም ተመሳሳይ ገፀ ባሕሪ ተላብሶ መጫዎትን፣ «እንደዚያ መሆን አልፈልግም» ትላለች።የተለያዩ ገፀ ባሕሪያትን መስላ-የመሰለችዉን እንደሆነች ያክል አስመስላ መተወኑን ትወዳለች...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የትግራይ መንግሥት ተቃዋሚዎች ሥጋትና ዉግዘት

የትግራይ ምክትል ርዕሠ-መስተዳድር ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል ባለፈዉ ሳምንት ማብቂያ ያስተላለፉትን ማስጠንቀቂያ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ነቀፉት።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

 የሞጣ ፀጥታ አሰከባሪ ኃላፊዎች ታሰሩ

ኃላፊነታቸውን በአግባቡ አልተወጡም የተባሉ 5 የከተማይቱ የፀጥታ አስከባሪ ኃላፊዎች መታሰራቸዉን የምሥራቅ ጎጃም ፖሊስ ዐስታወቀ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ይዞታ እና የድሬዳው ሰልፍ 

አንድ የዩኒቨርስቲው ተማሪ ለዶቼቬለ እንደተናገረው ዩኒቨርስቲው ባመቻቸው ነጻ የባቡርና የአውቶብስ ትራንስፖርት ተማሪዎችን ወደ የመጡበት እየሸኘ ነው። ዩኒቨርስቲው ላልተወሰነ ጊዜ መዘጋቱ ነው የተነገረው። ዩኒቨርስቲው ስለተዘጋበት ምክንያት እና ስለ ተማሪዎቹ ሽኝት ዶቼቬለ ከዩኒቨርስቲው ትክክለኛውን መረጃ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሕገ ወጥ ንግድን በመከላከል የመገናኛ ብዙሃን ሚና

መገናኛ ብዙሃን በነጻነት የምርመራ ዘገባዎችንና መረጃዎችን አከታትለው እንዲያወጡ ልዩ ድጋፍ ሊደረግ እንደሚገባ ተገልጿል። የቁጥጥር መላላት፣የውጪ ምንዛሪ እጥረትና የፖለቲካ አለመረጋጋት በኢትዮጵያ እያሻቀበ ለመጣው ሕገወጥ ንግድ ዋነኛ ምክንያት ናቸው ተብሏልም። በተለይ የሕገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ሀገሪቱን ስጋት ላይ እየጣላት መሆኑም ተገልጿል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አዲስ አበባ የቱሪስት መዳረሻ

የአዲስ አበባ አስተዳደር ባህል፤ ኪነ ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ከተማዋ በዓለም የጎብኚዎች አንዷ መዳረሻ መሆኗን አመለከተ። ከተማዋ በዓለም ቱሪዝም ምክር ቤት በጎርጎሪዮሳዊው 2020 ላይ ተመራጭ ከሆኑ ከተሞች ተርታ መግባቷም ተሰምቷል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በደሴና ጅማ ከተሞች የእስልምና እምነት ተከታዮች ሰልፍ አደረጉ

ደሴ እና ጅማን ጨምሮ በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች በሞጣ ከተማ የእምነት ተቋማት ላይ የተፈጸመውን የማቃጠል ተግባር የሚኮንኑ ሰልፎች አድርገዋል። የሰልፎቹ ተሳታፊዎች በእምነት ተቋማት ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች አገሪቱን ለከፋ ቀውስ ሊዳርጉ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ቤተ እምነቶች ለምን ዒላማ ሆኑ?

ዛሬ ዛሬ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ተቃርኖ ምንም እንኳን በብሔርተኝነት የተቃኘ ቢመስልም በውስጠ ታዋቂነት የሃይማኖት ተቃርኖ ያለበት መሆኑን መካድ አይቻልም። የኦሮሞ ብሔርተኞች የክርስትና ወይም የእስልምና እምነት ተከታዮች ቢሆኑም ቅሉ፥ አብዛኛዎቹ የዋቄፈና እምነት ዓመታዊ በዓል የሆነውን የኢሬቻ በዓል ከማክበር አይቆጠቡም።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኦፌኮ የታሰሩ አባላቱ ሲፈቱ ሌሎች በዚህ ሳምንት ታስረዋል ይላል

ከተፈቱት መካከል የምስራቅ ወለጋ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ   ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፈቃዱ  አያና ከተፈቱት መካከልይገኙበታል። አቶ ፈቃዱ እና ሌሎች የኦፌኮ አባላት  በነጻ መለቃቀቸውን የተናገሩት የዞኑ ኦፌኮ ጸሐፊ  አቶ ዓለሙ ኦሉማ በዚህ ሳምንት ደግሞ በምስራቅ ወለጋ ሃሮ ሊሙ በተባለ አካባቢ  የኦፌኮ አባላት መታሰራቸውንም ገልጸዋል፡፡...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በሞጣ 33 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ፖሊስ አስታወቀ

ሰሞኑን በሞጣ ከተማ ከቤተ-እምነቶች ቃጠሎና ዝርፊያ ጋር በተያያዘ 33 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ አስታወቀ። በአማራ ክልል የሰላምና ደህንነት ቢሮ የሚመራ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትና የኃይማኖት በሞጣ ዛሬ ጉብኝት ማድረጋቸውን የከተማዋ ባለስልጣናት ተናግረዋል። ...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ምሥራቅ ጎጃም ዞን ሞጣ ከተማ መስጊዶች ተቃጠሉ

በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን ሞጣ ከተማ በአራት መስጊዶች ላይ ጥቃት መፈጸሙን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታወቀ። ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ ሁለቱ መስጊዶች በቃጠሎ ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን እና ሌሎች ሁለቱ ላይ ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው አስታውቋል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጉልህ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ማጣራት እንደሚጀምር የዕርቀ -ሠላም ኮሚሽን አስታወቀ

ጉልህ የሆኑ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ማጣራት እንደሚጀምር የፌድራል ዕርቀ -ሠላም ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ የዕርቀ -ሠላም ኮሚሽን አባላት ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ነዋሪዎች ጋር በአሶሳ ውይይት አድርገዋል፡፡...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብሰባ በትግራይ

«የትግራይ ሁለንተዊ ጥቅም በኢትዮጵያ ጥላ ሥር» በሚል ርዕስ በትግራይ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች፤ምሁራን እንዲሁም የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ንቁ ተሳታፊዎች  የተገኙበት ውይይት መቀሌ ላይ እየተካሄደ ነው።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የባለሃብቶች ንብረት ምዝገባ

የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት  ያስመዘገቡትን ሃብት ለማንኛውም ኢትዮጵያዊ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እና ምክንያት መረጃ እንደሚሰጥ የፌደራል  የፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የበይነ መረቡ ምኅዳር ፈተና የመቋቋምያ አማራጮች

ማንነትን ለመሰወር እና ከአደገኛ ስለላም እራስን ለመጠበቅ ደካማ የኔትወርክ አገልግሎት ባላቸው አገራት ቶርን መጠቀም አስቸጋሪ መሆኑ አያጠያይቅም።በአሁኑ ወቅት ግለሰቦችንና እንደ ዶይቼ ቨለ "DW"ያሉ ድርጅቶች የበይነ መረብ ቅድመ ምርመራን ለመከላከል በስፋት የሚጠቀሙባቸው የኦንየን ድር ጣቢያዎችን መድረስ የሚችሉ ልዩ የቶር አውታረ መረቦችም አሉ።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ ምዕራብ ዘረጋች?

ኢትዮጵያ ከዓለም የገንዘብ ድርጅት፤ ከዓለም ባንክና የልማት አጋሮች 8.9 ቢሊዮን ዶላር ብድርና ርዳታ ማግኘቷን ባለሥልጣናቱ አስታውቀዋል። የዓለም የገንዘብ ድርጅት ለኢትዮጵያ የሚያበድረው 2.9 ቢሊዮን ዶላር አገሪቱ ካላት ከተቋሙ የመበደር አቅም በ700% ይልቃል። ብድር የውጭ ምንዛሪ ግብይት ሥርዓቱን ጨምሮ ለተለያዩ ዘርፎች ማሻሻያ የታቀደ ነው።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የዳንር እና የጃዊ ተፈናቃዮች ሮሮ

የቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል የአደጋ ስጋት ጽ/ቤት ከሐምሌ 2011 አንስቶ በተለያዩ መጠለያ ጣቢያዎች አዋቂዎችን ጨምሮ 14 ህጻናት በወባ እና የተለያዩ በሽታዎች መሞታቸውን ተናግረዋል፡፡በጥቅምት ወር  የሚቀርበው እርዳታ ዘግይቶ እንደነበር የተናገሩ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ በፓዌ ወረዳ ከውሀ እጥረት ውጭ ወቅቱን ጠብቆ ዕርዳታ እየተሰጠ ነው ብለዋል፡፡...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የአዲሱ ነጻነት እና እኩልነት ፓርቲ የምርጫ ዝግጅት

ሴራ ፖለቲካ ይልቅ አብሮ በማሸነፍ መርህ ላይ የተመሰረተ ትግል እንደሚያካሂድ የገለጸው ፓርቲው ተመሳሳይ አመለካከት ካላቸው ፓርቲዎች ጋር በመስራት በሃገራዊ ምርጫ ለመሳተፍ መዘጋጀቱን ገልጿል።ፓርቲው በመሃል አገር ተወስኗል ያለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ በሃገሪቱ የጠረፍ አካባቢዎች ያለው ሕዝብ እንዲያካትት የማድረግ ዓላማም እንዳለው አስታውቋል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የፍልሰተኞች ቀን በአዲስ አበባ 

ድርጅቱ ፍልሰተኞች የችግሮች ሁሉ ምንጭ ተደርገው ሲወነጀሉ እንጂ የመፍትሄ አካል ተደርገው አይታይም ብሏል።ፍልሰት በብዙ ሃገሮች ስጋት ሆኖ ስለሚታይ ለህገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል ያለው ድርጅቱ ዛሬ የተከበረው የፍልሰተኞች ቀን ቤታቸውንና ሃብታቸውን ለስደተኞች የሚያጋሩ መልካም ማህበረሰቦች የሚታሰቡበት ነው በማለት ዛሬ አስታውቋል...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

«ትዴፓ» በትግራይ የፖለቲካ ምህዳሩ ጠባብ ነዉ አለ

«ትዴፓ» በትግራይ የፖለቲካ ምህዳሩ ጠባብ ነዉ አለ። በዶክተር አረጋዊ በርኸ የሚመራው ትግራይ ዴሞክራስያዊ ፓርቲ «ትዴፓ» በትግራይ የፖለቲካ ምህዳር ጠባብ በመሆኑ በክልሉ የሚያደርገው እንቅስቃሴ የተገደበ መሆኑን ገልፆአል። በቅርቡ ስያሜውን ከትግራይ ዴሞክራስያዊ ትብብር ወደ ትግራይ ዴሞክራስያዊ ፓርቲ «ትዴፓ» የቀየረው በዶክተር አረጋዊ በርኸ የሚመራው ፓርቲ በትግራይ ያለው የፖለቲካ ምህዳር ጠባብ በመሆኑ በክልሉ የሚያደርገው እንቅስቃሴ የተገደበ መሆኑ ገለፀ፡፡ ፓርቲው በአዲስ አበባ ከከፈተው ጽ/ ቤቱ በተጨማሪ በቅርቡ የመጀመሪያ ማስተባበርያ ቢሮ በመቐለ ከፍቷል፡፡  የትግራይ ክልል መንግስት በክልሉ የፖለቲካ ምህዳሩ ጠባብ ነው የሚለው ወቀሳ አይቀበልም፡፡ https://radiodownloaddw-a.akamaihd.net/Events/dwelle/dira/mp3/amh/4E44875A_1_dwdownload.mp3
Tagged with: ,
Posted in Amharic News

ዉይይት፣ ፓርቲና ፎረም

የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች በተለይ የገዢዉ ፓርቲ መሪዎች ግን ግጭት ግድያዉን ለማስቆም ከሚያደርጉት ጥረት ይልቅ ጎራ ለይተዉ አዲስ አበባ እና መቀሌ ላይ የብልፅግና ፓርቲ እና የፌደራሊስት መድረክ ያሏቸዉን የፖለቲካ ስብሰቦች መመስረታቸዉን እየነገሩን ነዉ።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ቆይታ ከድምፃዊ አብርሃም በላይነህ ጋር

ድምፃዊ አብርሃም በላይነህ በናይጄሪያ ሌጎስ ለ6ኛ ጊዜ በቅርቡ በተካሄደው የመላው አፍሪካ የሙዚቃ ውድድር /AFRIMA/ "እቴ አባይ" በተሰኘ ነጠላ ዜማው በአፍሪካ ባህላዊ የሙዚቃ ዘርፍ የዘንድሮዉ/2019/ አሸናፊ ነዉ።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የበሳይበር ምህዳር ጥቃትና ጥበቃ

ቴክኖሎጂ የሰዉ ልጆችን የዕለት ተዕለት ህይወት በማቅለል ረገድና ዓለም አቀፋዊ ትስስርና ቅርርብ በመፍጠር የሚጫወተዉ ሚና ቀላል አይደለም። ይሁን እንጅ ይህ የቴክኖሎጅ አጠቃቀምን ተከትለዉ የመጡ የጎንዮሽ ስጋቶችም የዚያኑ ያህል አሳሳቢ ናቸዉ።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የተቃውሞ ሰልፍ በፓሪስ

ዛሬ በርካታ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያናት እና የዕምነቱ ተከታዮች ላይ «የሚፈፀም በደል ይቁም» ሲሉ በፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስ የተቃውሞ ሰልፍ አካሂደዋል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭት በኢትዮጵያ

በሀገሪቱ ከሶማሌ ፣ ኦሮሚያ እና የደቡብ ክልሎች በስተቀር በሌሎቹ ክልሎች የቫይረሱ ስርጭት በወረርሽኝ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ዳንኤል በትረ ለዶቼቬለ ተናግረዋል። ሴተኛ አዳሪዎችን ጨምሮ የረዥም ርቀት አሽከርካሪዎች እና መለዮ ለባሾች በከፍተኛ ደረጃ ለቫይረሱ  ተጋላጮች መሆናቸው መለየቱንም አቶ ዳንኤል ገልጸዋል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኢሕአዴግ ውሕደት የመጨረሻ ምዕራፍ 

የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዲፒ) እና እና የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) ብልጽግና የተባለውን የአዲሱን ዉሕድ ፓርቲን መመስረት ከማፅደቃቸዉ በፊት ከውህደት በኋላ ሊገጥሟቸው በሚችሉ ተግዳሮቶች ላይ ከአባላቶቻቸው ጋር መምከራቸውን በየፊናቸዉ አስታወቁ።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በደቡብ ክልል የጉራጌና የወላይታ ዞን ጥያቄ 

በደቡብ ክልል ቀደምሲል ራሳቸውን በክልል ለማደራጀት ወሳኔ ባሳለፉ ዞኖች የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጥያቄው ገቢራዊ እንዲሆን የተለያዩ ግፊቶችን እያደረጉ ይገኛሉ።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር / ኦነግ / ያቀረበዉ ጥሪ

ሸኔ ማለት በድሮው አጠራር የፖሊት ቢሮ አባል ወይም በአሁኑ የመዋቅር ደረጃ የስራ አስፈጻሚ ማለት ነው ያሉት ቃል አቀባዩ በአሁኑ ወቅት እንዲህ ያለው አደረጃጀት ከድርጅታቸው መዋቅር ውጪ መሆኑን በመግለጽ፡ ህዝቡ ግን ከጠቅላላው የኦነግ አባላት እና ከሚያደርሱ ጥፋቶች ጋር በማያያዝ ባልተገባ መንገድ ሲነሳ ይታያል ብለዋል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የትግራይ ክልል የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ቅሬታና ስጋት 

ግጭቶች ሰግተው ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲዎች ያልገቡና ትምህርታቸው አቋርጠው ወደ ቅያቸው የተመለሱ የትግራይ ተማሪዎች መንግስት መፍትሔ ስላልሰጠን ከትምህርት ውጭ ሆነናል ሲሉ ቅሬታቸው ገለፁ፡፡...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ህወሓት በኢህአዴግ ዉሕደት አቋሙን ለመግለፅ ጉባኤ ሊቀመጥ ነዉ

ህወሓት የኢህአዴግ ውህደት አጀንዳ በስራ አስፈፃሚውና ማእከላይ ኮሚቴ ደረጃ ያልተቀበለው ቢሆንም የመጨረሻ የሚታወቀው በቅርቡ በሚጠራው የህወሓት ጉባኤ ላይ ነው ሲሉ የህወሓት ሊቀ መንበር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ተናገሩ፡፡ ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በመንገድ ደህንነት ቀን በተሽከርካሪ አደጋዎች 49 ሰዎች ሞቱ

በኢትዮጵያ የሚደርሰው የተሽከርካሪ አደጋ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ተከትሎ ወደ ሃገር ውስጥ የሚገቡ ተሽከርካሪዎችን የዕድሜ ገደብ በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ተግባራዊ እንደሚያደርግ ትራንስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ። በኦሮሚያ ትናንት እሁድ በሰባት የተለያዩ አካባቢዎች በደረሱ አደጋዎች የ34 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ60 ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል። ...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ዓለም አቀፍ የኤሌክትሮኒክ ግብይትን ለማስጀመር የተካሄደ ስምምነት 

በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የኤሌትሮኒክስ ግብይት ለማስጀመር የሚያስችል ስምነት ከአሊባባ ቡድን ጋር ተፈራረመች። ይህ መገበያያ የሀገሪቱን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ የሚደግፍ መሆኑን ታዉቋል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

19 የጎንደር ዩንቨርስቲ ተማሪዎች በምርመራ ላይ ናቸዉ 

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሁከት ለመፍጠርና የመማር ማስተማሩን ሂደት ለማደናቀፍ ሲሞክሩ ተይዘው ከነበሩ 40 ተጠርጣሪዎች መካከል 21ዱ በምክርና በተግሳፅ ሲለቀቁ 19ኙ ተጨማሪ ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አስታወቀ።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከ«ኢሕአዴግ» ወደ «ብልጽግና»?

ኢሕአዴግ ከእለት ተእለት ፖለቲካዊ አውድ ገሸሽ ሊደረግ፤ አለያም ሊወገድ ጠርዝ ላይ ተጠግቷል። ለምን ያኽል ጊዜ እንደሚቆይ ባይታወቅም በምትኩ «ብልጽግና» የተሰኘ አዲስ ፓርቲ የፖለቲካ መድረኩን ሊቆጣጠር ዳር ዳር እያለ ነው።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ወጣቱ በግብርና የማይሰማራበት ችግር ላይ ውይይት ተካሄደ

በኢንዱስትሪ የበለጸጉት ሀገራትን ያካተተው ቡድን ሰባት ተብሎ የሚጠራው ስብስብ ተወካዮች ከሰሃራ በታች ካሉ ሀገራት ከሚገኙ የተለያዩ አፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ወጣት አርሶ አደሮች ጋር በአዲስ አበባ ተወያይተዋል። ስብሰባውን በበላይነት ያስተባበረችው የቡድን ሰባት የወቅቱ ሊቀመንበር የሆነችው ፈረንሳይ ነች።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

“ህዝበ ውሳኔው ስርዓቱን የተከተለ ነው”-የሲዳማ ፓርቲዎች

ትናንት የተካሄደው የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ “ህጋዊ ስርዓቱን የተከተለ፣ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድም ገለልተኝነቱን ያስመሰከረበት ነበር” ሲሉ ሁለት የሲዳማ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጀቶች ገለፁ። የሲብዴፓ እና የሲአን አመራሮች ህዝበ ውሳኔው “የሲዳማ ብሄር በህገ መንግስቱ ያገኛቸውን መብቶች በአግባቡ እንዲጠቀም ምቹ ሁኔታን የፈጠረ ነው” ብለዋል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ውጤት በየጣቢያዎች ይፋ ተደርጓል

የሲዳማ ክልል የመሆን ጥያቄ ህዝበ ውሳኔ ውጤቶች ዛሬ በየምርጫ ጣቢያዎች ይፋ ተደርጓል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የህዝበ ውሳኔውን የመጀመሪያ ደረጃ ውጤት ከ24 እስከ 48 ሰዓት ባለው ጊዜ እንደሚያስታውቅ ትላንት ምሽት ቢገልጽም እስካሁን ድረስ ውጤቱን አላሳወቀም።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ህወሓት ከኢህአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ ለምን ቀረ?

ህወሓት ዛሬ መካሄድ በጀመረው የኢህአዴግ ምክር ቤት ላይ እንደማይሳተፍ አስታውቋል። ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸው አንድ የህወሓት አመራር አባል ድርጅታቸው የውህደቱ ጉዳይ በሰከነ መንፈስ እንዲታይ በመፈለጉ ከዚህ ውሳኔ ላይ እንደደረሰ ገልጸዋል። በመቀለ ዩኒቨርስቲ የሚያስተምሩ የፖለቲካ ተንታኝ “ህወሓት ከኢህአዴግ ጋር ያለው ፍቺ አልቋል”ብለዋል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኢህአዴግ ውህደት በአዲስ አበባ ነዋሪዎች ዕይታ

በአዲስ አበባ ከዛሬ ጀምሮ ለስብሰባ የተቀመጠው የኢህአዴግ ምክር ቤት በዋነኛነት ከሚመለከታቸው ጉዳዮች አንዱ በግንባሩ ስራ አስፈጻሚ ደረጃ የጸደቀው የውህደት ጉዳይ አንዱ ነው። የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ስለ የኢህአዴግ ውህደት የሰጧቸውን አስተያየቶች የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሃንስ ገብረ እግዚያብሔር እንደሚከተለው አሰባስቧቸዋል።     ...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኢትዮጵያ በእግርኳስ ግጥምያ ኮትዲቯርን 2 ለ1 ረታች

ዛሬ ባህር ዳር ከተማ ውስጥ በተካሄደዉ የአፍሪቃ ዋንጫ ማጣሪያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን የኮትዲቯር ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድንን 2 ለ 1 አሸነፈ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኢሕአዴግ ዉሕደትና የበኒሻንጉል ተቃዋሚ ፓርቲ

የበኒ ሻንጉል መስተዳድር ተቃዋሚ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ መሐመድ ኢስማኤል እንደሚሉት በክልሉ ለህዝብ የሚወግንና ህዝባዊ መሰረት ያለው አመራር ባለመኖሩ ዉሕደቱ ለውጥ  ያመጣል የሚል እምነት የላቸዉም፡፡...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሕወሓትና የትግራይ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አንድነትና ልዩነት

አረና ትግራይ ለፍትሕና ለሉዓላዊነት ፓርቲ የኢሕአዴግን መዋሐድ ደግፎ፣ ሕወሓትም ዉሕደቱን መቀበል ነበረበት ብሏል።በቅርቡ ከተመሰረቱት ሁለት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሳልሳዊ ወያኔ የተባለዉ የሕወሓትን አቋም ሲደግፍ፣ የታላቅዋ ትግራይ ብሔራዊ ሸንጎ ወይም ባይቶና ፓርቲ ግን በኢሕአዴግ ዉሕደት ላይ የተፈጠረዉን ልዩነት «አደገኛ» ብሎታል...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኢሕአዴግ ዉሕደትና የሕግ ባለሙያ አስተያየት

ከሕግ ባለሙያዎች መካከል ገሚሶቹ ከእንግዲሕ የሚደረገዉ የዉሕደቱ ሒደት ሕጉን ጠብቆ እንዲከናወን የሚዋሐዱት ፓርቲዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ይመክራሉ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኢሕአዴግ ሲዋሐድ «አካታች የካፒታሊዝም ሥርዓት» ለመፍጠር ማቀዱን አስታወቀ

ኢሕአዴግ ሲዋሐድ የሚመራበት ፕሮግራም ለግንባሩ ምክር ቤት እንዲቀርብ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው መስማማቱን አስታወቀ። የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው አባል አቶ ፍቃዱ ተሰማ እንዳሉት የግንባሩ ሥራ አስፈፃሚ በሁለተኛ ቀን ውሎው ውህድ ፓርቲው በሚኖሩት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና የውጭ ጉዳይ መርሐ-ግብሮች ላይ ውይይት አድርጓል። ...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኢህአዴግ ውህደት፥ በፖለቲካ አመራሮችና በፖለቲካ ምሁራን እይታ!

በአማራ ዴሞክራሲዊ ፓርቲ (አዴፓ) ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብርሀም አለኸኝ እንደገለፁት ውህደቱ ለኢህአዴግ እህት ድርጅቶችና ለአጋር የፖለቲካ አደረጃጀቶች በአገራቸው የፖለቲካ እንቅስቃሴ እኩል የተሳታፊነት ድርሻ ይሰጣቸዋል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ዉይይት፤ ሰላም በኢትዮጵያ እንዴት ይረጋገጥ?

«ወጣቱን መዉቀስ ብቻ ሳይሆን፤ ቆም ብለን ለወጣቱ ምን ያስፈልገዋል ብለን ልናስብ ይገባል። ለምን ወጣቱን ቀረብ ብለን አናወያይም? ለአዛዉንቶች የሚዲያ መድረክ ከምንሰጥ እና ግጭትን ከምናሰፋ ወጣቱን ቀረብ ብለን እናወያይ። ድሕነትና መሐይምነት ሲጋቡ አሁን እኛ ሃገር የሚታየዉን ችግር ወልደዋል። »...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኢሕዴግ የ«ውኅደት» ሒደትና ኦዲፒ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ሊወሀድ ነው መባሉን ተከትሎ ከግንባሩ አባል ድርጅቶች አንዱ በሆነው የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ውስጥ ክፍፍል መፈጠሩ ተሰምቷል። ምንም እንኳን ፓርቲው ያን ቢያስተባብልም። የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ እና አንድ የፖለቲካ ተንታኝን ዶይቸ ቬለ(DW) አነጋግሯል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኢሕአዴግ ጡቃንጡቅ

እንደሚባለዉ ኢሕአዴግ ወደ ዉሁድ ፓርቲነት እንዲለወጥ ከ1996 ጀምሮ በመርሕ ደረጃ ተቀብሎት ሲገፋ የነበረዉ ሕወሓት የጀመረዉ ከግብ ሊደርስ ሲል አሁን የወለፊንድ መቃወሙ ለብዙዎች  አስገራሚ፣ ለሌሎች እንቆቅልሽ ነዉ።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በስጋት ውስጥ የሚገኙት የዩንቨርስቲ ተማሪዎች

ሰሞኑን ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ  አንዳንድ ዩንቨርስቲዎች  የተካሄዱት ብሔር ተኮር ግጭቶች  የተማሪዎች ህይወት እስኪጠፋ የዳረጉ ነበሩ ። አሁን ድረስም የመማር ማስተማር ስራው የተቋረጠባቸው ዮንቨርስቲዎች አሉ። ዮንቨርስቲ ተማሪዎች ስጋታቸውን አካፍለውናል።  ...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከሰሞኑ፦ ግጭት በዩኒቨርስቲዎች፤ የአቃቤ ህግ መግለጫ

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በወልዲያ ዩኒቨርስቲ የተቀሰቀሰው ግጭት እና እርሱን ተከትሎ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የተከሰቱ ሁከቶች እና አለመረጋጋቶች የማህበራዊ መገናኛ ተጠቃሚዎች የሰሞኑ መወያያ ነበሩ። በወልዲያው ግጭት ሁለት ተማሪዎች ማጣታቸው ከተነገረ በኋላ በበርካታ ዩኒቨርስቲዎች መጠነኛ ግጭቶች እና አለመረጋጋቶች ተስተውለዋል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የትግራይ «ራስ-ገዝ» ግዛት መመስረት ሐሳብ ላይ አስተያየት

የህወሓት ፓርቲ ልሳን የሆነው ወይን መፅሔት መጪው ሀገራዊ ምርጫ ሳይካሄድ ከቀረ ቀጥሎ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ፈተናዎች ለማለፍ ትግራይ አብዝሀ የምሉእ መንግሥትነት ቅርፅ የያዘ ግን ደሞ ዓለምአቀፋዊ ተቀባይነት የሌለው (Defacto state) ሆና መቆየት አለባት የሚል ሀሳብ ከትግራይ የተለያዩ አስተያየት እየተሰነዘረበት ነው፡፡...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኢህአፓ በኢትዮጵያ ጠቅላላ ጉባኤ ሊያካሄድ ነው

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አዲስ የአመራር አባላትን መርጦ ሰላማዊ ትግል እያካሄደ እንደሚገኝ አስታውቋል። ፓርቲው በቅርቡ ጠቅላላ ጉባኤ እንደሚያካሄድም ገልጿል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከስራ ተፈናቅለናል ያሉ የሃይማኖት አባቶች አቤቱታ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ስር በተለያዩ ቦታዎች ሲያገለግሉ የቆዩ 217 የሃይማኖት አባቶች ከስራችን አላግባብ ተባርረናል ሲሉ ቅሬታቸውን አሰሙ። የቤተክርስቲያኒቱ ሲኖዶስ እንዲከፈላቸው ወስኖላቸው የነበረው የውዝፍ አበል ጉዳይም ተግባራዊ ባለመደረጉ መቸገራቸውን ገልጸዋል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የማትረሳው የሴቶች መብት ተሟጋች፤ ዶ/ር ቦጋለች ገብሬ

ባለፈው ሳምንት ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይም በደቡባዊ የሀገረቱ ክፍል የሴት ልጅ ግርዛት እንዲቆም ከፍተኛ ተግባራትን ያከናወኑት ዶክተር ቦጋለች ገብሬ ከዚህ ዓለም የመለየታቸው ዜና ተሰምቷል። ዶ/ር ቦጋለች ባቋቋሙት መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት አማካኝነት የአዳጊ ሴቶች ሕይወት እንዳይጨልም ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳደረጉ ይነገርላቸዋል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ለሲኤንኤን የጀግኖች ሽልማት የታጩት ኢትዮጵያዊት

CNN የተሰኘው የአሜሪካ የቴሌቪዥን ጣቢያ የአካባቢያቸውን ማህበረሰቦች ህይወት የሚለውጡ ስራዎችን የሚያከናውኑ ግለሰቦችን በየዓመቱ የሚሸልምበት መርኃ ግብር አለው። የCNN ጀግኖች ለተሰኘው ለዚህ ዕውቅና ዘንድሮ ከታጩ አስር ግለሰቦች መካከል ኢትዮጵያዊቷ ፍረወይኒ መብራህቱ አንዷ ናቸው።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የበርሊን ግንብ የፈረሰበት 30ኛ አመት በጀርመን እየተከበረ ነው

በዛሬው ዕለት በበርሊን ብራንደንቡርግ አደባባይ በመካሔድ ላይ በሚገኘው የመታሰቢያ ሥነ-ሥርዓት የፖላንድ፣ ስሎቫኪያ፣ ቼክ ሪፐብሊክ እና ሐንጋሪ መሪዎች ታድመዋል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከጀርመንን አንድነት ምን እንማራለን?

ጀርመናዉያን ከተዋሃዱ አንድነት ከፈጠሩ በኋላ ያላቸዉ የኤኮኖሚ እድገት እና በዓለም ደረጃ ያላቸዉ ተሰሚነት መጨመሩ ብቻ ሳይሆን ፤ ኑሮአቸዉ የተሻሻለዉ ከተዋሃዱ በኋላ ነዉ። በሰላም መኖር የጀመሩትም፤ የዓለም ስደተኛ ሁሉ ወደ እነሱ መምጣት መፈለግ የጀመረዉ ሁሉ የሚከፋፍላቸዉን ነገር ካስወገዱ በኋላ ነዉ።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የትምህርት ማቋረጥ ስጋት በዋግኽምራ

በአማራ ክልል ዋግኽምራ ብሔረስብ አስተዳደር በአካባቢው ከተከሰተው ድርቅ ጋር ታያይዞ ትምህርት ቤት ምዝገባ ፕሮግራም በቅርብ ካልተጀመረ ትምህርት ሊቋረጥ ይችላል የሚል ስጋት እንዳደረባቸው ተማሪዎችና መምህራን ተናገሩ።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሰላም ሚኒስቴር ችግሮችን ለመፍታት እየሰራሁ ነዉ አለ 

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሰላም ሚኒስቴር እና በስሩ የሚገኙት ተጠሪ ተቋማት ደፈር ያለ ሕግን የማስከበር እርምጃ እንዲወስዱ አሳሰበ።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኦብነግ ጉባኤ በጎዴ

በምሥራቅ ኢትዮጵያ ከ30 ዓመታት በላይ ኦጋዴንን ነጻ ለማውጣት በሚል ነፍጥ በማንሳት ከአዲስ አበባው መንግሥት ጋር በይፋ ሲዋጋ የነበረው የኦጋዴን ነጻነት ግንባር በምህጻሩ ኦብነግ የረዥም አመታት መሪውን ሊቀይር ነው።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የአዳማ ከንቲባ ንግግር የአማርኛ ትርጉም ሲፈተሽ 

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽነር ነው የተባለ እና ሁለት ደቂቃ ከአስራ አምስት ሰከንድ የሚረዝም ንግግር ወደ አማርኛ ተተርጉሞ በማኅበራዊ ድረ-ገፆች በተለይም በፌስቡክ ሲዘዋወር ሰንብቷል። በትንሹ አስራ ስድስት የፌስቡክ ገፆች ላይ የተጫነው ይኸው ንግግር በአፋን ኦሮሞ የተደረገ ሲሆን ወደ አማርኛ የተረጎመው ወገን ማንነት ግን አልተገለጸም። ...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኢትዮጵያ ወዳጁ ታዋቂ ጀርመናዊ ደራሲና ጋዜጠኛ

ኢትዮጵያን ብቸኛዋ የአፍሪቃ ሃገራት ኩራት፤ የአድዋ ድልም ኩራቴ፤ ራሳቸውንም ኢትዮጵያዊ ነኝ ብለዉ ሲናገሩ በኩራት ነዉ። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት በናዚ አገዛዝ ዘመን በረሃብ ተሰቃይተው እንደነበር፤ ምግብን ጠግበዉ በልተዉ እንደማያውቁም ተናግረዋል። ...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የገምሹ በየነ ኩባንያ ሰራተኞች ከመርሐቤቴ መውጣት ጀመሩ

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን መርሐቤቴ ወረዳ ባለፈው እሁድ ጥቃት የተፈጸመበት የግንባታ ኩባንያ ሰራተኞች በመከላከያ ሰራዊት ታጅበው መውጣት መጀመራቸውን ለዶይቼ ቬለ ተናገሩ። ሰራተኞቹ ማሽኖች እና ቡልዶዘሮች ከተቃጠሉበት ጥቃት በኋላ ለቀው ለመውጣት ተቸግረው ነበር።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ መግለጫ

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ መንግሥት ሕግን እንዲያስከብርና የዜጎችን ደህንነት እንዲያስጠብቅ አሳሰበ። ዛሬ የ7ቱም የሃይማኖት ተቋማት የበላይ ጠባቂዎች በተገኙበት በተሰጠው መግለጫ፤ መንግሥት ከንግግር ባለፈ ሕይወታቸው ለተቀጠፈው፣ ጉዳት ለደረሰባቸውና የመቃጠል ችግር ለደረሰባቸው የሃይማኖትና የንግድ ተቋማት ፍትህ ሊሰጥ ይገባል ተብሏል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የአንበጣ መንጋን የመከላከሉ እንቅስቃሴ

የዓለም የምግብ ድርጅት በእንግሊዝኛው ምሕፃር FAO በየጊዜው የአምበጣ መንጋ ከየት አካባቢ ተነስቶ ወደየት እያመራ እንደሆነ የሚያመላክት ትንበያውን በየጊዜው ይሰጣል። ዘንድሮም ከጥቂት ሳምንታት በፊት ድርጅቱ ከየመን የተነሳ የአንበጣ መንጋ ወደ ምሥራቃዊ የኢትዮጵያ ግዛት መትመሙን አመልክቶ ነበር።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ለሰሞኑ የዜጎች ጥቃት ተጠያቂዎች ለሕግ እንዲቀርቡ ጠየቀ

ከሰሞኑ ኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተው የዜጎች ግድያ ፣ የአካል ማጉደል ፣ መፈናቀል ብሎም የሃይማኖት ተቋማት ማውደምና የንብረት ማጋየት ወንጀል ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የተፈጸመበት መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን አመለከተ። ተቋሙ አክሎም በአደባባይ የሕግ የበላይነትን የተገዳደረ ድርጊት መሆኑንም አስታውቋል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የባሌ ሮቤ ከተማ ወቅታዊ ሁኔታ 

የከተማዋ ከንቲባ እና አንድ ሐይማኖታዊ መሪ ግን ተላለፈ የተባለው ትዕዛዝ የባሌን ሕዝብም ሆነ የሮቤን ከተማ አይወክልም ባይ ናቸው። ታምራት ዲንሳ ተጨማሪ ዘገባ አለው። ...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሲዳማ ሕዝበ ዉሳኔ ዝግጅት 

የሲዳማ ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄን ተከትሎ፤ የሚካሄደዉን ሕዝበ ዉሳኔ በሚመለከት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ 5 ሺህ አስመራጮች በፈረቃ ስልጠና በመስጠት ስራዉን መጀመሩ ተነገረ።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በወንጀል የተገኘ ገንዘብን ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብን መከላከል

ኢትዮጵያ ወንጀሉን መቆጣጠር እና መከላከልን አስመልክቶ ክፍተት እንዳለባት ቡድኑ በመገምገሙ በፋይናንስ ድርጊት ግብረ ኃይል ክትትል ድረገጽ ላይ ስሟ ሰፍሮ ነበር።ሆኖም የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል በዚህ ሳምንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳሉት ግብረ ኃይሉ የኢትዮጵያን ሁኔታ በመገምገም ከክትትሉ ሂደት እንድትወጣ ወስኗል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኦሮሞ ፖለቲካ ፓርቲዎች፣እና የሀገር ሽማግሌዎች ጥሪ 

ዛሬ ከሰዓት በኋላ ቦሌ በሚገኘው የጃዋር መኖሪያ ቤት  በጉዳዩ ላይ የተነጋገሩት ፣ጃዋር የተለያዩ የኦሮሞ ፓርቲዎች መሪዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰልፎቹ እንዲቆሙ የተዘጉ መንገዶችም እንዲከፈቱ እና ሰላማዊ ሁኔታ እንዲፈጠር ጥሪ አቅርበዋል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ውጥረት በኦሮሚያ ከተሞች

የኢትዮጵያ መንግሥት የጸጥታ ኃይሎች የኦሮሞ መብት ተሟጋች እና የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ቴሌቪዥን (OMN) ጣቢያ ዋና ዳይሬክተር ጃዋር መሐመድ መኖሪያ ቤት አቅራቢያ ተሰማርተዋል መባሉን ተከትሎ በአብዛኛው የኦሮሚያ ከተሞች ውጥረት ነግሷል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ልዩ ቃለ-ምልልስ ከኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር

የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከዶይቼ ቬለ (DW) ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የደህንነት ባለስልጣኖቻቸው በቂ መረጃ ይሰጧቸው እንዳልነበር ተናግረዋል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የርእሰ-ሊቃነ-ጳጳሳት አቡነ ማትያስ ብርቱ ማሳሰቢያ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳት እና አደጋ አሁንም መቀጠሉን ርእሰ-ሊቃነ-ጳጳሳት አቡነ ማትያስ ተናገሩ። ፓትርያርኩ ዛሬ የተጀመረውን የዓመቱን የሲኖዶስ ምልአተ-ጉባኤ ሲከፍቱ ከውጪ ጣልቃ ገብነትና ከውስጥ ጥቅመኞች የተነሳ ምዕመናንን የመጠበቅ ተግባር ተደጋጋሚ እንቅፋት የበዛበት መኾኑን አስገንዝበዋል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የአዲስ አበባ የዛሬ ውሎ

የኦሮሞ አክቲቪስት እና የኦሮሞ ሚድያ ኔትወርክ ሥራ አስኪያጅ የጀዋር መሐመድ መኖሪያ ቤት ከትናንት ሌሊት አንስቶ እስከ ዛሬ ከእኩለ ቀነ በኋላ ድረስ በወጣት ደጋፊዎቹ ተከቦ ውሎዋል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የለዛ ሽልማት ለኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ተሰጠ

በየዓመቱ በተለይም በፊልምና ሙዚቃ ዘርፍ ሽልማት ከሚሰጡት መካከል አንዱ የሆነውና 9ኛው የለዛ ሽልማት ከ10 በላይ በሆኑ ዘርፎች ሽልማቱን በሳምንቱ አጋማሽ ሰጥቷል። በሽልማት ስነ ስርዓቱ ላይ በቅርቡ ሕይወቱ ያለፈው ሙዚቀኛው ኤልያስ መልካ በእጅጉ ታስቦበታል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በመቐለ ሊካሄድ የነበረ ሰልፍ በፖሊስ ተበተነ

በትግራይ በመቐለ ከተማ ዛሬ ጠዋት ሊያረግ የነበረ ሰልፍ በክልሉ ፖሊስ ተበተነ። “ሰብ ሕድሪ ሲቪክ ማሕበረሰብ ትግራይ” የተሰኘው ድርጅት የጠራው ይህ ሰላማዊ ሰልፍ ከክልላቸው ውጪ የሚማሩ የትግራይ ተወላጅ ተማሪዎች ደህንነትን በተመለከተ ሊደረግ የታሰበ ነበር።  ...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የታከለ ኡማ፤ የህወሃት እንዲሁም የአማራ ክልል የፀጥታ ጉዳይ

«ታከለን ስቃወም ነው የቆየሁት አሁን ሊነሳ ነው ሲባል ደብሮኝ ነበር እንኩዋን ተመለስክ በኢትዮጵያዊነትህ ቀጥልበት የኦነግን አጀንዳ አታራምድ»«የትግራይ ሕዝብ ትልቅ ሕዝብ ነው ፤ ግን እስከመቼ በተወሰኑ ግለሰቦች ሐሳብ እንደሚመራ አይገባኝም»...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ዋግ ኽምራ አፋጣኝ የምግብ ርዳታ ያሻዋል

በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ አስተዳደር ዞን ከ126 ሺህ በላይ ሕዝብ አስቸኳይ የምግብ ርዳታ እንደሚያስፈልገው ተገለጠ። ባለፈው ዓመት በነበረው ዝቅተኛ ዝናብ የተነሳ ከዞኑ ነዋሪዎች ገሚሱ አስቸኳይ ርዳታ የሚያሻው ነው ተብሏል።  አርሶ አደሮች አፋጣኝ መፍትኄ እንዲሰጣቸው ተማጽነዋል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የደምበኞች ቅሬታና የኢትዮ ቴሌኮም ማስጠንቀቂያ

ኢትዮ ቴሌኮም ከኩባንያው ፈቃድ ወስደው የተለያዩ አጫጭር መልዕክቶችን ለቴሌኮሙ ደንበኞች ያለ አግባብ እና ያለ ፍላጎታቸው የሚልኩትን እንደማይታገስ አስጠነቀቀ።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በአማራ ክልል 100 ሚሊዮን ብር የወጣቶች ብድር አልተመለሰም

በአማራ ክልል ለወጣቶች ከተመደበው ሀገራዊ ተዘዋዋሪ ብድር ውስጥ 100 ሚሊዮን ብር ያህሉ ወቅቱን ጠብቆ እንዳልተመለሰ የአማራ ብድር እና ቁጠባ ተቋም ገለጸ። የፌደራል መንግስት ከሰጠው ከዚሁ 2.7 ቢሊዮን ብር ተዘዋዋሪ ብድር ውስጥ ተጨማሪ 500 ሚሊዮን ብር ያህሉም ያለመመለስ ስጋት እንዳለበት ተቋሙ አስታውቋል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News
Follow us on Facebook
Follow us on Facebook