ብዙዎች ከእርኩስ መንፈስ ጋር የሚያመሳስሉት ‘ድንገቴ የልብ ምጥ’ በሽታ ምንድነው?

በማይቆጣጠሩት ምክንያት፣ ባልተገመተ ሁኔታ እና ባልጠበቁት ጊዜ የልብ መፍረክረክ፣ የእግር መብረክረክ፣ የሰውነት መራድ ይከሰታል። ድንገተኛ ፍርሃት እና ጭንቅ፣ ጥብ ድንገት ደርሶ ይሰፍርብናል። ያለምንም በቂ ምክንያት መሬት ትከዳለች። አንዳንዶች እንደማዞር ያደርጋቸዋል። አንዳንዶች ያቅለሸልሻቸዋል፤ መሬት እንደ እንዝርት ትሾርባቸዋለች።…