የህዝቡን አንድነት በማፅናት አስተማማኝ የህዝብ ደጀንነት እያረጋገጠ እንደሚገኝ የደብረ ኤልያስ ወረዳ ጊዚያዊ መንግስት አስታወቀ።

የህዝቡን አንድነት በማፅናት አስተማማኝ የህዝብ ደጀንነት እያረጋገጠ እንደሚገኝ የደብረ ኤልያስ ወረዳ ጊዚያዊ መንግስት አስታወቀ።

በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ በመልሶ ማደራጀት ትግበራው የህዝብን አስተዳደር የፀጥታና የፍትህ ጥያቄዎችን በመመለስ አስተማማኝ የህዝብ ደጀንነትን እንዲያረጋግጥ ታስቦ በአዲስ የተዋቀረው ጊዚያዊ መንግስት በ206ኛ ኮር ባሉ ወረዳዎችና ቀበሌዎች አገልግሎት በመጀመር በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል።

በ206ኛ ኮር 14ኛ ክ/ጦር ስር የሚገኘው የደብረ ኤልያስ ወረዳ ጊዚያዊ መንግስት ከጠላት ነፃ በወጡ ሁሉም ቀበሌዎች የአስተዳደር መዋቅር በመዘርጋት የፍትህና ህግ አገልግሎት፣ ፀጥታ፣ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን በማከናወን ከህዝቡ የሚነሱ ጥያቄዎችን በፍጥነት ምላሽ በመስጠት አመርቂ ለውጥ እያስመዘገበ መሆኑን የወረዳው ጊዚያዊ መንግስት ገልጿል።

የህዝብን አስተማማኝ ደጀንነት በማረጋገጥ ሰፊ ስራዎችን እያከናወነ የሚገኘው ጊዚያዊ መንግስቱ የግል ታጣቂዎችን በማደራጀት የአካባቢያቸውን ሰላም በማረጋገጥ እንደቻሉ በማውሳት የሚሰጣቸውን ማንኛውንም ድርጅታዊ ግዳጅ ከመደበኛ ሰራዊቱ ጎን ተሰልፈው እንደሚወጡም አረጋግጧል።

በመልሶ ማደራጀት ትግበራው ባንዳዎችን በማፅዳት የሰራዊቱን የህዝቡንና የትግሉን ደህንነት በማስጠበቅ የጠላትን እረጅም እጅ እየቆረጠ የሚገኘው 206ኛ ኮር ለደብረ ኤልያስ ወረዳ ጊዚያዊ መንግስት አመራሮች፣ በህግና እና ስነ-ስርዓት እንዲሁም በጊዚአዊ መንግስት መመሪያዎች ላይ ከ14ኛ ክ/ጦር አመራሮች ጋር በመተባበር ስልጠና ሰጧል።

የድርጅቱን ህግ እና ደንብ ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች የፀደቁ መመሪያዎች ላይ ስልጠና የተሰጣቸው የወረዳ ጊዚያዊ መንግስት አመራሮች ህዝቡን ለማስተዳደርና የድርጅታችንን ህግና ደንብ ለማስፈፀም በቂ ግንዛቤ ማግኘታቸውንም ተናግረዋል ።
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል