የነ አሰፋ ቸኮለ ሰሜን ምስራቅ ዕዝ ዛሬም በድጋሚ አከርካሪው ተሰብሯል!
በዕዙ ስር በዘመቻ አባናደው ከባድ ጉዳት ደርሶባት ዳግም የተደራጀችው 61ኛ ክ/ጦር ትናንት በስቲያ በተደረገ ውጊያ የሰው ኃይሏን ጨምሮ 197 ወታደሮቿ ሲገደሉ ከ85 በላይ የሚሆኑት ቁስለኛ ተደርገውባታል።
ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጄኔራል አሳምነዉ ፅጌ ኮር በአርበኛ አምሳ አለቃ ጌታየ ተፈሪ የሚመራው ጄኔራል ተፈራ ማሞ ክፍለ ጦርና ዋግሹም ብርጌድ እንዲሁም ከአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሜጀር ጄኔራል ውባንተ አባተ ኮር የተውጣጡ የፋኖ ኃይሎች በጥምረት ባደረጉት አውደ ውጊያ የጠላት አከርካሪን በመስበር ታላቅ ድል መቀዳጀታቸውን ምኒልክ ዕዝ ለመረብ ሚዲያ በላከው መረጃ አስታውቋል።
ታህሳስ 19/2018 ዓ/ም ከንጋቱ 10:00 ሰዓት ጀምሮ በሰሜን ምስራቅ ዕዝ 803ኛ ኮር ስር በሻምበል ጫላ የሚመራው 61ኛ ክ/ጦር ከዕዙ ሜካናይዝድ ጋር በመሆን መነሻውን ከአይና ቡግና ከተማ አድርጎ ወደ ብርኮ በአራት አቅጣጫ ማለትም በብርኮ ገብርኤል አቅጣጫ፣በጤና ጣቢያው አቅጣጫ፣በጭቃው አቅጣጫ እና በብርኮ ኪዳነ ምህረት አቅጣጫ ለማጥቃት አስቦ ተኩስ የጀመረ ቢሆንም፡ ነገር ግን ከወደ ፋኖ የተሰነዘረበትን የፀረ ማጥቃት እርምጃን መከላከል ሳይችል ቀርቶ ከባድ የሆነ የሰብአዊ፣ ቁሣዊና ሞራላዊ ኪሳራን ተከናንቧል።
በዙ-23፣ በሁለት ሞርታር በበርካታ ዲሽቃና በሌሎች የቡድንና ከባባድ ሜካናይዝድ ታግዞ ተሰልፎ የነበረው የጠላት ኃይል፡ ልብ እና እውነት ከሌለው መሣሪያ ብቻውን ዋጋቢስ መሆኑን አስመስክሮበታል ተብሏል።
የ61ኛ ክፍለ ጦር የሰው ኃይል ኃላፊና ሌሎች የክፍለጦሩ አመራሮችን ጨምሮ 197 የአገዛዙ ወታደሮች ሲገደሉ፡ ከ85 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ቁስለኛ ተደርገዋል፣ ሰባት ወታደሮች እጅ ከፈንጅ ተማርከዋል ብሏል ምኒልክ ዕዝ ለመረብ ሚዲያ በላከው መረጃ።
በተጨማሪም ሁለት ብሬን፣43 ክላሽንኮቭ መሣሪያ፣ 84 ወታደራዊ ሻንጣ፣ 2ሺ 850 የብሬን ተተኳሽ፣2ሺ 200 የክላሽ ተተኳሽ ፋኖ ማርኮ ታጥቋል።