የአማራ ፋኖ አንድነት ም/ቤት ተመሰረተ

በአራቱም ማዕዘን ተበታትኖ የነበረው አማራ ፋኖ በአንድ ተዋሃደ!

የአማራ ፋኖ አንድነት ም/ቤት መግለጫ:-

የአማራ ፋኖ አንድነት ምክር ቤት ከ4ቱም ማዘናት በተውጣጡ የፋኖ ተወከዬች ማለትም ከ ሽዋ፣ከጎንደር፣ከወሎ እና ከጎዳም በተውጣጡ ብርቅየ የቁርጥቀን ልጆች አማካኚነት የአማራ ፋኖ ተመስርቷል።

መላው የአማራ ህዝብ በጉጉት ሲጠብቀው የነበረው የአማራ ፋኖ አንድነት አንድ ከቡዙ ድካም በኃላ በጎንደር ክፈል ሃገር ህዳር 13/2015 ዓ/ም ሊመሰረት ችሏል።

በምርረታ መረሃ ግብሩ ላይ ተገኚተው ንግግር ያደረጉት ሽህአለቃ ሰፈር መለሰ አማራ ፋኖን አንድ ለማድረግ ከተለያዮ አካባቢዎች የተገኙ ፋኖዎችን አመስግነው አንድነት አተን ብዙ ውርደት እና መከራ ደርሶብናል ብዙ መሳውትነት ከፍለናል አንድነት ሃይል ነው አንድ ከሆንን የሚደፍረን አይኖርም ብለዋል።
አክለውም ስለ እራያና ወልቃይት ጉዳይም አንስተዋል። እኛ በህወት እያለን መሬቻችንን አሳልፈን አንሰጥም በርግጥ ህወት ከተረኛው ጋር በመተባበር መሞከሩ የማይቀር ነው ነገር ግን በዚህ ጉዳይ መንግስትም የሚደፈር አይመስለኚም ሲሉ ተናግረዋል።
በመጨረሻም የምስራቅ አማራ ፋኖ በጦርነቱ ያስመዘገበውን ድል በማውሳች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በቦታው የተገኙት ዶ/ር ወንድወሰንአስፋው በበኩላቸው ጦርርነቱን ያሸነፈው ያማራ ፋኖነው አማራው ደሞዝ ሳይከፈለው በሬውን ሽጦ እራሱን አስታጥቅ ዘምቶ ባሸነፈው ጦርነት የፌድራል መንግስት እና ህዋሃት አማራን በማግለል በአማራ ላይ ተደራድሯል ብለዋል።አክለውም ትጥቅ እፈታለሁ ብሎ የተደራደረው ህዋት አሁን ደግሞ ለዳግም ወረራ እየተዘጋጀ ይገኛል ብለዋል።

በዕለቱ የአማራ ፋኖ አንድነት ምክርቤት የአቋም መግለጫ አውጥቷል።

ከሁሉም ክፍል ሃገራት በተውጣጡ የአማራ የአማራ ሃይል ህዳር 13/2015ዓ/ም የአማራ ፋኖ ምክርቤት ተመስርቷል።
ለዚህ ምስረታ በቀናነት ስታገለግሉ ለነበራችሁ እና የአማራ ሞት መሰደድ ያገባናል የምትሉ ወዳጆቻችን እንኳን ደስ አላችሁ።

ከሁሉም በላይ ስንቅ እና ትጥቅ ለሆናችሁን በውስጥም በውጪም አማራዎች በሙሉ በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንወዳለን።

ፋኖነት በጠብታ ውሃ እየተዋለ ደረቆት እየተቆረጠመ በዱር በገደል በውርጪና በፀሃይ ሃሩር እየታገሉ ሃገር ያስከበሩ የቀደምት አባቶቻችን የእነ አፄ ምኒልክ፣ የእነ በላይ ዘለቀ፣የእነ አፄ ቴወድሮስ፣የእነ ብርጋዴል ጀነራልአሳምነው ፅጌ እርሾ ነው።

ፋኖነት ኢትዮጲያን ከውጪ ወራሪ እና ከውስጥ ባዳ እየተከላከለ ያቆየ የብረት አጥር ነው።

እንሆ እኛም የአባቶቻችን ልጆችነን ጥቅምት 24/2013 ዓ/ም በመከላከያ ሰራውይት ላይ የትግራይ ልዩ ሃይል በፈፀመው ክህደት ክተት ለነፃነት ብለን እኛ የአማራ ፋኖዎች በሬችንን እና ላማችንን ሸጠን በገዛነው ጠመጃ የሃገር መከላከያን ከአፈና አስለቅቀናል።
አገራችን ኢትዮጲያንም ከውርደት ታድገናል።

ወራሪው ትህነግ በዚህ አላቆመም በድጋሜ ወረራ በመጣበት በክረምት ወራት ክተት መክት በሚል ጥሪ ተደርጎልናል ክተት መክት ገጀራህን ይዘህ ውጣ ማርከህ ታጠቅ ተብለናል።ባንጠራም ደራሾቹ እኛ የአማራ ፋኖዎች ከተን ወተናል።

ከሃገር መከላከያ እና ልዩ ሃይል ጋር እኩል ተሰልፈን ያለደሞዝ በራሳችን ስንቅ እና ትጥቅ ታግለናል ደምተናል ፣ቆስለናል መሳውትነትም ከፍለናል በዚህም ማርከን ታጥቀናል ነገር ግን እህል ለሰጠ አፈር፣ወርቅ ለሰጠ ጠጠርእንዲሉ እኛ ፋኖዎች ሃገርን ከውርደት በጠበቅን ለሃገራችንንና ለክልላችን ተጨማሪ አቅም በሆንን ተሰድበናል፣ታስረናል፣ተገድለናል፣ በምክርቤትና በፓርላም ፣በሚድያ ሳይቀር ፋኖ የታጠቀው ጥቁር መሳሪያ መከላከያን ገድሎነው ተብለናል።

እኛም ለከጂ ከጂ ይስጠው ብለን ከክብራችን ሳንወርድ ከከፍታችን ሳንሸራተት እንሆ ዛሬም እየታገል እንገኛለን።

ገዢው መንግስት የአማራ ፋኖን ይዘልፍል ጠላታችን ትህነግም ፋኖን ይፈርጃል እንሆ በዚህ ሰአት እንኳን በጋራ እያጠቁን ይገኛሉ።

የተነሳንለት የአማራ ህዝብ በዚህ ጦርነት ከየትኛውም ክልል በበለጠ ሞቷል፣ወድሞል፣ተጎሳቅሏል በሚያሳዝን ሆኒታ በድርድሩ አልተወከለም ህዝባችን እንደ ህዝብ አልተሳተፈም።ፋኖም ከመከላከያእናልዩ ሃይል ጋርእኩል መሳውትነት ቢከፈልም በዚህ ድርድር ውስጥ ግን አልተጋበዘም።

የአማራ ህዝብ አንድነት በውስጥና በውጪ ያለው በጋራ የወከላቸው
1 ብርጋዴል ጀነራል ተፈራ ማሞ
2 ዶ/ደስአለኚ ጫኔ
3 ዶ/ወንደሰን አሰፋ
4 አቶ ቴወድሮስ ትርፌ
እውነተኛ ያማራ ተወካዩች እናተቆርቋሪ በመሆናቸው እንደ ህዝብ ቅቡልነት ማግኘታቸውን እናውቃለን እኛም እንደማንኛውም ያማራ ህዝብ እንቀበላለን ነገር ግን እኛ ከመከላከያውና ከልዩ ሃይሉ ጋር እኩል ተሰልፈን ዋጋ እንደመክፈላችን መጠንእንደፋኖ በድድሩ ልንወከል ይገባል የሚል ቁርጥ አቋም አለን።

ከዚህ ውጪ በሆነ መንገድ ግን ከአሸባሪው ከአሸባሪው ህዋት ጋር እየተደራደረ ያለው መንግስት ፋኖን ትጥቅ እናስፈታለን ማለት ግን ከአሸባሪወች ጋር በአቻነት እያቀረቡ ፓለቲካ ሰርተን እናተርፋለን ማለት ኢየሱስ ክርስቶስን እና በርቫንን እንደማወዳደር ይቆጠራል።

ዛሬ የአማራ ፋኖ አንድነት ምክርቤት አመራሮቻችንን በመረጥንበትእና ባፀደቅንበት በዚሁ ዕለት የሚቀጥለውን ባለ10 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥተናል።

1 ወልቃይት ጠገዴ ጠለምትና እራያ የመላው የአማራ ህዝብ የፓለቲከ አስኳል ማጠንጠኛ ሲሆኑ ከዚህ በፌት የሄዱት በጉልበት እንጂ በህገመንግስታውይ ውሳኔ ባለመሆኑ እና ፈፅሞ የማንደራደርባቸው ቀይ መሰመሮች ናቸውእጣፋንታችንን በክንዳችን እንወስነዋለን።

2 በመንግስት በኩል የአማራን ህዝብ እውነትኛ ጠባቂ የሆነውን ፋኖን ትጥቁን ለማስፈታትእና ለመበተን የሚሞከር ሃይል የአማራን ህዝብ እጂን አስሬ ለጠላት እንስጥ ከሚል የመነጨ መሆኑን እንደፋኖ እንረዳለን በመሆኑም ይህ ሊተገበር ቀርቶ ሊታሰብ የማይገባ ቀይ መስመር መሆኑን አበክረን ከወዲህሁ አበክረን እንገልፃለን።

3 በሃገራችን በተለያዩ ክልሎች የአማራ ተወላጆችም በማንነታቸው ማፈናቀል፣መግደልና የዘር ጪፍጨፍን በመፈፀም በመንግስት መዋቅር ከጀመረ 32 አመታትን ያስቆጠረ ቢሆንም በተለይም ላለፉት 4 አመታት እየተፈፀመ ያለው የዘር ፍጂት እንደሰደድ እሳት እየተቀጣጠለ ያለውና ህግ መንግስት የሌለው እንዳውም በአንዳንድ አመራሮች መዋቅራውይ ድጋፍ እየተደረገለት መሆኑን እናምናለን።በተለይም በወለጋ፣ መቢሻንጉል ጉምዝ እና በደራ አማራን የማፈናቀልና የማሳደድ መዋቅራውይ ጪፍጨፋውንመንግስት እንዲያስቆም በጥብቅ እንጠይቃለን።

6 የአማራ ፋኖ ለዚች ሃገር ለከፈለው

4 የአማራን ጪፍጨፋ በስሙ በመጥራታቸው ሰበሳ ሰበብ በመፍጠር የታሰሩ ፓለቲከኞች፣ጋዜጠኞችና ፋኖዎች እንደነ አርበኛ የአማራ ምልክት የሆኑ ዘመነ ካሴ አይነት እስረኞች እንዲፈቱ በጥብቅ እንጠይቃለን።

5 በሃገራችን ድርድሩና ምክክሩ የአማራ ሁነኛ ተደራዳሪዎች ህዝብ ያመነባተውና የተቀበላቸው

ብርጋዴል ጀነራል ተፈራ ማሞ
ዶ/ደስአለኚ ጫኔ
ዶ/ወንደሰን አስፋው
አቶ ቴዎድሮስ ትርፌ
ህዝባውይ ቅቡልነት እንዳላቸው ከላይ በመግቢያችን እንደገለፅነው እናምናለን እኛም እንደህዝብ የምንቀበለው ቢሆንም ከታጋዮቹ ከመከላከያ ሰራውይትና ከልዩ ሃይል ጋር እኩል ተሰልፈን በራሳችን ስንቅና ትጥቅ ዋጋ እንደመክፈላችን መጠን እንደፋኖ በድርድሩ ውስጥ ሊካተት ይገባል የሚል ጥያቂያችንን በዚሁ አጋጣሚ እንጠይቃለን።

6 የአማራ ፋኖ በዚች ሃገር ለከፈለው መሳዋትነት እውቅና ሊሰጠው እንደሚገባም እናምናለን መንግስታችን ግን በውሃ ቀጠነ ሰበብ ለመወንጀል የሚያደርገውን ፕሮፖጋንዳ እንዲ

7 በዛሬው ዕለት የተመሰረተው የአማራ አንድነት ምክርቤት አልተጠቃለልነም የሚል ተቀራርበን ለመስራትና የአማራ ያገባናል ከሚሉት ጋር ለመተባበር ፈቃደኛ መሆናችንን ከወዲሁ እንገልፃለን።

8የአማራን ክልል ለመበተንና ለማፈራረስ የሚሰራ ህዝባችንን ከግዙፍ ማንነት ወደ ዳጣን የሚሰራ የፓለቲካ ሴራን ፈፅሞ እንደማንታገስ እንገልፃለን።

9 የተወላገደ አማረኛ የሚናገር አማራ የለም የተወላገደህገ መንግስት ልጫንብህ የሚልእና እኛ እንወቅልህ በሚል አማራ ጠል ትርክት በመፍጠር የአማራን ህዝብ ለመከፍፈል የሚሰራ መንግስታውይ አሻጥርን በጥብቅ እንቃወማለን።

10 የተከበርከው የአማራ ህዝብ ሆይ ዛሬ የመሰረትነው የአማራ ፋኖ አንድነት ምክር ቤት ዋና አላማው የአማራን ህዝብ እንግልት፣ሰቆቃ፣ሞትና ስደት ለመቀልበስ ብርቱ ህብረት የአማራ መዳኛ እንደሚሆን የአማራን ህዝብ ለማዳን ቤቴ ፣ልጄ፣ሚስቴ ሳንል ዱር ቤቴ ድንጋይ ትራሴ ብለን መዳኛህን በአንድ ዕዝ መስርተናል ለዚህም በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ እያልን በመንግስት በኩል የሚፈፀመውን ወከባና ማሳደድ ከፍኖ ጎን በመቆም ለፋኖውም ልክ እንደዚህ ቀደሙ ምሽጋችን፣ ጫካችን፣ ትጥቃችን ስንቃችንእና መሳሪያችን ስለሆናችሁ ፋኖን ከተኩላዎች እንድትጠብቁ በአማ ፋኖ አንድነት ስም ጥሬችንን እናስተላልፋለን።
ፋኖነት በክብር የሚኖር የሚኖርበት የክብር ሰገነት፣የብረት ምሰሶ የአማራነት ራስ ነው።

የአማራ ፋኖ አንድነት ምክር ቤት ምስረታ ጎንደር 13/2015 ዓ/ም።