ግንቦት ሰባትና አብን ሊነጋገሩ መሆኑ መልካም ዜና ነው #ግርማካሳ


ኢትዮጵያን ካጋጠሟት እጅግ ውስብስብ ችግሮች ለማዳን የተለያዩ ጠቃሚ ሃሳቦችን እና ገንቢ ትችቶችን የሚያቀርቡ ነፃ ሚዲያዎች ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ ይታወቃል። ስለዚህም ኢትዮ360፣ መረጃ ቲቪ፣ አዲስ ድምጽ፣ ምንሊክ ቲቪ እና ሌሎችም የኢትዮጵያዊነት አጀንዳ የሚያራምዱ ሚዲያዎች በመተባበር ፕሮግራሞቻቸውን በሳተላይት ቲቪ ለኢትዮጵያ ህዝብ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ሚዲያዎች የፈጠሩት ማህበር የሳተላይት ወጪውን መሸፈን እንዲያስችለው ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ ከፍተናል → እዚህ ሊንክ ላይ ይጫኑ። ለትብብርዎ እናመሰግናለን።

ታስሮም፣ ከመታሰሩም በፊት፣ ከታሰረም በኋላ ብዙ ጊዜ ጽፊያለሁ። አንዳርጋቸው የማከብረውና የማምው ሰው ነው።አደርባይና አጨበራባሪ አይዸለም። አዎን ከቅንጅት ወደ ግንቦት ሰባት ሲሄድ፣ የአላማ ሳይሆን የስትራቴጂ ልዩነቶች ስለነበሩኝ፣ እንደ አንዳራጋቸው ሳይሆን እንደ ግንቦት ሰባት አመራር እቃወመው ነበር። ያም ቢሆን ፣ ያመነበትን፣ ሰው ባይቀበልም ሳይፈራ የሚናገር ፣ ኢንቴግሪቲ ያለው ሰው እንደሆነ አውቃለሁ። እኔ ብቻ ሳልሆን ከርሱ ጋር በፖለቲካ አመለካከት የማይስማሙ የማውቃቸው ወገኖችም ተመሳሳይ አመለካከት ነው ያላቸው።

አንዳርጋቸው ከወ/ሮ እማዋይሽ ጋር በድብረ ታቦር ግንቦት ስባትን ወክሎ ህዝባዊ ስብሰባ አድርጓል። ስበሰባዉን ለመረበሽ፣ አንዳንድ ቄሮ መሳይ አክርሪዎች በሶሻል ሜዲያ “ረብሹ፣ በጥብጡ፣ ባነር ንቀሉ ..ወዘተረፈ” እያሉ ርካሽና የወረደ ቅስቀሳ ቢያደርጉም፣ ስብሰባው ግን በሰላም ብዙ ሕዝብ ባለበት ተጠናቋል።

በአንድ ደርጅት ላይ ተቃዉሞ ሊኖር ይችላል። ያ ደርጅት ፣ “እኔ ስለምቃወመው አባላቱንና ደጋፊዎችን መሰብስ የለበት” ከማለት በስብሰው ተገኝቶ ተቃዉሞም ካለ ተቃዉሞን ማቅረብ፣ ጥያቄዎችም መጠየቅ የሰለጠ ፖለቲካ ነው።

በደብረ ታቦሩ ስብሰባ በግንቦት ሰባት ደስተኛ ያልሆኑ ብዙ ወገኖች ተገኝተው አንዳርጋቸው ጽጌን ጠይቀዉታል። ይሄን ጊዜ ሌሎች ቢሆኑ ይሳደቡ፣ arrogantly ምላሽ ይሰጡ ነበር። አንዳርጋቸው ግን ግልጽነት ባለው መልኩ ነው በትህትና ምላሽ የሰጠው።

ሁለት ከተናገራቸው ያስደሰቱኝ መልሶች አሉ። አንደኛው የአብን አመራር ስልክ እንዳለውና ከአብኖች ጋር እንደሚነጋገር መግለጹ ነው። ይሄ ትልቅ ነገር ነው። አብኖች በአማራ ስም ተደራጁ እንጂ የመጨረሻ ግባቸው የአንድነት ሃይሉ የሚፈልገው ለሁሉም እኩል የሆነች ፣ አንዲት ዴሞክራሲያውት ኢትዮጵያን ማየት ነው። አሁን አብን ውስጥ ያሉ የቀድሞ አንድነት፣ መኢአድ፣ ሰማያዊ ሆነው ልከኢትዮጵያ አንድነትና ለኢትዮዮጵያዊነት ሲታገድሉ፣ ሲታሰሩ፣ መከራ ሲቀበሉ የነበሩ ናቸው። አብን ላይ ብዙ ብዙ የግንቦት ሰባት ካድሬዎች አላስፈላጊ የዉሸት ዘመቻዎች ማድረግ ልማዳቸው ነው። ምን አልባት አሁን አቶ አንዳርጋቸው ከአብን ጋር መነጋገሩ ብዙ ቀዳዳዎችን በመድፈን እነዚህ ካድሬዎችን መስመር ሲያዚልን ይችላል ብዬ አምናለሁ።

ሌላው አቶ አንዳርጋቸው ስለ ኦሮሞ ክልል የተናገረው ነው። “በኦሮምያ እንዳንገባ ተከልክለናል ግን ለአቢይ አመልክተናል” ነው ያለው። ዶር አብይ ሁሉንም ነገር ማድረግ አይችልም። ለዶ/ር አብይ ማመልከት ብቻ ሳይሆን ያለውን ሁኔታ በይፋ ለሕዝብ በመናገር ፣ ሕዝብ ይሄንን አፍርና እንዲታገል ሕዝብን ማንቀሳቀስ አስፈላጊ ነው። ለምሳሌ የአሰላ ከንቲባ ሕግ ወጥ በሆነ መንገድ ስብሰባ አይደረግም ብላ በሌላ በኩል የነጃዋርን ስብሰባ ስትፈቅድ፣ የአሰላ፣ መስቀል አታከብሩም ሲባሊ ተድራጅተው እንደተነሱት ለነብታቸው እንዲነሱ ግንቦት ሰባት ምሪት መስጠት ነበረበት። ሕዝብ ተዘጋጅቶ ነበር። ግን የግንቦት ሰባቱ መሪ አፈገፈጉ።

ሕዝብን ማንቀሳቀስ ብቻ አልነበረም። ስብሰባዎች የከለከሉ የኢህዴድ/ኦዴፓ የዞንና ወረዳ ባለስልጣናት ማባባል ሳይሆን (ዶ/ር ብርሃኑ ከአክራሪዋ የአሰላ ከንቲባ ጋር እንዳደረገው) በፍርድ ቤት መክሰስ ያስፈልግ ነበር።

ለማንኛውም ቢያንስ ዶ/ር ብርሃኑ ሊደባብሰው የነበረዉን አቲ አንዳርጋቸው ሕዝብን ሳይደብቅ በኦሮሚያ ያለውን አሳዛኝ ሁኔታ መናገሩ በጣም አስደስቶኛል።

ከፍያለው ጎላ በየነ የተባለ ጦማሪ፣ ” የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጥያቄና መልስ በደብረታቦር” በሚል ከጻፋቸው የተወሰኑትን እንደሚከተለው አቅርቢያለሁ፡

————————-
አቶ አንዳርጋቸውን እንኳን ተፈታህ ለማለት ከጎንደር የተወሰኑ ወረዳዎች የተውጣጡ የመኢአድ አባላት በቦታው ተገኝተዋል። የአርበኞች አባል የነበሩ እና የግንቦት 7 አባላት እንዲሁም የቀድሞ የደርግ ሰራዊት አባላት የነበሩ ግለሰቦች በስብሰባው ተገኝተዋል፡፡ የሚከተሉትን ጥያቄወችም አንስተው ነበር።

1. የሞቱትን ወታደሮች ለቤተሰብ አላረዳችሁም ለምን?
አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ:- ለማርዳት ተቸገርን ፈራን እሬሳ ጭናችሁ አምጡ ብየ ነበር በ8 ሳጥን 78 አፅም አምጥተናል ፡፡

2 . አላማችሁ ምንድን ነው ድሮ አማራ ተደራጅ ትል ነበር ዛሬ ምን ተገኘ ?
አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ:- እኔ አማራና ኦሮሞ ዝርያ ነው ያለኝ አማራ ለመዳን መደራጀት አለበት ብየ የፃፍኩት በአማራ ላይ የሚደርሰው አድሎና በደል አንገፍግፎኝ ስሜታዊ ሁኘ ነበር አሁንም ቢሆን አማራ አይደራጅ አላልኩም ፡፡

3. 100 ሽህ ብር እንሰጣለን እያላችሁ ከገበሬው ትጥቅ ወስዳችኃል ? የግ 7 መታወቂያ እንስጥ እያላችሁ 100 ብር ሽጣችኃል በማለት የሰነድ ማስረጃ ከጋይንት የመጡ ጠያቂ ሲጠይቁ ?
አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ:- እኛ አይደለንም የታችኛው መዋቅር ነው ይሄንን ያደረገው ህገወጥ ነበር፡፡

4. ግንቦት 7 እጣ ፈንታው ምንድን ነው ? አንዲ:- ከሳምንታት በኃላ በይፋ ይፈርሳል ፡፡

5. ግንቦት 7 ለወታደሮቹ እና አባላቱ ሰጠው እያለ አመራሩ ገንዘብ በልቷል አንተ እንዴት አየኸው ?
አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ:- ለኔ ያሉኝ እና የማውቀው 41 ሚሊዬን ብር ለትግሉ ለእናንተ እንደተሰራጨ ነው በየቦታው ግን አልደረሰንም ይለኛል ሰው ስለዚህ የተበላ ነገር ደረሰኝ የለውም እንዴት እንወቀው ፡፡

6. በሌሎች ክልሎች እንዳትገቡ ተከልክላችኃል ለምን በኢትዬጵያዊነቱ የማይደራደረውን አማራ ታደነዝዛላችሁ አማራን አሞኛችሁት ?
አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ:- እንዳላችሁት በኦሮምያ እንዳንገባ ተከልክለናል ግን ለአቢይ አመልክተናል ፡፡

7. የሻለቃ መሳፍንት /ገብርየ/ ግድያ አሁንም ሚስጥር ነው ለምን ?
አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ:- እጅግ በጣም ጀግና ነበር ከእስር ስወጣ መጀመሪያ ስጠይቅ ሞቷል አሉኝ በሴራ ነው የተገደለው እርስ በርሳችን ከውስጥ ችግር ነበር ፡፡

8. ወደፊት ዓላማችሁ ምንድን ነው ?
አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ:-ሌላ ፓርቲ ማቋቋም እኔ ግን ደክሞኛል አርጅቻለሁ ወጣቶቹ ተተኩ ፡፡

9. ከሌሎች የአማራ ፓርቲወች ጋር እንዴት ትሰራላችሁ?
አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ:- ስለአማራ የተቋቋመው አብን ብቻ ነው የአንዱን ስራ አስፈፃሚ ስልክ ይዣለሁ ላነጋግራቸው ነው የተማሩና የተሻሉ ልጆች ስላሉ በየወረዳው ቢመረጡ አማራ ክልልን ሊወክሉ ይችላሉ ፡፡

10. አማራ አይደራጅ እያላችሁ ከኦነግ ጋር ትብብር ፈጥራችኃል የብሔር ፓለቲካ አይጠቅምም የምትሉት አማራን ብቻ ነው ?
አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ:- አሁን ትተናል ፡፡

11. ወረታ ካምፕ የገቡት ወታደሮች ለርሃብና ችግር ተጋልጠዋል አብዛኛዎቹም ወደ በርሃ ሸቀል ተበትነዋል ለምን ?
አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ:- ዛሬ የመጣሁት ለነሱ ነው ተነጋግረን ችግሩ ይፈታል።