በደብረ ማርቆስና ደምበጫም እንቅስቃሴዎች ቆመዋል፤ በአማኑኤል ከተማ የሁለት ወጣቶች ህይወት አልፏል::

በደብረ ማርቆስና በደምበጫ መካከል በሚገኘው አማኑዔል ከተማ በ አገዛዙ ወታደቶች በተተኮሰ ጥይት የሁለት ወጣቶች ህይወት አልፏል:: ይህን ተከትሎ በአማኑኤል ከተማ ከፍተኛ ተቃውሞ ተቀስቅሷል::

በደብረ ማርቆስና ደምበጫም እንቅስቃሴዎች ቆመዋል:: አማራ ክልል ጦርነቱ አሁንም እንደቀጠለ ሲሆን የአማራ ህዝብ በብርሀኑ ጁላ የሚመራው የኦነግ ሸኔ ሰራዊት ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑ ተሰምቷል::

በጎጃም የተለያዮ ከተማዎች ገብቶ የአማራ አርሶ አደሮችን ሰላም የነሳው ወራሪው የብርህኑ ጁላ ጨፍጫፊ ሀይል በህዝቡ የተባበረ ትግል እየተደመሰሰ ነው:: ቀሪው ደግሞ የቡድንና የግል መሳሪያውን ለ አርሶ አደሩ በማስረከብ እግሬ አውጪኝ እያለ መሸሹን ከቦታው የደረሰን መረጃ ያሳያል::

ከሶስት ቀን በፊት በፍኖተ ሰላም ለአገዛዙ የሚያገለግሉ ቅጥረኞች ላይ ህዝቡ የማያዳግም እርምጃ መውሰዱ ይታወቃል:: በጎጃም የተለያዮ ከተማዎች ህዝቡ ከዳር እስከዳር በመቆጣት የተነሳ ሲሆን አሁንም ከፍተኛ ውጥረት ይስተዋላል::