በጋምቤላ በተቀሰቀሰ ግጭት ሰዎች መገደላቸው ተነገረ

በጋምቤላ ክልል ኢታንግ ልዩ ወረዳ በተቀሰቀሰ ግጭት አምስት ሰዎች መገደላቸው ተነገረ

በጋምቤላ ክልል ኢታንግ ልዩ ወረዳ በሁለት ቀበሌዎች ነዋሪዎች መካከል በተከሰተ ግጭት አምስት ሰዎች መገደላቸውን የልዩ ወረዳው አስተዳደር ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አስታወቀ። በግጭቱ ጉዳት የደረሰባቸው ሰባት ሰዎች ደግሞ በህክምና ላይ መሆናቸውን አስተዳደሩ ገልጿል።

የኑዌር፣ አኝዋ እና ኮሞ ብሔረሰቦች መኖሪያ በሆነው ኢታንግ ልዩ ወረዳ ግጭት የተቀሰቀሰው፤ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ እሁድ ግንቦት 13፤ 2015 መሆኑን የልዩ ወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኡቦንግ ጊሎ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። በዚሁ ዕለት ጠዋት ጀልባ በመቅዘፍ ላይ የነበረ አንድ የሚሊሺያ አባል በጥይት ተመትቶ መገደሉ፤ በልዩ ወረዳው ለተነሳው ግጭት መነሻ ምክንያት መሆኑንም አስረድተዋል።

ጥቃት የተፈጸመበትን የሚሊሺያ አባል ሁኔታ ለመመልከት ወደ ስፍራው የሄዱ የአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ተኩስ ከተከፈተ በኋላ ሁኔታው ወደ ግጭት ማምራቱን አቶ ኡቦንግ ገልጸዋል። ተኩሱን የከፈቱት “ደፈጣ ላይ” የነበሩ ታጣቂዎች መሆናቸውን የጠቀሱት ዋና አስተዳዳሪው፤ ይህን ጥቃት ተከትሎ የአኝዋ እና ኑዌር ብሔረሰቦች መኖሪያ በሆኑ ቀበሌዎች መካከል “ውጊያ” መጀመሩን አብራርተዋል።

ለዝርዝሩ፦ https://ethiopiainsider.com/2023/11031/