” የሹመቱ ቀን ወደፊት ይገለፃል ” – ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር)

” የሹመቱ ቀን ወደፊት ይገለፃል ” – ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር)

የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የግንቦት 2015 ዓ/ም የርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤን በተመለከተ አጭር መግለጫ ሰጥተዋል።

ምን አሉ ?

– የግንቦት 2015 ዓ/ም የርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ በሰላም እና ደስ በሚል ሁኔታ ተጠናቋል።

– ዛሬ የመጨረሻው አጀንዳ ላይ ብዙ ውይይት ተካሂዷል።

– በመጨረሻ ሁሉም አባቶች ተወያይተው ቤተክርስቲያንን የሚጠቅመው ምንድነው ? የሚለው ላይ በመምከር ዛሬ ውሳኔ ተላልፏል።

– የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት እንዲካሄድ ተወስኗል። የመጀመሪያው ችግር ያለባቸው ሀገረ ስብከት የሚል ሲሆን አሁን 7 አባላት ያሉት ኮሚቴ ተቋቁሟል እነሱ በሚያቀርቡት ጥናት ሹመት ይካሄዳል። የሹመቱ ቀን #ወደፊት ይገለፃል። ዋናው ነገር ለቤተክርስቲያን የሚጠቅመው የትኛው ነው ? የሚለውን የጉባኤው አባላት በሙሉ ተስማምቶ ፣ በአንድ ልብ፣ በአንድ ሃሳብ፣ በመነጋገር ውሳኔ ተላልፏል።

– ረቡዕ የማጠቃላይ መግለጫ በቅዱስ ፓትርያኩ ይሰጣል።

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) ፦

” ብዙ የተጨነቃችሁ ምዕመናን እንዳላችሁ እናውቃለን፤ ምዕመናን በሙሉ ተጨንቃችኃል፤ አንዳንድ ጊዜ እውነት ነው ሌላ ጊዜ ወሬም ብዙ ይበዛል በዚህ ሚዲያ በበዛበት ዘመን በጣም ብዙ የተጨነቃችሁ ምዕመናን እንዳላችሁ እናውቃለን ፤ በእውነት እግዚአብሔርን እናመሰግናለን ግሩም የሆነ የትምህርት ጊዜ፣ ግሩም የሆነ የውይይት ጊዜ ፣ ቤተክርስቲያን ለይተን የምትፈልገው ምንድነው የሚለውን የተወያየንበት ጊዜ ነው እግዚአብሔርን እናመሰግናለን “