የፍትህ ሚኒስቴር “የሰው እና ሰነድ ማስረጃ ማቅረብ ባለመቻሉ፤ በማንነታቸው እና በፖለቲካ አቋማችው የታሰሩ ሰዎች ለከፍተኛ ሰብዓዊ ጉዳት ” ተዳርገዋል ሲሉ የምክርቤት አባል ተናገሩ፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በበኩሉ በማንነቱ ሆነ በፖለቲካ አቋሙ የሚታሰርም ሆነ የተሰረ ሰው እንደሌለ ተናገሮ ግን እንድ ሰው የፖለቲካ ግቡን ለማሳካት በህገወጥ መንገድ የሚንቀሳቀስ ፖለቲከኛም ፣የመንግስት ሰራተኛም ሆነ የመንግስት ሃላፊ ላይ የህግ ተጠያቂነትን አረጋግጣለሁ ብሏል፡፡
ይህ ጉዳይ የተነሳው የፍትህ ሚኒስቴር ዛሬ በፓርላማ መደበኛ ስብሰባ ላይ ቀርቦ ከምክርቤት አባላት ለተነሱለት ጥያቄዎች የ25 ደቂቃ ምላሽ እና ማብራርያ ባቀረበበት ወቅት ነው፡፡
የምክርቤት አባሉ አበባው ደስአለው (ዶ/ር) የፍትህ ሚኒስቴር ዋነኛው ስራው ክስ በመመስረት ፣ክሱን ሂደት በመከታታል አፋጣኝ ፍትህ ለዜጎች ማደረስ መሆኑንን አስተውሰው “በማንነታቸው እና በፖለቲካ አመለካከታቸው ብቻ ከ2 ዓመት ከስድስት 6 ወር በላይ የታሰሩ የአማራ ፖለቲከኞች ፣ጋዜጠኖች ፣እንቂዎች እና የሃይማኖት አባቶች እናንተ የሚጠበቅባችሁን የሰነድ ፣የሰው ማስረጃ እና መስክር ማቅረብ ባለመቻላችሁ ለክፍተኛ ሰብዓዊ ጉዳት ተዳርገዋል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የምክርቤት አባሉ”ማስረጃ እና ምስክር ማቅረብ ካልቻላችሁ የተሰጣችሁን ክስ የማቋረጥ ስልጣን መጠቀም ሲገባችሁ ዜጎች በፍትህ መጓደል የሚሰቃዩት አስከመቼ ነው?”ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
“ከፖለቲካ ጫና ወጥታቹሁስ እውነተኛ ፍትህ የምታሰፍኑት መቼ ነው “በሚል ሌላ ጥያቄም አበባው ደስአለው (ዶ/ር)አክለዋል ፡፡
በማረሚያቤት የሚገኙ አስረኞች ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሲያጋጥም ዳኞችም ፍርድ ሲሰጡ ፌደራል ማረሚያ ቤቶች ግን ይህን ትዕዛዝ ሲተገብሩ አይታይም ሲሉ የምክርቤት አባሉ ከስዋል፡፡
በስብዓዊ ተቋት እንደተረጋገጠው በአገሪቱ በተለያዩ ክፍሎች በተለይም በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች ከፍተኛ የመብት ጥሰቶች መኖራቸውን የምክርቤት አባሉ ተናግረው ለዚህ የመብት ጥሰት ፍትህ እንዲረጋገጥ ተቋሙ ምን ሰራ ነው? የሚል ጥያቄ ጠይቀዋል፡፡
ለጥያቄዎቹ ምላሽ የሰጡት የፍትህ ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሃና አርዕያ ስለሳሴ ናቸው፡፡
ሚኒስትሯ በማንነቱ አልያም በፖለቲካ አቋሙ ብቻ የከሰስነውም ሆነ ፍርድ ቤት ያቆምንው ሰው የለም ሲሉ ተናግረው “ግን አንድ ሰው የፖለቲካ ግቡን ለማሳካት በህገወጥ መንገድ የሚንቀሳቀስ ከሆነ ፖለቲከኛም ፣የምንግስት ሰራተኛም ሆነ የመንግስት ሃላፊ የህግ ተጠያቂነትን እናረጋግጣለን ሲሉ መልሰዋል፡፡
ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን መጠበቅ ማለት ማንኛውም ሰው ከህግ በታች ነው ያሉት ሚኒስትር ወ/ሮ ሃና በህጉ በተቀመጡ ገደቦች ነው የትኛውም የፖለቲካ አጀንዳ ሊከናውን የሚችለው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ስለዚህም አሁንም “በክስ ሂደት ላይ ያሉ ጉዳዮቻችን በሙሉ ህገ መንግስቱን፣ ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን ሌሎች ህጎችን ማስጠበቅ ላይ የተኮሩ ናቸው” ብለዋል ሚኒስትሯ፡፡
በአቃቢ ህግ በኩል ምስክሮችን እና ሰነዶችን ማቅረብ ላይ ችግር አለ የሚለውን ሲመልሱ ደግሞ እኛ መስክር ሳናቀርብ የተንጓተተ ሆነ የቀረ ጉዳይ የለም፤ ምስከሮችም ሰነዶችም ይቀርባሉ ሲሉ ወ/ሮ ሃና ተናግረዋል፡፡
ነገር ግን “መገንዘብ የለብን የሽብር እና ተመሳሳይ ውስብስብ የሆኑ ወንጀሎች ላይ ክርክሩ ረጀም ጊዜ የሚወስድ ነው ፡፡ጉዳይውም ውስብስብ ስለሆነና ብዙ መስክሮች ሰለሚጠራ ብዙ ሰነዶች የሚቀርቡበት እንዲሁም ደግሞ ከመጀመርያ ደረጃ መቃወሚያዎች ጀምሮ በየደረጃው እያንዳንዱ ጭብጥ ላይ ክርክር ተደርጎ ብይን የሚሰጥበት ስለሆነ ሂደቱ በራሱ የሚውስደው ጊዜ አለ”ሲሉ አስረድተዋል፡፡
ይህ ማላት ግን የወንጀል ምርመራ እና ክስ ሂደቱ ቅልጥፍና የምንፈልገው ደረጃ ነው ማለት እይደለም ሲሉ የፍትህ ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሃና አርዕያ ስለሳሴ መልሰዋል፡፡
የውንጀል ተጠያቂነትን ማረጋገጥ ከባድ ስራ ስለሆነ ውሳኔውም አንድ ሰው ስለፈለገ ብቻ ማስወሰን እንደማይቻል አስረድተዋል ሚኒስትሯ፡፡
በግጭት ውስጥ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን በተመለከተ ደግሞ መንግስት ችግሩን ለመፍታት ሁለት የመፍተሄ መላዎችን እየተከተለ እንደሆነ ሚኒስትር ሃና ጠቅሰዋል፡፡
በግጭት ወስጥ የመብት ጥስት እንደሚፈጸም ያስረዱት ሚኒስትሯ ግጭትን ለመስቆም እና ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የሀገራዊ ምክር በስራ ላይ ነው በግጭት አውድ ውስጥ ለተፈጸሙ የመብት ጥሰቶች ደግሞ በሽግግር ፍትህ ለመፍታት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
ይህ እንዳለ ሆነ የመንግስት የጸጥታ አካላት ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች የህግ የማስከበርስራን እየሰሩ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡