በአርሲ ዞን አቦምሳ ከተማ በቅርብ እርቀት ላይ በሚገኘው ልዩ ስሙ “ሞፈር ግቢ” በተሰኘ ስፍራ ላይ 6 አማራ ኦርቶዶክሳውያን (ንፁሃን ዜጎች) ታግተው ወደ አልታወቀ ቦታ ተወስደዋል ።
በአርሲ ዞን አቦምሳ ከተማ በቅርብ እርቀት በሚገኘው “ሞፈር ግቢ” ተብሎ በሚጠራው ስፍራ፤ በቀን 16/04/2018 ዓ.ም ከአሰኮ ወረዳ ሰንጎ ቀበሌ ለቅሶ ደርሰው ፒካፕ መኪና እያሽከረከሩ ወደ ናዝሪት ከተማ ሲጓዙ የነበሩ 6 ንፁሃን ዜጎች – አማራ ኦርቶዶክሳውያን ታግተው ወደ አልታወቀ ቦታ መወሰዳቸውን የታጋች ቤተሰቦች መረጃውን አድርሰውናል ።
ይህ አማራ ኦርቶዶክሱን ማረደና በአሰቃቂ ሁኔታ መግደል እንዲሁም ከፍተኛ ገንዘብ በመጠየቅ…ግፈኛው፣ ዘራፊው፣ ገዳዩ የጥምር ቡድን እነኝህንም ንፁሃን ዜጎች አግቶ ከወሰደ በኋላ ለያንዳንዳቸው #አንድ_አንድ_ሚሊዮን_ብር ጠይቋል ። መረጃውን ያደረሱን የታጋች ቤተሰቦች እንዲህ ሲሉም ተደምጠዋል “ይህ መፍትሄ የታጣለት የማንነት ተኮር ግድያ፣ ዘረፋና እገታ…ዛሬም እንደቀጠለ ነው፤ ይሄው ቤተሰቦቻችን አግተው ከወሰዱ በኋላ ስልክ በመደወል እስከ 1 ሚለዮን ብር ክፍሉ አልበለዚያው እንገድላቸዋለን በማለት እያስፈራሩን ይገኛሉ ፥ ገንዘቡን ብንከፍልም ስለመለቀቃቸው ምንም አይነት ዋስትና የለንም፤ ምክንያቱም ከዚህ በፊትም በተመሳሳይ ገንዘብ እየተቀበሉ ብዙ አማራ ኦርቶዶክሳውያንን ገድለዋል” በማለት ለጣቢያችን ተናግረዋል ።