የሀገር አቀፍ የቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ጉዳይ አስተባባሪ ኮሚቴ ዋና ሰብሳቢ በእስር ላይ እንደሚገኙ ተረጋግጧል።

May be an image of 1 personየሀገር አቀፍ የቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ጉዳይ አስተባባሪ ኮሚቴ ዋና ሰብሳቢ በእስር ላይ እንደሚገኙ ተረጋግጧል።

የነገረ መለኮት ምሩቃን ማኅበር ሰብሳቢና የሀገር አቀፍ የቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ጉዳይ አስተባባሪ ዐቢይ ኮሚቴ ዋና ሰብሳቢ የሆኑት ቀሲስ አክሊሉ ዳምጠው ትናንት ግንቦት 14 ቀን 2015 ዓ.ም በጸጥታ አካላት የተወሰዱ ሲሆን በአኹኑ ሰዓት ሜክሲኮ በሚገኘው የፌደራል ፓሊስ ኮሚሽን ውስጥ እንደሚገኙ እና አስፈላጊውን ሕጋዊ መፍትሔ እንዲያገኙ በጠበቆች በኩል ሙከራ እየተደረገ እንደሚገኝ ከቤተሰቦቻቸው ለማረጋገጥ ችለናል ሲል የማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማዕከል ገልጿል።

ቀሲስ አክሊሉ አብረዋቸው በዐቢይ ኮሚቴው ላይ ከሚያገለግሉት አባላት ጋር በመሆን በማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን በኩል ወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ መስጠታቸው ይታወሳል።

ግንቦት 15 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)