የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ለክፍለ ጦር አመራሮችና ለሰራዊት አባሎች ፖለቲካዊ ስልጠና ሰጠ!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር ለተከታታይ ሶስት ቀናት አጠቃላይ ለክፍለጦር፣ለሻለሻለቃ አመራሮችና አጠቃላይ ለሰራዊቱ በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል። እንደሚታወቀው የአብይ አህመድ አገዛዝ ወሮበላው የኦሮምማው ስብስብ አማራን ለማጥፋት በተለያዩ የአማራ ግዛቶችና ከአማራ ግዛቶች ውጭ ባሉ የአማራ ተወላጆች ላይ የዘር ፍጅት እያደርገ መሆኑን አለም የሚያቀው ሀቅ ነው።
ሆኖም ይህን የብልፅግና ፋሽስታዊ ስርዐት የአማራ ልጆች በነበልባል ክንዳቸው እየተፋለሙትና እየመከቱ የበላይነታቸው እየወሰዱ ይገኛል። ስለሆነም የአሳምነው አናብስቶች ከትግሉ ጎን ለጎን በተለያዩ ለሰራዊት ፖለቲካዊ ስልጠና ማለትም፦
*የሰራዊት ስነምግባር እና ስነስረዓት መወሰኛ ደንብ
*ጓዳዊ ዝምደና
*ባህል እና ጨዋነት
*ድርጅትና የድርጅት ምንነት
*የአማራ ህዝብ ምንነት እና *የገጠሙት ፈተናወች እና ያደረጋቸው ተጋድሎወች
*ፋኖነት እና መገለጫ ባህሪያት በሚሉ
አርዕስቶች ላይ ለተከታታይ ሶስት ቀናት በአሳምነው ዕዝ ምክትል ድርጅት ጉዳይ አርበኛ ኢያሱ ሙሉጌታ ፣የአሳምነው ዕዝ ህግ ክፍል ሀላፊ አርበኛ ተስፋዬ ገስጥ እና የአሳምነው ዕዝ ሎጀስቲክ ኃላፊ ሻለቃ ሞገስ ለማ በመሆን ከትምህርት እና ስልጠና መምሪያ በተሰጠው ዕቅድ መሰረት የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ኛ ክር አፄ ይኩኖ አምላክ ክፍለጦር የሻለቃ አመራሮች እና ለሰራዊት አባላት በበቂ ሁኔታ ስልጠና በመስጠት አመርቂ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።
በስልጠናውም የተገኙት የዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር ዓፄ ይኩኖአምላክ ክፍለ ጦር አመራሮችና የሻለቃ አመራር አባላት በስልጠናው የአማራን የሞኖር ነፃነት በቅርቡ እንዲሚያበስሩ እርግጠኛ እየሆኑ ከአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የሚሰጣቸውን ማነኛውምንም ግዳጅ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።
©የፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት መምሪያ!