ግብፅ አገራት ሊግን በመጠቀም በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማሳደር የምታደርገው ጥረት በአባይ ወንዝ አጠቃቀም ላይ የተደረሰውን ስምምነትን የጣሰ ነው ስትል ኢትዮጵያ ወቀሰች። የግብፅን አካሄድ “ቀናነት የጎደለው” ሲልም የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ተችቷል። የአረብ ሊግ ኢትዮጵያ ከታላቁ የሕዳሴ ግድብ አንጻር እየወሰደች ካለችው “የተናጥል እርምጃ እንድትቆጠብ” ውሳኔ ማስተላለፉን ተከት…