አንድ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ ከነአጃቢዎቹ መገደሉ ተሰምቷል

በጊራና ግንባር ልዩ ቦታው ፋጂ አከባቢ ላይ በተፈፀመ ደፈጣ ጥቃት ማዕረጉ በውል ያልታወቀ አንድ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ ከነአጃቢዎቹ መገደሉ ተሰምቷል።

በደፈጣ ጥቃቱ ወታደራዊ አዛዡ ተሳፍሮባት የነበረችው ወታደራዊ ፓትሮልም የወደመች ሲሆን፡ የአዛዡን ደህንነት ለመጠበቅ በመንገዱ ግራ ቀኝ ወጥረው የነበሩ ወታደሮችም ሙሉ በሙሉ መደምሰሳቸውን የመረብ ሚዲያ የምስራቅ ዐምሓራ ቀጠና ዘጋቢዎች ለማረጋገጥ ችለዋል።

የአገዛዙ ኃይል፡ ወታደራዊ አዛዡን ጨምሮ ከተገደሉበት በተጨማሪ በጥቃቱ የቆሰሉበት ወታደሮቹን እስከ ትናንት እኩለ ለሊት ድረስ እያንዘፋዘፈ ወደ ሕክምና ሲያጓጉዝ እንደነበር ታውቋል።