Yared Hailemariam
ታዬን ለመበቀል፣ ቀነኒን ፍትህ በመንፈግ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአማራ ብሔር ተወላጅ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞችን በማንነታቸው ላይ ያነጣጠረ ጥቃት በመፈጸም የዘቀጠው የፍትህ ሥርዓት።
የፍትህ ሥርዓቱን ለበቀል፣ ለፖለቲካ እና የወገኑለትን ከተጠያቂነት ለማስመለጥ በመንግስት ደረጃ ታስቦበት ሲተገበር ማየት እጅግ ያማል። ሰዎች በማንነታቸውና በሃሳባቸው ብቻ ተፈርጀው፣ ታስረው እና በሃሰት ሽብርተኛ ተብለው ተከሰው በሚጉላሉበት አገር ብዙ ጥፋትና ወንጀል የፈጸሙና ያስፈጸሙ ሰዎች ደግሞ ያለጠያቂት በነጻነት ይንቀሳቀሳሉ።
ታዮ ደንድአን በሰንሰለት አስሬ ፍርድ ቤት ካላቀረብኩ ማለት ከፖለቲካ በቀል ውጪ ሌላ ትርጉም የለውም። አንድ እስረኛ በሰንሰለት ታስሮ ፍርድ ቤት የሚቀርበው እስረኛው አንድም ሊያመልጥ ይችላል ወይም ጉልበተኛ ሆኖ ፖሊሶቹን ወይም ዳኞችን ሊተናኮስ ይችላል ተብሎ ሲታሰብ ነው። ታዬን ማሰር ግን አላማው ማዋረድ፣ ማሸማቀቀ እና ፍትህን መበቀያ ማድረግ ነው። የታዮ ሁኔታ ሲገርመኝ ባለቤቱን ቀነኒን በመግደል ፖሊስ ጠርጥሮና ማስረጃ አሰባስቦ ለአቃቤ ሕግ ክስ እንዲመሰርትበት የተላለፈውን ፋይል በመዝጋትና ተጠርጣሪውን በመልቀቅ የወንጀሉን ጉዳይ አባገዳዎች በሽምግልና እና በካሳ እንዲጨርሱት ማድረግ ከነውርም አልፎ የፍትህ ሥርዓቱ ምን ደረጃ ላይ እንዳለ ማሳያ ነው። ( Yared Hailemariam )