በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት መካከል፣ በአራቱም የወለጋ ዞኖች ውስጥ የሚደረገው የተኩስ ልውውጥ፣ ለዓመታት ቤተሰቦቻቸውን እንዳይጎበኙ እንዳከላከላቸው፣ የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የአካባቢው ተወላጆች ተናገሩ።
በአራቱም ዞኖች ውስጥ በቀጠለው ጦርነት ሳቢያ፣ የአካባቢው ተወላጆች ወደየቀዬአቸው ለመሔድ ባለመቻላቸው፣ ለማኅበራዊ ችግሮች እንደተጋለጡ አመልክተዋል።
በተለያዩ የሥ…