የኢትዮጲያ የባሕር በር ጥያቄ የሚፈታው የኤርትራ መንግስት ሲወገድ ብቻ ነው ሲል የቀይ ባሕር አፋር ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ በሠጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ገለጸ።
የፓርቲው ሊቀመንበር ኢብራሂም ሃሩን ይህን የተናገሩት፣ ኢትዮጵያ የአሰብ ወደብ ታሪካዊ ባለቤት የመሆኗን ጉዳይ ፓርቲያቸው ይቀበለው እንደሆነ ዋዜማ ላቀረበችላቸው ጥያቄ በሠጡት ቀጥተኛ ያልሆነ ምላሽ ነው።
ኢብራሂም፣ ፓርቲያቸው ከኢትዮጵያ መንግስት የሚያገኘው የትጥቅም ሆነ ሌላ ድጋፍ እንደሌለም ተናግረዋል።
የፓርቲው ዋነኛ ዓላማ የአፋርን ሕዝብ መብቶች ማስከበር እና የኤርትራን መንግስት ማስወገድ እንጅ የአፋርን ሕዝብ ከኤርትራ መገንጠልም ሆነ ከኢትዮጵያ ጋር ማቀላቀል እንዳልሆነም ኢብራሂም ገልጸዋል።
የኤርትራ መንግሥት በቀይ ባሕር አፋሮች ላይ እያደረሠ ነው ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት በማስመልከት ለአፍሪካ የሕዝቦችና ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ክስ ማስገባቱን የጠቀሰው ፓርቲው፣ ሁኔታዎች ካልተሻሻሉ ከኤርትራ የመገንጠልንና የመቀጠልን ጉዳይ በሂደት እንደሚያየው ገልጧል።የጠቀሰው ፓርቲው፣ ሁኔታዎች ካልተሻሻሉ ከኤርትራ የመገንጠልንና የመቀጠልን ጉዳይ በሂደት እንደሚያየው ገልጧል።