ሙሉ ጎንደር ክፍለሀገርን ለመውረር በያቅጣጫው ዝግጅቱ ተጧጡፎ ቀጥሏል

በተለይ ጎንደርን በተመለከተ ወቅታዊ አስጊ ሁኔታ፤

*የምስጋናው አንዱአለም መረጃ

ሙሉ ጎንደር ክፍለሀገርን ለመውረር በያቅጣጫው ዝግጅቱ ተጧጡፎ ቀጥሏል፡፡ ከሱዳን፣ ከትግራይ እና ከአዲስ አበባ፡፡ ሱዳን ላይ አብይና ወያኔ የሳምሪን ቡድን እያዘጋጁ ናቸው፡፡ ከዚህ በፊት ሁመራ ባከር ላይ አዳዲስ ፊቶች ታይተዋል፡፡ እዚሁ ባከር ላይ የነበሩ 1500 የአማራ ወታደሮች ባልታወቀ ምክንያት ትጥቃቸውን እንዲያወርዱ ተደርገው ታስረዋል፡፡

እንደሚታወሰው ሀዋሳ እና አዋሽ አርባ ታስረው የነበሩ የትግራይ ተወላጆች ተፈተው እና ውዝፍ ደመወዛቸው ተከፍሎ አማራ ክልል ባለው ጦርነት እንዲሳተፉ ተደርጉዋል።

ከዚህ በፊት ማይካድራ እና ጭና ላይ አማራን የጨፈጨፉት አሁን የጎንደር መታወቂያ 17-30 ሺ ገንዘብ እየከፈሉ በመግዛት ወደ ጎንደር እየገቡ ናቸው። ለዚህ ተባባሪ ደሞ መተማ አካባቢ ያሉ የሀሳብና ብሄር ተጋሪ ባለስልጣናት ናቸው።

ከአገዛዙ ጋር ቅርበት ያላቸው ሰዎች እንደሚያስጠነቅቁት ጎንደር ክተት ብሎ ካልተነሳ እንደ ማይካድራ ለማድረግ ነው ታቅዶ እየተሰራ ያለው፡፡ “ጎንደርን እና እንስራላቸዋለን” እያሉ እንደሚፎክሩ ታውቋል፡፡ ባጭር አማርኛ ወያኔ ጎንደርን ለማንበርከክ ከአብይ ጋር እየተመካከረ ይገኛል፡፡

አሁን ላይ አብዛኛው ጦር ከትግራይ ተከዜን ተሻግሮ ወደ ሁመራ እየገባ ነው፡፡ ጦሩ መከላከያ ነው ቢሉም የትግራይ ሃይሎችን የመከላከያ ልብስ አልብሰው እያመጧቸው እንደሆነ ነው የአይን እማኞች እየተናገሩ ያሉት፡፡ ሁኔታውን የታዘቡ እንደሚሉት “ወልቃይትን እንሰጣችኋለን፣ አግዙን” ተብለው ነው እየገቡ ያሉት፡፡ የትግራይ አክቲቪስቶች በፌዴራሉ ጥያቄ መሰረት “የትግራይ ሃይሎች ወደ ጎንደር ገቡ” እያሉ መረጃ እንደሚያሰራጩም ታውቋል፡፡ በሳንጃ በኩል የገባው ሰራዊት ዋና አላማው የሰሜን አማራ ሀይሎችን በመክበብ ማዳከም ነው፡፡ ገፍቶ ገብቶ እንደማያሸንፍ ስለሚያውቅ፡፡

ደሴ ዙርያ አደገኛ ሰሰለት ተፈጥሯል፡፡ እሱም መዋጋት የማይፈልጉትን የአማራ እና አንዳድ የደቡብ ተወላጆች መታወቂያ አመቻችተው የትራንስፖርት ትንሽ ብር ሰጥተው መሳርያ ለእነሱ አስረክበው እንዲጠፉ ያደርጋሉ።

(የመረጃው ምንጭ : ምስጋናው አንዱአለም)