ቀናቶችን በወሰደው ተጋድሎ ባለሽርጡ ክፍለጦር በመደበኛ ውጊያ እና ደፈጣ ጥቃት አመርቂ ድሎችን አስመዘገበ::

ቀናቶችን በወሰደው ተጋድሎ ባለሽርጡ ክፍለጦር በመደበኛ ውጊያ እና ደፈጣ ጥቃት አመርቂ ድሎችን አስመዘገበ::

ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 1 ባለሽርጡ ክፍለጦር በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ ፋጂ በተባለ ቦታ ማዕረጉ በውል ያልታወቀ የስራዐቱ ወታደር ከፍተኛ አመራር ከጊራና ወደ ፋጂ ሲንቀሳቀስ በተያዘ የተጠና ደፈጣ ጥቃት ከነ ፖትሮሉ እና ከአጀቢዎቹ ጋር በመደምሰስ ድል ተጎናፀፈ።

በእብሪትና ትቢት ተሞልቶ የመጣውን የአብይ አህመድ ጭራቅ ሰራዊት በሀብሩ ወረዳ ፋጂ በተባለ ቦታ በተወሰደ የደፈጣ ጥቃት አንድ ጓድ የስርዐቱ ሀይሎችን በመደምሰስ እና ቁጥሩ በውል ያልታወቀ ባንዳ የስርዐቱን ወንበር ጠባቂ ሀይሎችን ማቁሰልና መበተን ተችሏል።

ዛሬ ታህሳስ 18/2018 አ.ም ከቀኑ 11:30 በተወሰደ የደፈጣ ጥቃት አመራሩን ከነተሽከርካሪው በመደምሰስና በማውደም አመራሩን ለማሳለፍ ግራና ቀኝ ቦታ ይዘው የነበሩትን የስርዐቱን ወታደር ጭምር በመደምሰሰና በማቁሰል የጥላትን ቅጥረኛ ሰራዊት ወደ መሬት በግስላዎቹ ነፍጥ እየተፈለፈለ የረገፈ ሲሆን፤ ከፊቱ የሚነጠፈውን ጓዱን የተመለከተ ጥላት ለተዎሰነ ሰዓት ባለበት ቁሞ መሸሻውን ቢያማትርም ግስላው ፋኖ ወደ ፊት በማጥቃት”አንድ ጥይት ለአንድ ጥላት” በሚል የአማራ ብሂል ለአንድ ጥላት በአንድ ጥይት ግንባር ግባሩን ተመቷል።

በርካታ ሙት እና ቁስለኛ ያስተናገደው የአብይ አህመድ ሰራዊት የሞራል ውድቀት፤የቁስ ክስረትን በማስተናገድ፣እና የደረሰበትን ብትር መቋቋም ሲያቅተው ሁለት ንፁሀኖችን በዘፈቀደ ተኩስ በመግደል የዘወትር ግብሩንና አቅዶት የመጣውን የጥፋት ተልዕኮ ሳያሳካ ወደ መጣበት ወደ ጊራና ከተማ መመለስ ተችሏል።አገዛዙ ክፉኛ የቆሰለውን ሰራዊቱን በአንቡላንሶች ወደ ጊራና ጤና ጣቢያ ሲያጓጊዝ አምሽቷል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም ቀናቶችን በወሰደው የመርሳ እና የአምባሰል ዙሪያ ተጋድሎ ምስራቅ አማራ ኮር 1 ባለ ሽርጡ ክፍለ ጦር 2ኛ ሻለቃ ታህሳስ 17/2018 ዓ.ም ንጋት 12:00 ከውጫሌ ከተማ እና አምባሰል ዙሪያ ሮቢት አካባቢ በርካታ ሃይሉን ይዞ ወደ አበት ማጥቃት ያደረገ ጠላት ጋር ብርቱ ትንቅንቅና ተጋድሎ በማድረግ በጠላት ላይ ከባድ ሰብዓዊ ኪሳራ በማድረስ ድል አስመዝግበዋል::

ባለሽርጡ ክፍለ ጦር በአጠቃላይ ባለፉት አንድ ሳምንት ተከታታይ ቀናቶች ያለማቋረጥ ተጋድሎ በማድረግ ጠላት ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊ ጉዳት በማድረስ ብሎም የነፍስወከፍ ክላሾችን ጨምሮ በርከት ያሉ ወታደራዊ ቁሳቁሶችን ማርከው ታላቅ ድል አስመዝግበዋል::
©አፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል!