ግብዣው ቀደም ብሎ ያልደረሰን ከመሆኑ ጋር ተያይዞ አንዳንድ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ይሰጠን – ዶ/ር ደብረጺኦን ገ/ሚካኤል

[addtoany]

ግብዣው ቀደም ብሎ ያልደረሰን ከመሆኑ ጋር ተያይዞ አንዳንድ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ቢሰጠን ሲሉ በፃፉት ደብዳቤ ጠይቀዋል። ህወሓት በደቡብ አፍሪካ የሰላም ድርድር ቢስማማም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ጠይቋል።ህወሓት በደቡብ አፍሪካ በሚደረገው የሰላም ንግግር ላይ ለመሳተፍ ዝግጁ መሆኑን አሳውቋል።ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ቆርጠኞች ነን ሲልም ገልጿል። ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ለአፍሪካ ህብረት ሊቀንበር በፃፉት ደብደቤ ፤ ለሰላም ሂደቱ ይረዳል ያሉትን ” ግጭት ማቆም ” ዋናው የድርድሩ የአጀንዳው አካል ተደርጎ ስለመያዙ ጠይቀዋል።ተደራዳሪዎቻችን ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመላክ ዝግጁ ነን ሲሉም አሳውቀዋል።

ግብዣው ቀደም ብሎ ያልደረሰን ከመሆኑ ጋር ተያይዞ አንዳንድ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ቢሰጠን ሲሉ በፃፉት ደብዳቤ ጠይቀዋል።እነዚህም ፦ በሰላም ውይይቱ ተጨማሪ ተዋናይን እንደ ተሳታፊዎች፣ ታዛቢዎች ወይም ዋስትና ሰጪዎች የሚጋበዙ ይኖሩ እንደሆነ፤ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ምን አይነት ሚናዎችን ሊሰጥ እንደታሰበ ፤ ለተደራዳሪ ቡድኑ የሎጅስቲክስ ፤ #የጉዞ እና የደህንነት ዝግጅቶችን በተመለከተ እንዲብራራላቸው ዶ/ር ደብረፅዮን ለፋኪ በላኩት ደብዳቤ ጠይቀዋል።

አፍሪካ ኅብረት ለሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ትላንት ያቀረበውን የንግግር ግብዣ መንግሥት ተቀብሎታል ሲሉ የመንግሥት ሰላም ተደራዳሪ አባልና የጠቅላይ ሚንስትሩ የብሄራዊ ደኅንነት አማካሪ ሬድዋን ሁሴን በትዊተር ገጻቸው ወዲያው አሳውቀው ነበር። ሬድዋን የኅብረቱ ግብዣ መንግሥት ጦርነቱን “ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ በሰላም ለመፍታት ከያዘው አቋም” ጋር የሚሄድ መሆኑን ገልጸዋል። የመንግሥት ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤትም፣ የኅብረቱ የንግግር ጥሪ መንግሥት “ከዚህ በፊት ያቀረባቸውን አቋሞች የጠበቀ” ነው ሲል የመንግሥትን አቋም ገልጧል። ከአንድ ቀን ቀደም ብሎ ጄኔራል ጻድቃን አሜሪካን አገር የሚገኝ አንድ ተቋም ለውይይት ጋብዟቸው እንደተናገሩት ከጅቡቲው ድርድር በኃላ በኢትዮጵያ መንግስት ክህደት ተፈፅሞብናል ለዛ ነው ጦርነቱን የጀመርነው ሲሉ አማርረው ተናግረው ነበር።

የአፍሪካ ሕብረት የመጀመሪያው ዙር ንግግር፣ የወደፊቱን የድርድር አካሄድ፣ የድርድሩን አጀንዳዎች፣ የድርድሩን ቅርጽና የጊዜ ሰሌዳ የሚመለከት እንደሚሆን ገልጧል። በአፍሪካ ቀንድ የኅብረቱ ልዩ ልዑክ ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ ድርድሩን ይመሩታል ተብሏል። የቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታና የኅብረቱ የሰላምና ደኅንነት አማካሪ የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ፉምዙሌ ንጉካ አወያይ እንደሚሆኑ ከሮይተርስ የዜና ምን ጭ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።