አንቶኒ ብሊንከን ከህወሓት አመራሮች ጋር መወያየታቸውን ገለጹ

በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደረጉት የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር (ሰክሬታሪ) አንቶኒ ብሊንከን ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ በሰጡት መግለጫ ከህወሓት አመራሮች ጋር በአዲስ አበባ ተገናኝተው መምከራቸውን ገለጹ።
አንቶኒ ብሊንከን የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭትን ለመፍታት የሠላም ስምምነት ለፈረሙት ሁለቱም ወገኖች እውቅና ሰጥተዋል። በግጭቱ የተሳተፈው የኤርትራ ጦር ከአካባቢው እየወጣ መሆኑንም ገልጸዋል።
የሰላም ስምምነቱ ተጠናክሮ ከቀጠለ ኢትዮጵያ ወደ አጎዋ የገበያ እድል ዳግም መመለስ የምትችልበት እድል እንደሚኖርም ገልጸዋል።
በተጨማሪም በሂደት ላይ ላለው የሽግግር ፍትህና አገራዊ ምክክሩ አሜሪካ አስፈላጊውን እርዳታ እንደምታደርግም ተናግረዋል።