Blog Archives

የአሜሪካ ደኅንነት ‘ዩፎዎችን’ በተመለከተ የሰበሰበውን መረጃ በይፋ አስታወቀ

የአሜሪካ ደኅንነት ስለ ዩፎዎች የሰበሰበውን መረጃ በይፋ አስታወቀ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሴኔጋላዊው የፒኤስጂ ተጫዋች ለተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን ድጋፍ አልሰጠም መባሉ አነጋጋሪ ሆነ

የፒኤስጂው ኢድሪሳ ጋና ጌዬ ለተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪን ድጋፍ ለመግለጽ የቀረበውን መለያ አለብስም ማለቱ አነጋጋሪ ሆነ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በምሥራቅ አፍሪካ በየ48 ሰከንዱ አንድ ሰው በረሃብ የመሞት አደጋ ተጋርጦበታል ተባለ

በድርቅ በተጠቁት ኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ሶማሊያ በየ48 ሰከንዱ አንድ ሰው በረሃብ ሊሞት እንደሚችል ኦክስፋም እና ሴቭ ዘ ቺልድረን ዛሬ ባወጡት ሪፖርት ገለጹ። ጃሚኤል ኦብዘርቫቶሪ ከተሰኘ ድርጅት ጋር በጥምረት የተሠራው ሪፖርት ዓለም ዳግም ከፍተኛ የረሃብ አደጋን ችላ ብሏል ሲል አስጠንቅቋል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አሜሪካ፣ ሰሜን ኮሪያዊ የኮምፒውተር ሊቆች የጎን ውጋት ሆኑብኝ አለች

ማንነታቸውን ደብቀው በአሜሪካ የበይነ መረብ ገበያ ሥራ አመልክተው የሚቀጠሩ የኮምፒወተር ቴክኖሎጂ ብልሆች ለደኅንነቴ ሥጋት ሆነዋል አለች።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኤርትራዊው ብስክሌተኛ ቢንያም ግርማይ ጂሮ ዲኢታሊያ ውድድርን በማሸነፍ የመጀመሪያው አፍሪካዊ ሆነ

የ22 ዓመቱ ኤርትራዊ ማቲው ቫን ደር ፖል የተሰኘውን ተወዳዳሪ የመጨረሻው መስመር አካባቢ በመንደርደር ቀድሞ ነው የውድድሩ አሸናፊ መሆን የቻለው።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ባይደን የነጭ የበላይነት “መርዛማ” ነው ሲሉ ወቀሱ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን በፋሎ በተሰነችው የኒው ዮርክ ክፍለ ግዛት ተገኝተው የነጭ የበላይነትን አወገዙ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከሜክሲኮ ወደ አሜሪካ አደገኛ ዕፅ ማስተላለፊያ ዋሻ ተገኘ

በመጠኑ ገዘፍ ያለና መብራትን ጨምሮ ሁሉ ነገር የተሟላለት ዋሻ ተገኘ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ወግ አጥባቂው የዩኬ የሕዝብ እንደራሴ በመድፈር ተጠርጥረው ታሰሩ

ስማቸው ያልተገለጸ የዩናይትድ ኪንግደም ወግ አጥባቂ የሕዝብ እንደራሴ በመድፈር እንዲሁም ወሲባዊ ትንኮሳ በማድረስ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በአዲስ አበባ ከአሠሪዋ ድብደባ ለማምለጥ ከአራተኛ ፎቅ የወደቀችው የ13 ዓመት ታዳጊ

ገና 13 ዓመቷ ነው። በቤት ሠራተኛነት ከተቀጠረች ውስን ዓመታት መቆጠራቸውን በቅርብ የሚያውቋት ሰዎች ይናገራሉ። ድብደባው እንደማያቋርጥ የተገነዘበችው ብርቱካን ነፍሴን ባድን ብላ ከቤቱ ሮጣ ወጥታ ከአራተኛ ፎቅ ወደ ምድር ተወረወረች። አንድ ሱቅ ጣሪያ ላይ አርፋ ከመሬት ወደቀች። የኮንዶሚኒየሙ ነዋሪዎች ተረባርበው ወደ ጤና ጣቢያ ወሰዷት። አሠሪዋን ደግሞ ለፖሊስ አስረከቡ። ብርቱካን ትባላለች [ለደኅንነቷ ሲባል በመጀመሪያ ስሟ ብቻ እንጠራታለን]። ራሷ ልጅ ብትሆንም የአሠሪዎቿን ልጆች የመንከባከብ ኃላፊነት ወድቆባት ቆይቷል። ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ሰዎች ለቢቢሲ እንደተናገሩት ብርቱካን አትማርም። በአሠሪዎቿ ትንጓጠጣለች። ትሰደባለች። ባስ ሲልም በተደጋጋሚ እንደምትደበደብ ፖሊስም ለቢቢሲ አረጋግጧል። ሚያዝያ 21/2014 ዓ. ም. የደረሰባት ግን ከመቼውም የባሰ ነው። እንግልት የሞላው አጭር ሕይወቷ ከፍ ያለ መከራ ገጠመው። የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ የብርቱካን አሠሪዎች ጎረቤቶች፣ ብርቱካንን በቅርብ የሚያውቋት ሰዎች እና የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የሴቶችና ሕጻናት ጽህፈት ቤት እንደነገሩን በዕለቱ የደረሰባት ይህ ነው። ክስተቱ ሰሚት ኮንዶሚኒየም ውስጥ ነው የተፈጸመው። ረፋድ ላይ አሠሪዋ “ከቤት እቃ ጠፍቷል፤ የት አለ?” ይላታል። ምንም እንደማታውቅ ትናገራለች። አሠሪዋ ግን “አላውቅም” ማለቷን ሳይቀበል ይደበድባት ጀመር። የልጅ አካሏ ከሚችለው በላይ ስትደበደብ ራሷን ሳተች። አሠሪዋ ውሃ ሲያፈስባት ነቃች። ድብደባው እንደማያቋርጥ የተገነዘበችው ብርቱካን ነፍሴን ባድን ብላ ከቤቱ ሮጣ ወጥታ ከአራተኛ ፎቅ ወደ ምድር ተወረወረች። አንድ ሱቅ ጣሪያ ላይ አርፋ ከመሬት ወደቀች። የኮንዶሚኒየሙ ነዋሪዎች ተረባርበው ወደ ጤና ጣቢያ ወሰዷት። አሠሪዋን ደግሞ ለፖሊስ አስረከቡ። ብርቱካን ይህ ዘገባ በወጣበት ወቅት በተወሰነ ደረጃ አገግማለች።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በሰሜን ኢትዮጵያ ሰላም ተመልሶ ቤተሰቦቻቸውን ማግኘት የሚናፍቁት የትግራይ ዳያስፖራዎች

በትግራይ ክልል የማህበራዊ አገልግሎቶች [ስልክ፣ ኢንተርኔት እና ሌሎች] በመቋረጣቸው ምክንያት በርካታ በውጪ አገራት የሚኖሩ የክልሉ ተወላጆች ለከፍተኛ ችግር መጋለጣቸው ይናገራሉ።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ምርጫና ቀጠናዊ አንደምታው

የ30 ዓመታት የእርስ በእርስ ጦርነት ያሽመደመዳት ሶማሊያ በበርካታ ውስጣዊና ውጫዊ ፖለቲካዊ ፍላጎቶች የተወጠረች አገር ናት። በዚያ ላይ ስር የሰደደ ሙስና እንዲሁም የጎሳ ክፍፍል ይንጣታል። አክራሪው ታጣቂ ቡድን አል-ሸባብ ሶማሊያን ከጥግ ጥግ ከማናጋት አልፎ የአፍሪካ ቀንድ ስጋት ከሆነም ሰነባብቷል። ለመሆኑ የሐሰን ሼክ ሞሐሙድ መመረጥ ለሶማሊያ፣ ለአፍሪካ ቀንድ እንዲሁም ለኢትዮጵያ ምን ማለት ...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ያሉበትን ማወቅ እንዳልቻሉ ባለቤታቸው ተናገሩ

ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ አዲስ አበባ ውስጥ ከቤታቸው እንደወጡ አለመመለሳቸውን ባለቤታቸው ወ/ሮ መነን ኃይሌ ለቢቢሲ ገለፁ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኤርትራ ህወሓት ለዳግም ጦርነት እየተዘጋጀ ነው አለች

የኤርትራ መንግሥት ህወሓት ለዳግም ጦርነት በዝግጅት ላይ እንደሆነ በመግለጽ እራሱን ለመከላከል አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ መሆኑን ገለጸ። የኤርትራ መንግሥት በማስታወቂያ ሚኒስቴሩ በኩል ዛሬ ግንቦት 09/2104 ዓ.ም. ባሰፈረው መልዕክት ህወሓት በኤርትራ ድንበር በኩል እና በምዕራብ ትግራይ አቅጣጫ በሁለት ግንባሮች ጦርነት ለመክፈት እየተዘጋጀ ነው ብሏል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በአዲስ አበባና አካባቢዋ ባለፉት 9 ወራት በደረሰ ድንገተኛ አደጋ ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ ውድመት መድረሱ ተገለጸ

በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ድንገተኛ አደጋዎች አጋጥመዋል። በዚህም የሰዎች ሕይወት አልፏል፤ በንብረት ላይም ከፍተኛ ውድመት ደርሷል።ባለፉት 9 ወራት ብቻ በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ በደረሰ የእሳትና ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት የንብረት ውድመት መድረሱ ተገለጸ።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከመጋረጃ ጀርባ የሚካሄደው የሩሲያና የምዕራባውያን ሰላዮች ጦርነት

ከቀዝቃዛው ጦርነት ማብቃት ወዲህ በአሁኑ ወቅት ሩሲያና ምዕራባውያን በስለላው መስክ ትግል ላይ ናቸው። ሩሲያ በዩክሬን ላይ ወረራ ከመክፈቷ ከዓመታት ቀደም ብሎ በተቀናቃኞቿ ግዛት ውስጥ ሰፊ የስለላ መረብ ዘርግታ መረጃ ስትሰበስብ እንዲሁም እርምጃ ስትወስድ እንደቆየች ይነገራል። አሁን ሁለቱ ወገኖች በስለላው መስክ ለይቶላቸው ተፋጠዋል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በደቡብ አፍሪካ ነጭ ተማሪ የጥቁር ተማሪ ንብረት ላይ መሽናቱ እያነጋገረ ነው

በደቡብ አፍሪካ ነጭ ተማሪ የጥቁር ተማሪ ንብረት ላይ መሽናቱ እያነጋገረ ነው
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በሶማሊያ ለሁለተኛ ጊዜ ፕሬዝዳንት የሆኑት ሐሰን ሼይክ ሞሐሙድ ማን ናቸው?

አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼይክ ሞሐሙድ ሥልጣነ መንበር ሲጨብጡ የመጀመሪያቸው አይደለም። እአአ ከ2012 እስከ 2017 የሶማሊያ ስምንተኛው ፕሬዝዳንት ነበሩ። በ2017 በድጋሚ ሲወዳደሩ ግን የቀድሞው ፕሬዝዳንት ሞሐመድ አብዱላሂ ፈርማጆ ረቷቸው።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ፕሪሚየር ሊግ፡ ማን ዋንጫ ያነሳል? ማንስ ከሊጉ ይወርዳል?

በሊጉ 15 ጨዋታዎች ይቀራሉ። ለዋንጫ ከሚደረገው ፉክክር በተጨማሪ በአውሮፓ ደረጃ የሚወዳደሩ እና ከሊጉ የሚወርዱ ቡድኖች ተለይተው አላለቁም። ሊጉ በምን መልኩ ሊጠናቀቅ ይችላል?...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የጉሮሮ ካንሰር ለምን የአርሲ እና የባሌ አካባቢ ማህኅረሰብን በተለየ ያጠቃል?

ምንም እንኳ እርግጠኛው የጉሮሮ ካንሰር መነሻ ምክንያቶች እነዚህ ናቸው ተብሎ ባይበየኑም፣ በበርካታ አገራት የአልኮል መጠጥን የሚያዘወትሩ፣ በሲጋራ ሱስ የተጠመዱ ሰዎች በጉሮሮ ካንሰር እንደሚጠቁ ጥናቶች ያሳያሉ። በተጨማሪም የሚፋጁ ምግቦች እና መጠጦችን የሚያዘወትሩ ለጉሮሮ ካንሰር የመጋለጥ ዕድላቸው ሰፊ መሆኑን እነዚህ ጥናቶች ጠቁመዋል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አባትና ልጅ ከ58 ዓመታት በኋላ በፌስቡክ አማካኝነት ተገናኙ

ጁሊ ሉንድ ከ58 ዓመታት በኋላ አባቷን አግኝታለች። ጁሊ አብዛኛውን ዕድሜዋን ያሳለፈችው አባቷን በመፈለግ ነው።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሐሰን ሼይክ መሐመድ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ

የቀድሞ የሶማሊያ ፕሬዝደንት የነበሩት ሐሰን ሼይክ መሐመድ ዳግም ፕሬዝደንት ሆነው ተመረጡ። አዲሱ ተመራጭ ሐሰን ሼይክ መሐመድ እአአ ከ2012-2017 የሶማሊያ 8ኛው ፕሬዝደንት በመሆን አገልግለዋል። ተመራጩ ፕሬዝዳንት ተቀናቃኛቸውን ተሰናባች ፕሬዝዳንት መሐመድ ፋርማጆን ከፍተኛ ድምጽ በማግኘት አሸንፈዋል፡፡...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ፊንላንድ እና ሰዊድን ታሪካዊ በተባለ ውሳኔ በይፋ ኔቶን እንቀላቀላለን አሉ

ሩሲያ ዩክሬንን ከወረረች በኋላ ስዊድንና ፊልናድ ታሪካዊ በተባለው ውሳኔያቸው የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን (ኔቶ) ለመቀላቀል መወሰናቸውን ይፋ አድርገዋል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አሜሪካዊው ታጣቂ ጥቁሮችን ብቻ ነጥሎ ጥቃት መፈፀሙ ተሰማ

በኒው ዮርክ ግዛት በፋሎ ከተማ አንድ ነጭ ታጣቂ ጥቁሮች የሚበረክቱበት መገበያያ ሥፍራ ገብቶ ጥቃቱ መፈፀሙ ተሰምቷል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሕዝቡ የማይመርጥበት የሶማሊያው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ

ሶማሊያ ለረጅም ጊዜ የተጓተተውን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዛሬ እሁድ ግንቦት 07/2014 ዓ.ም. ታካሂዳለች። ይህም መጀመሪያ ሊደረግ ከታቀደው ከአንድ ዓመት በላይ ዘግይቶ ነው።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኢሰመኮ በሰሜን ኢትዮጵያ ውጥረት እየጨመረ መምጣቱ እንዳሳሰበው ገለጸ

በትግራይ ክልልና በፌደራል መንግሥት ኃይሎች መካከል ውጥረት እየጨመረ መምጣቱ እንዲሁም አልፎ አልፎም ግጭቶች ሪፖርት መደረጋቸው እንዳሳሰበው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጸ።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

መንግሥት በኦሮሚያ ባለው ታጣቂ ቡድን ላይ ጠንካራ ወታደራዊ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ገለጸ

የመንግሥት ኃይል በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች በሚንቀሳቀሰው ታጣቂ ቡድን ላይ የተጠናከረ ወታደራዊ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከጨረቃ በተወሰደ አፈር ለመጀመሪያ ጊዜ ተክሎችን ማብቀል ተቻለ

ሳይንቲስቶች ከጨረቃ በተገኘ አፈር ተክሎችን ለመጀመሪያ ጊዜ ማብቀል ችለዋል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሩሲያ ጎረቤቴ ፊንላንድ ኔቶን ከተቀላቀለች የአጸፋ ርምጃ እወስዳለሁ ስትል ዛተች

ሩሲያ ጎረቤት አገር ፊንላንድ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅትን (ኔቶ) ከተቀላቀለች "የአጸፋ ርምጃዎችን" እወስዳለሁ ስትል ዛተች።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ጦርነት ሊቀሰቀስ ይሆን?

ላለፉት 17 ወራት በጦርነት ሲናጥ የነበረው የሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢ የትግራይ ኃይሎች ከአፋር ወጥተናል ማለታቸውን ተከትሎ መረጋጋት ያሳየ ቢመስልም ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ዳግም ግጭቶች ሊያገርሹ እንደሚችሉ እየታዩ ነው። የትግራይ ኃይሎች ከኤርትራ ጋር አዋሳኝ በሆኑት አካባቢዎች ላይ የከባድ መሳሪያ ጥቃት ከፍተው ለአጭር ጊዜ የቆየ ወታደራዊ ግጭት መካሄዱን ቢቢሲ ከምንጮቹ አረጋግጧል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን የዘ ኢኮኖሚስት ዘጋቢን ፈቃድ ሰረዘ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን በኢትዮጵያ የዘ ኢኮኖሚስት ጋዜጣ ዘጋቢ የሆነውን ቶም ጋርድነር ፈቃድ መሰረዙን አስታወቀ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ወላጆች የልጅ ልጅ አላሳየንም ያሉትን ልጃቸውን ከሰሱ

በሰሜን ህንድ በምትገኘው የኡታራካንድ ግዛት የሚኖሩ ሕንዳዊያን አያቶች የልጅ ልጅ አልወለደልንም ሲሉ ብቸኛ ልጃቸውን እና ሚስቱን ፍርድ ቤት ገተሩ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ፕሬዚዳንት ሼክ ካሊፋ በ73 አመታቸው አረፉ

በአለም ላይ ካሉት ከናጠጡ ንጉሶች አንዱ የሆኑት የአረብ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ፕሬዝዳንት ሼክ ካሊፋ ቢን ዛይድ አል ናህያን በ73 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኬንያዊቷ ነርስ በዓለም አቀፍ ውድድር አሸንፋ 250 ሺህ ዶላር ተሸለመች

ኬንያዊቷ ነርስ የዓለም አቀፉን የነርሶች ሽልማት ውድድርን በማሸነፍ 250 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ተበረከተላት። በሰሜን ኬንያ መርሳቢት በሚገኘው ሆስፒታል የምትሰራው ነርስ ቀበሌ (Qabale) ዱባ ይህን ሽልማት ያሸነፈችው በምትኖርበት ማኅብረሰብ የሴት ልጅ ግርዛትን ለማስቆም ባደረገችው ጥረት ነው።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የተመድ ዋና ጸሃፊ በአልጀዚራዋ ጋዜጠኛ ግድያ መደንገጣቸውን ተናገሩ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ትላንት ረቡዕ በአንጋፋዋ ፍልስጤም-አሜሪካዊ የአልጀዚራ ጋዜጠኛ ሺሪን አቡ አቅላ ላይ የተፈጸመው ግድያ "አስደንጋጭ ነው" ብለዋል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

‘በተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖች ከዓለም ዓይን የተሰወረ ጦርነት እየተካሄደ ይገኛል’ ኦፌኮ

በተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖች ከዓለም ዓይን የተሰወረ ጦርነት እየተካሄደ የሰው ህይወት እየጠፋ ነው ሲል የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ዛሬ ግንንቦት 04/2014 ዓ.ም. አዲስ አበባ ውስጥ በሰጠው መግለጫ አመለከተ።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በአልቢኖ ግድያ የተሳተፉ ሦስት ግለሰቦች እያንዳንዳቸው የ155 ዓመት እስራት ተበየነባቸው

የማላዊ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አልቢኖ ያለበትን ግለሰብ የገደሉ ሦስት ሰዎችን እያንዳንዳቸውን በ155 ዓመት እስራት ቀጣ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የጉግል መተርጎሚያ በትግርኛና ኦሮምኛ ቋንቋዎች አገልግሎት ሊጀምር ነው

ግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጉግል ትግርኛና ኦሮምኛን ጨምሮ ከ300 ሚሊዮን በላይ የሚናገራቸውን 24 አዳዲስ ቋንቋዎች በጉግል መተርጎሚያ ዝርዝሩ ውስጥ አካቷቸዋል።በኢትዮጵያ እና በኬንያ ወደ 37 ሚሊዮን የሚጠጉ ነዋሪዎች ኦሮምኛን የሚናገሩ ሲሆን ስምንት ሚሊዮን የሚጠጉ የኤርትራና የትግራይ ተወላጆች ትግርኛን ይናገራሉ።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሶስት ሴቶችን የገደለው ወንጀለኛ ማረሚያ ቤት ውስጥ ማግባት እንደሚፈልግ ገለጸ

ወንጀለኛው ማርሻ ማኮኔል፣ ኤምሊ ዴላግራንዴ እና ሚሊ ዶውለር የተባሉ ሴቶችን በጭካኔ በመግደል ጥፋተኛ ተብሎ ሁለት የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደበት ነበር።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በሶማሌ ክልል በባህላዊ የምርጫ ሥነ ሥርዓት ላይ በፀጥታ ኃይሎች የተፈጸመውን ግድያ ኢሰመኮ ኮነነ

በሶማሌ ክልል ቦምባስ ከተማ በባህላዊ ሥነ ሥርዓት የጎሳ መሪ ለመምረጥ በተሰበሰቡ ሰዎች ላይ በፀጥታ ኃይሎችና በታጠቁ ግለሰቦች በተፈጸሙ ጥቃቶች የ11 ሰዎች ህይወት መጥፋቱን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ኮነነ።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኢትዮጵውያንን እየፈተነ ያለው የኑሮ ውድነት መፍትሄው ምን ይሆን?

በኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት የዋጋ ግሽበት በተከታታይ ጭማሪ ሲያሳይ ቆይቷል። በተለይም ኀብረተሰቡ በዕለት ተዕለት በሚጠቀምባቸው መሰረታዊ ፍጆታዎች፣ በግንባታ እቃዎችና በሌሎች ላይ እየታየ ያለው የዋጋ ንረት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የዜጎችን ህይወት እጅግ እየተፈታተነው ይገኛል። የምጣኔ ባለሙያዎችም እርምጃ ካልተወሰደ መዘዙ ብዙ እንደሆነ አበክረው እየተናገሩ ነው።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አብርሮ የማያውቀው ተሳፋሪ ፓይለቱ የታመመበትን አውሮፕላን በሰላም አሳረፈ

በአሜሪካዋ ፍሎሪዳ ግዛት አብራሪው መታመሙን ተከትሎ አንዲት አውሮፕላንን ያለምንም ችግር ማሳረፍ የቻለው ተሳፋሪ በበርካታ መገናኛ ብዙኃን መነጋገሪያ ሆኗል። ማንነቱን ለማጣራትም የዜና ወኪሎች ፍለጋ ላይ መሆናቸውም ተሰምቷል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኮቪድ -19፡ ሰሜን ኮሪያ የኮቪድ ወረርሽኝ በመከሰቱ ጥብቅ የእንቅስቃሴ ገደብ እንዲጣል አዘዘች

ሰሜን ኮሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ በይፋ በኮቪድ የተያዙ ሰዎች መገኘታቸውን ተከትሎ ጥብቅ ብሔራዊ የእንቅስቃሴ ገደብ እንዲጣል አዘዘች።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በኋላ ወደ ሥራ ቦታ መመለስና ፈተናዎቹ

ከሁለት ዓመት በኋላ በርካታ የዓለማችን ድርጅቶች ሠራተኞቻቸው በየቤታቸው ከመስራት ወደ ቢሮ ስለመመለስ እንዲያስቡ እያደረጉ ነው። አብዛኞቹም ወደ ሥራ ቦታቸው መመለስ ጀምረዋል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የወር አበባ እረፍት ዘግይቶም ቢሆን ተቀባይነት እያገኘ ይሆን?

ሁንም ድረስ እንደ አሜሪካ ባሉ ባደጉት አገራት ጭምር እንኳን ሴቶች ወር አበባቸውን ሲያዩ እረፍት እንዲወጡ አልያም ከቤታቸው እንዲሰሩ የሚያደርጉ ሕጎች እምብዛም አይስተዋሉም።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሪሃና የፌንቲ የውበት መጠበቂያ ምርቶቿን በአፍሪካ ልታቀርብ ነው

ሪሃና ፌንቲ ቢውቲ እና ፌንቲ ስኪን የተባሉ የውበት መጠበቂያ ምርቶቿን ከዚህ ወር መጨረሻ ጀምሮ በስምንት የአፍሪካ ሃገራት እንደሚቀርቡ አስታውቃለች።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የአል ጀዚራ ጋዜጠኛ ዌስት ባንክ ውስጥ በእስራኤል ጦር ተገደለች

ትውልደ ፍልስጤማዊ እና የአሜሪካ ዜግነት ያላት የዓለም አቀፉ የመገናኛ ብዙኃን ተቋም፣ አል ጀዚራ ጋዜጠኛ በወረራ በተያዘው ዌስት ባንክ ጄኒን ውስጥ በእስራኤል ኃይሎች ተተኩሶባት ተገለደለች።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ተደራራቢው የኢትዮጵያ ሴት ጋዜጠኞች ጭቆና

ቢቢሲ ለዚህ ዘገባ ያነጋገራቸው ሴት ጋዜጠኞች በተለይም የጋዜጠኝነት ሥራ በጀመሩባቸው የመጀመሪያ ግዜያት የተለያዩ ማባበያዎችን በማቅረብ፤ ባስ ሲልም ማስፈራሪያ እና ጉልበት በመጠቀም አካላዊ ጥቃቶች በሥራ ቦታቸው አጋጥሟቸዋል። ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች በመገናኛ ብዙኃን ውስጥ ስር መስደዳቸውን እና የተለመደ የየቀን ሕይወት አካል መሆኑን ሴት ጋዜጠኞቹ ይናገራሉ። እነዚህ ጥቃቶች ኢኮኖሚያዊ መልክ...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከታራሚ ጋር ተያይዛ የጠፋችው የማረሚያ ቤት ፖሊስ ራሷን በጥይት አጠፋች

በግድያ ወንጀል ከተጠረጠረ ታራሚ ጋር ጠፍታ የነበረችው የማረሚያ ቤት ፖሊስ ራሷን ተኩሳ መግደሏን ፖሊስ አስታወቀ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በኢትዮጵያ በምግብ ነክ ሸቀጦች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት መመዝገቡ ተገለጸ

በኢትዮጵያ በምግብ ነክ ሸቀጦች ላይ ከፍተኛው የዋጋ ግሽበት እየተመዘገበ መሆኑን ያለው የአገሪቱ ብሔራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ምክር ቤት ገለጸ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ተይዞ ስለቆየበት ሁኔታ በዝርዝር ተናገረ

ከአንድ ሳምንት በላይ ደብዛው ጠፍቶ የነበረው ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ፤ ከመኖሪያ ቤቱ 'የተደራጀ የሕገ-ወጥ ቡድን' በሚመስል አካል ከተያዘ በኋላ ጦር ኃይሎች አካባቢ ባለ 'የድሮ ቤት' ውስጥ ሳያቆዩኝ አይቀርም አለ።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የጦር ወንጀል ማስረጃ እንዲጠፋ ተባብሯል መባሉን አጣጣለ

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በምዕራብ ትግራይ የትግራይ ተወላጆች በጅምላ መቀበራቸውን የሚያሳይ የጦር ወንጀል ለመደበቅ የአማራ ሚሊሻዎችን ረድቷል የሚለውን ሪፖርት አጣጣለ።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በተባበሩት መንግሥታት የሚመራው የሱዳን ድርድር ተቃውሞ ገጠመው

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሚመራው የሱዳን የፖለቲካ ፓርቲዎች ሁለተኛ ዙር ድርድር በዛሬው ዕለት እንዲጀመር እቅድ የተያዘለት ቢሆንም መከፋፈሎች አጋጥመዋል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ቴክኖሎጂ፡ የሞባይል ኔትዎርክ የመጨረሻው ቴክኖሎጂ 5ጂ ለኢትዮጵያ ምን ይፈይዳል?

አምስተኛው ትውልድ ወይም 5ጂ ዓለም የደረሰበት የመጨረሻው ፈጣን የሞባይል ኔትዎርክ ቴክኖሎጂ ነው። "የመጨረሻው ፈጣን" ማለት 2 ሰዓት የሚፈጅ ፊልምን በሰከንዶች ውስጥ ማውረድ [ዳውን ሎድ] ማድረግ የሚያስችል ነው። ትናንት በኢትዮጵያ ወደ ሥራ የገባው ይህ ቴክኖሎጂ፣ ለቅድመ ገበያ [ለማስተዋወቅ] በአዲስ አበባ በተመረጡ አካባቢዎች ላይ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የዩክሬን የአውሮፓ ህብረት አባል የመሆን ጥያቄ አስርት አመታትን ይወስዳል ተባለ

ዩክሬን የአውሮፓ ህብረት አባል ለመሆን ያቀረበችው ጥያቄ አስርት አመታትን እንደሚወስድ የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አስታወቁ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

‘ሲጨንቀን ከሐኪም የማይጠበቅ ምክር እንሰጣለን’ – በዓይደር ሆስፒታል የካንሰር ሕክምና ባለሙያ

ለ17 ወራት በቀጠለው ጦርነት ምክንያት በክልሉ የሚገኙ የካንሰር ህሙማን ከባድ ችግር ላይ ወድቀው ከሚገኙ ታካሚዎች መካከል ይጠቀሳሉ። ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ ባሉ ጊዜያት 1643 አዋቂዎች እና 126 ህጻናት የካንሰር ታካሚዎች ወደ ሆስፒታሉ መምጣታቸው የሚያሳየው የሆስፒታሉ ሪፖርት፣ አብዛኛዎቹ ግን በትራንስፖርት ችግር፣ በገንዘብ ማጣት እና የስልክ አገልግሎት ባለመኖሩ ምክንያት መጥተው ህክምና ማግ...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

“ከደረሰብኝ ጥቃት አንፃር ልጄን ሌላ ሰው ወስዶት ስለእናቱ ታሪክ ሳያውቅ እንዲያድግ እመኛለሁ”

“ከደረሰብኝ ጥቃት አንፃር ልጄን ሌላ ሰው ወስዶት ስለእናቱ ታሪክ ሳያውቅ እንዲያድግ እመኛለሁ"
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በኢትዮጵያ ከሰሞኑ በተከሰቱ የሃይማኖት ግጭቶች ላይ ገለልተኛ ምርመራ እንዲደረግ ተመድ ጠየቀ

በኢትዮጵያ በቅርቡ በተከሰቱ የሃይማኖት ግጭቶች ላይ መንግሥት ገለልተኛ፣ ግልፅና ጥልቅ ምርመራ እንዲደረግ የተባበሩት መንግሥታት ድርጀት ጠየቀ። ከሰሞኑ በሙስሊሞችና በኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች መካከል በተፈጠሩ ግጭቶች የሰዎች ህይወት መቀጠፍና የአካል ጉዳቶች መድረሱ በእጅጉ እንዳሳዘናቸው የተመድ የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚሼል ባችሌት ገልጸዋል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ዛሬ በኢትዮጵያ ተግባራዊ የሚሆነው የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ከባለፈው ጋር ሲነጻጸር ምን ያህል ጭማሪ አሳየ?

የንግድ እና ቀጠናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ መናሩን በምክንያትነት በመጥቀስ ከአራት ወራት በፊት ባወጣው የዋጋ ተመን ላይ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ማሻሻያ ማድረጉን አሳስታውቋል።መንግሥት ባለፉት አራት ወራት የነዳጅ ዋጋን ለመደጎም ባወጣው ወጪ ከፍተኛ ጫና ላይ መውደቁንም አትቷል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

“የእንግሊዝ መንግሥት ወደ አምባገነኗ ሩዋንዳ ይልከኝ ይሆን? “ ኤርትራዊው ታዳጊ

ለቢቢሲ ፎከስ ኦን አፍሪካ ፕሮግራም ወደ ካሌ ከተማ ሳቀና ስደተኞች በሚበዙባት በዚህች የወደብ ከተማ ቁማር ቤት አያለሁ ብዬ አልጠበቅኩም ነበር።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በኢትዮጵያ የጦር ወንጀል ማስረጃዎች እንዲጠፉ እየተደረገ መሆኑን የዓይን እማኞች ተናገሩ

በምዕራብ ትግራይ ውስጥ የተፈጸመ የዘር ማጽዳትን ለመሸፈን በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አስክሬን እየተቃጠለ እንደሆነ የዓይን እማኞች ተናገሩ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አንሶላችንን መቀየር ያለብን በምን ያህል ቀናት ልዩነት መሆን አለበት?

ነገሩ በአደባባይ አይወራም የሚሉ ብዙ ናቸው። ግን የአንሶላ ቅያሪ ጉዳይ የሁላችንንም ደጅ ያንኳኳል። ብዙዎች በምን ያህል ቀናት አንሶላ ይቀየር? በሚለው ቁጥር ላይ አይስማሙም። እርስዎ ግን በምን ያክል ጊዜ አንሶላ ያጥባሉ?...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በሩስያ ጦር በተከበበው ብረት ፋብሪካ ውስጥ ተሸሽገው የነበሩ ሲቪል ሰዎች መውጣታቸው ተገለጸ

በዩክሬን ማሪዮፖል ከተማ በሩሲያ ጦር በተከበበው የአዞቭስታል ብረት ፍብሪካ ውስጥ ተሸሽገው የነበሩ አዛውንቶች፣ ሴቶችና ህጻናት ፍብሪካውን ለቀው መውጣታቸውን ሩሲያና ዩክሬን አስታውቀዋል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከአራስ እስከ 114 ዓመት ዕድሜ የኮቪድ-19 ሕሙማንን ያከመው የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ውለታ

በሺዎች የሚቆጠሩ ሕሙማንን ተቀብሎ ያስተናገደው ሆስፒታሉ፣ ባለፈው ሐሙስ በእንክብካቤው ስር የነበሩት ብቸኛ ታካሚ አገግመው ወደ ቤታቸው መሄዳቸውን አሳውቋል። የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ያሬድ አግደው ለቢቢሲ እንደተናገሩት፣ ታካሚው አገግመው ወደ ቤታቸው በመሸኘታቸው ላለፉት ሁለት ዓመታት በአገሪቱ የኮቪድ-19 የሕክምና ማዕከል ሆኖ አገልግሎት በመስጠት ላይ ያለው ሆስፒታል ለመጀመሪ...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኢትዮጵያ ውስጥ ‘ለመዝናናት’ የሚደረግ አደን አለ? እንዴትስ ይከናወናል?

የዱር እንስሳትን በሕጋዊም ሆነ በሕገ-ወጥ መልኩ አድኖ መያዝ ወይም ለምግብነት ማዋል ለረዥም ዓመታት ከሰው ልጅ ጋር የዘለቀ ተግባር ነው።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በዋጋ የማይተመነው የሮማ ጥንታዊ ቅርጽ በቴክሳስ ያገለገሉ እቃዎች መሸጫ ሱቅ እንዴት ተገኘ?

ላውራ ያንግ በኦስቲን ቴክሳስ ወደሚገኝ ያገለገሉ እቃዎች መሸጫ ሱቅ ጉድዊል ጎራ ያለችው እአአ በ2018 ነበር። ወደ ሱቁ ስታመራ ጥሩ እቃ አገኛለሁ ብላ ነበር።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ለመጀመሪያ ጊዜ ለዋይት ሀውስ ጥቁር ሴት ቃል አቀባይ ተሾመች

ካሪን ጃንፒሬ የመጀመሪያዋ ጥቁር፣ ሴት፣ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ቃል አቀባይ ሆና በፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ተሰይማለች።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሰላም እንዲወርድ የሩሲያ ኃይሎች ከዩክሬን መውጣት እንዳለባቸው ዘለንስኪ ተናገሩ

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ከሩሲያ ጋር ሰላም እንዲወርድ የሩሲያ ኃይሎች በዩክሬን ከያዟቸውን ቦታዎች መልቀቅ እንዳለባቸው ተናገሩ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ቼልሲ ቡድኑን ለአሜሪካው ባለሃብት ቶድ ቦህሊ ለመሸጥ ስምምነት ላይ ደረሰ

የቼልሲ እግር ኳስ ክለብ፣ በአሜሪካ ሎስ አንጀለስ በሚገኘውና የቤዝቦል ቡድን አንዱ ባለቤት በሆኑት ቶድ ቦህሊ ለሚመራው ጥምረት 5.2 ቢሊየን ዶላር ለመሸጥ የሚያስችል ስምምነት ላይ መድረሱ ተገለጸ።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በኩባ ዋና ከተማ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል በደረሰ ከባድ ፍንዳታ 22 ሰዎች ሞቱ

ኩባ፣ ሐቫና ውስጥ በሚገኝ ሆቴል ውስጥ የተነሳውን ፍንዳታ ተከትሎ ቢያንስ 22 ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ናይጄሪያዊው ፓስተር “ወደ መንግሥተ ሰማያት” ለመውሰድ 700 ዶላር እያስከፈሉ ነው በሚል ተከሰሱ

ናይጄሪያዊው ኢቫንጀሊካን ፓስተር ተከታዮቻቸው ገንዘብ ከከፈሉ ወደ መንግሥተ ሰማያት ወደሚያደርሳቸው በር እንደሚመሯቸው ከተናገሩ በኋላ ችግር ገጥሟቸዋል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

“ከደረሰብኝ ጥቃት አንፃር ልጄን ሌላ ሰው ወስዶት ስለእናቱ ታሪክ ሳያውቅ እንዲያድግ እመኛለሁ”

በወ/ሮ ዘሃራ በህወሓት ወታደሮች በርካታ ጾታዊ ጥቃቶች እንደተፈፀሙባት ትናገራለች። ወይዘሮ ዘሃራ ይህንን እና ሌሎች ታሪኮቿን ከቢቢሲ ጋር በነበራት ቆይታ አጋርታለች።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኮቪድ-19፡ በመላው ዓለም በኮቪድ የሞቱ ሰዎች ትክክለኛው ቁጥር 15 ሚሊዮን እንደሚጠጋ ተገለጸ

የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን በዓለም ዙሪያ 15 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን ሕይወት መቅጠፉን የዓለም ጤና ድርጅት ግምት አመለከተ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ምጣኔ ሃብት፡ በቱርክ የኑሮ ውድነት 70 በመቶ ገደማ መጨመሩ ተገለጸ

በቱርክ የኑሮ ውድነት በአንድ ዓመት ውስጥ 70 በመቶ ገደማ መጨመሩ ተገለጸ። ይህም በሁለት አስርት ዓመታት ውስጥ ከፍተኛው ነው ተብሏል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በአንዴ ዘጠኝ ሆኖ በመወለድ የመጀመሪያ የሆኑት ልጆች አንደኛ ዓመታቸውን አከበሩ

በዓለም ብቸኛ የሆኑት ዘጠኝ ልጆች አንደኛ ዓመታቸውን እንዳከበሩና መልካም ጤና ላይ እንደሚገኙ አባታቸው ለቢቢሲ ገለጸ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሩሲያ በዩክሬን እየተካሄደ ያለው ‘ልዩ ወታደራዊ ኦፕሬሽን’ ነው በሚለው አቋማ ጸናች

ሩሲያ በዩክሬን እየሆነ ያለው 'ጦርነት' ሳይሆን 'ልዩ ወታደራዊ ኦፕሬሽን' ነው አለች
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በኢትዮጵያ የጠፋ መድኃኒት የሚያፈላልገው መተግበሪያ

"ጤናዎ" የሞባይል መተግበሪያ የጤና ጥበቃ ከፍተኛ ተጠሪ በተገኙበት በሸራተን አዲስ የተመረቀው ከወራት በፊት ነበር፡፡ በአጭሩ ለማስቀመጥ ደንበኛው የሚፈልገው መድኃኒት የት እንዳለ ይጠቁመዋል፡፡ ይህን የሚያደርገው በስልክ መተግበሪያ በመጠቀም ነው፡፡ መጀመርያ ለደንበኛው፣ ካለበት በ500 ሜትር ራዲየስ ያሉ መድኃኒት ቤቶችን ያሳየዋል፡፡ ወይም ደግሞ መድኃኒት ፈላጊዋ ካለችበት ሆና በከተማው ያሉ መድ...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በአሜሪካ ተያይዘው የጠፉት እስረኛና የማረሚያ ቤት ፖሊስ ‘ልዩ ግንኙነት’ ነበራቸው ተባለ

በአሜሪካ አላባማ ግዛት ያመለጠው እስረኛ እና እንዲያመልጥ ረድተዋለች ተብላ የተጠረጠረችው የማረሚያ ቤት ፖሊስ "ልዩ ግንኙነት" እንደነበራቸው መርማሪዎች ተናገሩ።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ፑቲን ምዕራባውያን ዩክሬንን ማስታጠቅ እንዲያቆሙ ለማክሮን ነገሩ

የሩሲያ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ምዕራባውያኑ ዩክሬንን ማስታጠቅ እንዲያቆም ለፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን ተናግሩ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሂውማን ራይትስ ዎች የሩሲያ ቅጥረኛ ወታደሮች በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ግፍ ፈፅመዋል አለ

የሩሲያ ቅጥረኛ ወታደሮች በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ሰላማዊ ሰዎች በመግደል፣በማሰቃየትና በመደብደብ ተከሰሱ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ህወሓት ለመዝመት ፍቃደኛ ያልሆኑ ልጆች ወላጆችን እያሰረ መሆኑ ተነገረ

ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ጦርነት ውስጥ የገባው ህወሓት እየተካሄደ ባለው ጦርነት ልጆቻቸው ያልዘመቱ ወላጆችን እያሰረ እንደሚገኝ የቤተሰብ አባላት ለቢቢሲ ተናግሩ። ህወሓት በበኩሉ ከዚህ በፊት ልጆች ለምን አልዘመቱም በሚል ወላጆችን የማሰር ምልክቶች ቢኖሩም አሁን ላይ ግን ይህ ቆሟል ይላል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር በምትዋሰንበት ድንበር አካባቢ በርካታ የፀጥታ ኃይል አሰማራች

ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር በምትዋሰንበት ድንበር አቅራቢያ በምትገኘው የማርሳቢት ግዛቷ ውስጥ በተቀሰቀሰ የጎሳ ግጭት ምክንያት በርካታ ሰዎች መገዳላቸውን ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ ፖሊሶች እና የፀጥታ ኃይሎች መሰማራታቸው ተገለጸ።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በህንድ በቡድን ተደፍራ ሪፖርት ልታደርግ የሄደችውን ታዳጊ ፖሊስ ደፍሯል መባሉ ቁጣ አስነሳ

በህንድ ኡታር ፕራዴሽ ግዛት በቡድን የተደፈረች አንዲት የ13 ዓመት ታዳጊ ሪፖርት ልታደርግ ወደ ፖሊስ ጣቢያ በሄደችበት ወቅት በፖሊስ ተደፍራለች መባሉ ቁጣን ቀስቅሷል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሰሜኑ ጦርነት ሃሳብን በመግለጽ ነጻነት ላይ ያሳደረው ጫና ምን ይመስላል?

በዛሬው ዕለት በምትከበረው የዓለም የፕሬስ የነፃነት ቀን ለረጅም ጊዜ በዘለቀ የርስ በርስ ጦርነት ሚሊዮኖች ያለ እርዳታና መረጃ እንዳያገኙ ባለበት ሁኔታ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ትኩረት ከሚደረግባቸው አገራት አንዷ ሆናለች።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ በማን እና የት እንደታሰረ ማወቅ እንዳልተቻለ ጠበቃው ተናገሩ

ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ያለበት ቦታ ሳይታወቅ ቀናት መቆጠራቸው እንዳሳሰባቸው ጠበቃው ተናገሩ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኬንያው ፕሬዚደንት ምክትላቸው ሥልጣን እንዲለቁ ጠየቁ

የኬንያ ፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታ ምክትላቸው ዊሊያም ሩቶ ከሥልጣናቸው እንዲለቁ ጠየቁ።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አንድ እግሯን በካንሰር ያጣችው ሯጭ የማራቶን ክብረ ወሰንን ሰበረች

ግራ እግሯን በካንሰር ካጣች በኋላ መሮጥ የጀመረችው ጃኪ ሃንት 104 ተከታታይ የማራቶን ውድድሮችን በ104 ቀናት በመሮጥ የጊነስ የአለም የተከታታይ ማራቶን ክብረ ወሰንን እንዳለፈች ተነግሯል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በዛሬው የአዲስ አበባ ግርግር ከ10 ወር ሕጻን ጀምሮ የጠፉ ልጆችን እያገናኙ ያሉት ወጣቶች

ዛሬ ሚያዝያ 24/2014 ዓ. ም. በአዲስ አበባ የኢድ ሶላት ላይ በተከሰተው ግርግር ሳቢያ ከቤተሰቦቻቸው ጋር የተጠፋፉ ልጆችን ለማገናኘት ወጣቶች እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ውለዋል። የጠፉትን ልጆች ፎቶ እና የሚገኙነትን ቦታ በፌስቡክ ገጽ ላይ በማጋራት፣ ከ100 በላይ ልጆችን ከወላጆቻቸው ጋር እንዳገናኙ ወጣቶቹ ለቢቢሲ ገልጸዋል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የእናቱን መኪና ያሽከረከረው የአራት ዓመቱ ሕፃን መነጋገሪያ ሆነ

የእናቱን መኪና ያሽከረከረው የአራት ዓመቱ ሕፃን መነጋገሪያ ሆነ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በዒድ ሶላት ላይ ሁከት ፈጥረዋል የተባሉ 76 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ

የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል በአዲስ አበባው የዒድ ሰላት ላይ ሁከትና ብጥብጥ በመፍጠር በግንባር ቀደምነት የተሳተፉ 76 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለጸ። ግብረ ኃይሉ ዛሬ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ፣ "የሁከትና ብጥብጥ ዓላማ ያላቸው ግለሰቦችና ቡድኖች ለብጥብጥ መነሻ በማይሆን ምክንያት" ከስታዲየም ውጭ በተለምዶ የቀይ ሽብር ሰማዕታት መታሰቢያ ሙዚየም አጠገብ ሆነው ባስነሱት ረብሻና...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ዓለም ዛሬም ያልረሳት አና ፍራንክ በናዚዎች ከተያዘች በኋላ ምን ደረሰባት?

በለጋ ዕድሜዋ ታሪክ የሠራችውና ዝናዋ በዓለም የናኘው አና ፍራንክ የተወለደችው እንደ ጎርጎሮሳውያኑ ሰኔ 12/1929 ነበር። ከናዚ ወታደሮች ተደብቃ የጻፈችው የውሎ መዝገብ የታተመው ሕይወቷ በናዚ ካምፕ ውስጥ ካለፈ ከሰባት ዓመታት በኋላ ግንቦት 30/1952 ነው።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በደሕንነት ስጋት ምክንያት ጎንደር ከተማ ሕዝበ ሙስሊሙ ለኢድ ሶላት አደባባይ ሳይወጣ ቀረ

ጎንደር ከተማከሳምንት በፊት ሃይማኖታዊ ይዘት ያለው ግጭት ባስተናገደችው ጎንደር ከተማ ሕዝበ ሙስሊሙ ለኢድ ሶላት አደባባይ ሳይወጣ መቅረቱን ነዋሪዎች ተናገሩ። ቢቢሲ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ከዚህ ቀደም የኢድ ሶላት ሥነ ሥርዓትን ያስተናግድ የነበረው ፋሲለደስ ስታዲየም ጭር ብሎ ውሏል ብለዋል። የጎንደር ከተማ ነዋሪ የሆኑ የእምነቱ ተከታዮች እንደሚሉት ወደ ስታዲየም ሄዶ በጀመዓ [በጋራ] መስገድ የቀረው የደኅንነት ስጋቶች ስላሉ ነው ይላሉ። ይህ የተሰማው ትናንት የጎንደር ከተማ ኡለማ ምክር ቤት ሕዝበ ሙስሊሙ በየመኖሪያ ቤቱ በዓሉን እንዲያሳልፍ ጥሪውን ካስተላለፈ በኋላ ነው። ምክር ቤቱ ትናንት ሚያዚያ 23/2014 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ ላይ “መንግሥት ተገቢውን ኃላፊነት ለመወጣት በማይችልበት ሁኔታ ውስጥ እራስን ከጉዳት መታደግ” በማስፈለጉ የኢድ አልፈጥር በዓልን ምዕምናን በየቤታቸው እንዲያሳልፉት ውሳኔ አስተላልፏል። ምክር ቤቱ በመግለጫ በጎንደር ከተማ ሚያዚያ 18 ባጋጠመው ግጭት ሕይወታቸው ላለፉት ፍትሕ እንዲሰጥ እና ንብረታቸው ለወደመ ተገቢው ካሳ እንዲከፈል ጨምሮ ጠይቋል። “ምንም እንኳን መንግሥት እንደከዚህ ቀደሙ የኢድ ሶላት ሥነ ሥርዓት በስታዲየም እንዲከበር ቢጥርም፤ ሕዝበ ሙስሊሙ በቤቱ ነው ያሳለፈው” ሲሉ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ የጎንደር ከተማ ነዋሪ ለቢቢሲ ገልጸዋል። የእምነቱ ተከታዮች በጋራ ሆነው በአደባባይ መስገድ ባይችሉም በየአካባቢው ባሉ መስጅዶች የሰገዱ ሰዎች መኖራቸውን ቢቢሲ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ተናግረገዋል። የሁለት ልጆች አባትና በጎንደር የቀበሌ 18 ነዋሪ የሆኑት የእምነቱ ተከታይ ደግሞ ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ የተፈጠረውን ግጭትና ጥቃት ተከትሎ በግጭቱ እጃቸው ያለበት ተጠርጣሪዎችን የመያዙ ሥራ ፍትሃዊ አይደለም ይላሉ። “ገለልተኛ ሰው አጣርቶ ድርጊቱን የፈፀሙ ሰዎች ለሕግ እስካልቀረቡ ድረስ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የዩኬ ፖሊስ ድንበር ሊያቋርጡ የነበሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን ያዘ

የብሪታኒያ ድንበር ጠባቂ ኃይል ኢንግሊሽ ቻናል ተብሎ በሚጠራው የውሃ ክፍል በኩል ወደ ዩናይትድ ኪንግደም ለመግባት የሞከሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ይዟል።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኒው ዚላንድ ከሁለት ዓመት በኋላ ድንበሯን ለውጭ አገር ዜጎች ከፈተች

በኮቪድ-19 ስርጭት ወቅት ጥብቅ መመሪያዎችን አውጥታ የወረርሽኙን ስርጭት መግታት ችላ የነበረችው ኒው ዚላንድ ድንበሮቿን ለውጭ አገር ሰዎች ክፍት አደረገች።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የአሜሪካ ፖሊስ ተያይዘው የጠፉትን እስረኛ እና የማረሚያ ቤት ፖሊስ እያፈላለገ ነው

የአሜሪካ ፖሊስ ከእስር ቤት ያመለጠን በግድያ የተከሰሰ እስረኛ እና ከእርሱ ጋር አብራ የጠፋች የማረሚያ ቤት መኮንንን እያሰሰ ነው።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በጅማ ዞን “ንብረትህን ስለሰረቅኩ ይቅር በለኝ” ሲል ደብደቤ የጻፈው ሌባ አነጋጋሪ ሆኗል

በጅማ ከተማ አንድ ሌባ ለግል ተበዳይ "ንብረትህን ስለሰረቅኩ ይቅርብ በለኝ" ሲል የጻፈው ደብደቤ አነጋገሪ ሆኗል፡፡
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጀርመንና ጣሊያን ከናዚ ዘመን የካሳ ጥያቄ ጋር በተያያዘ ተካሰሱ

ጀርመን ጣሊያንን በተባበሩት መንግሥታት ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከሳታለች፡፡
Posted in Amharic News, Ethiopian News

እውቁ የአውሮፓን እግር ኳስ የሚዘውረው ቱጃር ‘ደላላ’ በሞት ተለየ

"ሚኖ" በሚለው በመጀመሪያ ስሙ የሚጠራው እውቁ የእግር ኳስ ተጫዋቾች ወኪል ሚኖ ራዮላ በ54 ዓመቱ ሕይወቱ አልፏል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የጊኒ ወታደራዊ አስተዳደር ሥልጣን ለሲቪል አስተዳደር አስረክባለሁ አለ

የጊኒ ወታደራዊ መንግሥት ከ39 ወራት የሽግግር ጊዜ በኋላ ሥልጣን ለሲቪል አስተዳደር አስረክባለሁ አለ፡፡
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ልቅ የወሲብ ፊልም ምክር ቤት ውስጥ የተመለከቱት ከምክር ቤት አባልነት ተገለሉ

በዩይናትድ ኪንግደም ምክር ቤት የሕዝብ እንደራሴ የሆኑት ኔል ፓሪሽ በምክር ቤት ሆነው በስልካቸው ልቅ የወሲብ ፊልም ሲመለከቱ ተይዘዋል፡፡
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከከፋው የአሲድ ጥቃት በኋላም ስጋት ውስጥ ያለችው ሰላማዊት

በአማራ ክልል በሁለት እጁ እነሴ ወረዳ በቀራኒዮ ከተማ ይኼነው ፈንታ በተባለ ግለሰብ የአሲድ ጥቃት የደረሰባት ሰላማዊት ጊዜው፤ አሁንም ከጥቃት አድራሹ ለእሷ እና ቤተሰቧ ማስፈራሪያ እንደሚደርስ ትናገራለች።...
Posted in Amharic News, Ethiopian News