ከአማራ ክልል የተገኙ የድል ዜናዎች እና መረጃዎች

የድል ዜናዎች እና መረጃዎች

. ለዛሬው ዕለት በጎጃም ዕዝ የሞጣ ፋኖ መብረቁ ብርጌድ ደፈጣ አካሂዶ የምስራቅ ጎጃም ዞን 7 ከፍተኛ አመራሮችን በቁጥጥር ስር አውለዋል።

. በጎጃም ዕዝ የክፍለ ጦር 4 አዛዥ 50 አለቃ ታደሰ የተመራው ፋኖ አማኑኤል ላይ የደብረ ኤልያስ የስናን የቸርተከል የንጉስ ተክለኃይማኖት ፋኖዎች በጥምረት 17 ብሬን 9 ስናይፐር እና ቁጥሩ የበዛ ምርኮኛ ይዘዋል።

. እዛው ምስራቅ ጎጃም የጁቤ ላይ ሌሊት በቆረጣ 130 ጠላት ተረፍርፏል። 8 መንገድ መሪ አቃጣሪ ሚሊሻዎች ተማርከዋል። ኮማንደር ቅዱስ የሚባል የደብረ ማርቆስ ሚሊሻ አመራር እርምጃ ሲወሰድበት በውጊያው 4 ብሬንና 52 ክላሽ ተማርኳል።

ጦርነቱን መቶ አለቃ አበበ ሰው መሆን፣ ፋኖ ትልቅአለም አሳብና ምንያምር ሞላ (ከዚህ በፊት ታንክ የማረከ) በበላይነት ጦሩን መርተውታል።

◦ የአማራ ሕዝባዊ ኃይል (ፋኖ) Tiger one ሲል በሰየመው ኦፕሬሽን በባህርዳር ከተማ ምሊሻ እና አድማ ብተናወች ላይ መብረቃዊ እርምጃ ወስዷል::

◦ አርበኛ ዘመነ ካሴ በሮሐ ሚዲያ በኩል የሰጠውን መመሪያ ተከትሎ ብተከናወነው በዚህ ኦፕሬሽን በባህርዳር ከተማ ድሪም ኬር ሆስፒታል አካባቢ ከብልፅግና ስምሪትወስደው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 6 ምሊሻ እና 2 የአድማ ብተና አባላት እስከ ወዲያኛው ተሸኝተዋል።

◦ የብልፅግናን የማጭበርበሪያ ጥሪ ተቀብለው ወራሪውን ሰራዊት የተቀላቀሉ የምሊሻ አባላት ለፋኖ እጃቸውን እስካልሰጡ ድረስ ይህ ኦፕሬሽን ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን የአማራ ሕዝባዊ ኃይል (ፋኖ) የታይገር ዋን ኦፕሬሽን መምሪያ አሳውቋል።

ከሸዋሮቢት ደቡብ ምስራቅ አቅጣጫ የተኩስ ድምፅ እንደሚሰማ ነዋሪዎች ጠቁመዋል።የዋናው መስመር እንቅስቃሴ እስካሁን(9:15) ድረስ የተቋረጠ ነገር የለም።

ደብረታቦር አቅራቢያ አለምሳጋ በተባለ ጫካ ማን እንደተኮሰው ባልታወቀ ጥይት ተመቶ አንድ ሹፌር መገደሉ ተሰምቷል።

ምስራቅ ጎጃም ባሶ ሊበን፣ የጁቤ፣አማኑኤል አካባቢ ትናንትና ዛሬ ማለዳ የተኩስ ልውውጥ ሲደረግ ነበር ተብሏል።

ምዕራብ ጎጃም ቡሬ ዙሪያና ሽንዲ ተኩስ ሲሰማ እንደነበር የተሰማ ቢሆንም ንጋት ላይ ቆሟል።

ደጋዳሞት ትናንት ምሽት የድሮን ጥቃት መፈፀሙ ተሰምቷል።የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ የተገለፀ ነገር የለም።