
፟
ስዊድን ይህንን ርምጃ እንደምትወስድ የተገለፀው በስዊድን የሚኖሩ ኢትዮጵያውን፤ በኢትዮጵያ በአማራ ላይ እየተፈፀመ ያለውን ጅምላ ጭፍጨፋ በሰነዶች አስደግፈው አቅርበው ሲያበቁ ሁኔታው ከተጣራ በኋላ ነው።
፟
የሰብአዊ መብት ተሟጋቾቹ ኢትዮጵያውያን ወንድማገኝ እጅጉ፣ አሕመድ አሊ፣ ናኩራ ኤፍሬም፣ ትዕግሥት መልሳቸው (ዶ/ር)፣ ኤልያስ አባይነህ፣ ይልማ ሺኩር ለስዊደን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሰነዱን እና ማብራሪያውን ባቀረቡ በጥቂት ቀናት ልዩነት ነው ከላይ የተገለፀውን ውሳኔ የሀገሪቱ መንግሥት የወሰነው።
ኢትዮጵያውያኑ ከዚህ ቀደምም በኢትዮጵያ እየተፈፀመ ስላለው ብሔር ተኮር የመብቶች ረገጣ እና ግድያ ለስዊድን የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ማሳወቃቸው ይታወሳል። (ምንጭ – ባልደራስ)
–
