
ጌታቸው ሽፈራው የሚከተለውን ከትቧል።
አንድ የማሕበራዊ ድረገፅ ጸሐፊ እንዳሉት ቤት እያፈረሱ ማፈናቀላቸው አጀንዳ ሲሆን 100 ሺህ ቤት እንገነባለን እያሉ ነው። ከሁለት አመት በፊት 500 ሺህ ቤት እንገነባለን ብለው አንድም አልሰሩም። ነዋሪው ከፍሎ ያሰራቸውን ኮንዶሚኒየሞች እንኳን፣ ከባለ ዕጣ ነጥቀው “የአርሶ አደር ልጅ” እያሉ ለራሳቸው ሰው ነው የሰጡት።
ውሸት አያልቅባቸውም። አይደለም አሁን 100 ሺህ ሊሰሩ 1997 በኋላ ዕጣ የወጣላቸውን ከህዝብ ነጥቀዋል። አይደለም ቤት ሊሰሩ በዶዘር እያፈረሱ ነው። ውሸት ነው። አጀንዳ ለማስቀየር ነው።

አዲስ አበባ ለኦሮሞ ብሔርተኞች ጠላት ነች። ዋጋ እንዲንር የሚገባውን ከለከሉ። ሌላውን አቅርቦት እንዲያጣ አደረጉ። ለራሳቸው በተጋነነ ዋጋ አቅራቢ ተኩበት። አሁንም በተመጣጣኝ ዋጋ አይደለም የሚሸጡት። ሰንበት ብለው ደግሞ “ብትገዛ ግዛ፣ ባትገዛ ተወው” የሚባልበት ጣሪያ ይሰቅሉታል።
ጠላት የሚሉት ከተማ ላይ ይህ ቁማር ገበያ ነው። ያስወድዳሉ። አቅርቦት እንዳይኖር ያደርጋሉ። ያተርፉበታል። እየሆነ ያለው ይሄ ነው።
ለባጃጁ ጋሪ አምጥተዋል። ለጤፉ ማሽላም ቢሆን ያቀርባሉ።

አዲስ አበባ የተፈናቀሉ ኦሮሞዎች መጥተው የሚሰፍሩበት፣ አዲስ አበባ የኖሩ አማሮች የሚፈናቀሉበት ሆኗል።
ከአማራ ክልል ነጋዴ፣ ለህክምና የሚመጣ እየከለከሉ ከኦሮሚያ ግን በርካታ ህዝብ መጥቶ ሰፍሯል።
ከኦሮሚያ የተፈናቀሉ አማራዎች አማራ ክልል ሜዳ ላይ ይገኛሉ። አሁን ጭራሽ ባጃጅ ሾፌርን ጨምሮ እየተፈናቀለ ነው። ከኦሮሚያ ግን ተፈናቃይ በመንግስት በጀት ቤት ተሰርቶለታል።
አዲስ አበባ ላይ “የአርሶ አደር ልጅ” እየተባለ በርካታ ህዝብ የቀበሌ ቤት ተሰጥቶታል፣ ኮንዶሚኒየም ተሰጥቶታል። አማራው ደግሞ ከሰራው ቤት እንዲፈናቀል ሆኗል።
