በአማራና በትግራይ ተፈናቃዮች “ተርበናል” እያሉ ነው
የኢትዮጵያ መንግስት ከዕርዳታ ጥገኝነት ለመውጣት ዘመቻ በጀመረበት፣ የአሜሪካ መንግስት ከፍ ያለ የገንዘብ ድጋፍ ባቋረጠበት በዚህ ወቅት በኢትዮጵያ ተፈናቅለው በመጠለያ የሚገኙ ዜጎች የረሀብ ፈተና ተርጋርጦባቸዋል።
ዋዜማ በተለያዩ የተፈናቃይ መጠለያዎች ያሉ ዜጎችን ያነጋገረች ሲሆን፣ እየተባባሰ በመጣው የምግብ እጥረት የሰው ህይወት እንዳይቀጠፍ ስጋት የገባቸው ተፈናቃዮች መንግስት መፍትሄ እንዲያበጅ ተማፅነዋል። መንግስት ዕርዳታ እያቀረብኩ ነው ብሏል።
በአማራ ክልል ፣ በትግራይ፣ በኦሮሚያ፣ ቤንሻንጉልና እና ሶማሌ ክልሎች ባሉ በርካታ የመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ለአመታት የቆዩ በሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች በአሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ነግረውናል።
ዝርዝር ዘገባ አዘጋጅተናል፣ አንብቡልን- https://miniliksalsawi.substack.com/p/displaced-people-in-ethiopia-face