ከጋዛ ሺፋ ሆስፒታል ያለጊዜያቸው የተወለዱ ህጻናት ለቀው ወጡ

የአለም የጤና ድርጅት በትንሹ 31 በጠና የታመሙ፣ ያለጊዜው የተወለዱ ሕፃናት ከጋዛ ሺፋ ሆስፒታል ወደ ግብፅ ሆስፒታል መወሰዳቸውን ዛሬ እሁድ አስታውቋል።

የእስራኤል ወታደሮች በሀማስ ታጣቂዎች ላይ ባደረጉት ወታደራዊ ዘመቻ ባለፈው ሳምንት ሆስፒታሉ ላይ ድንገተኛ ጥቃት ማድረሳቸው የሚታወስ ሲሆን፤ የዓለም ጤና ድርጅት ልዑክ ትላንት ቅዳሜ ሆስፒታሉን ከጎበኘ በኋላ “በአንድ ወቅት በጋዛ ውስጥ ትል…