በሆሮ ጉድሩ ዞን የኦነግ ሸኔ አባል መገደሉን ተከትሎ የቡድኑ ደጋፊ ቄሮዎች አማራዎችን እያሳደዱ መሆኑ ተገለጸ።

በሆሮ ጉድሩ ዞን አሙሩ ወረዳ በገጠር ቀበሌ አንድ የኦነግ ሸኔ አባል መገደሉን ተከትሎ የቡድኑ ደጋፊ ቄሮዎች አማራዎችን እያሳደዱ መሆኑ ተገለጸ።

በሆሮ ጉድሩ ዞን አሙሩ ወረዳ በገጠር ቀበሌ አንድ የኦነግ ሸኔ አባል መገደሉን ተከትሎ የቡድኑ ደጋፊ ቄሮዎች ያለበደላቸውና በማያውቁት ነገር አማራዎችን እያሳደዱ መሆኑን አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ለመረዳት ችሏል።

አንድ የአሸባሪው እና ወራሪው ኦነግ ሸኔ አባል ከአሙሩ ከተማ 2 ሰዓት በሚወስድ የገጠር አካባቢ ባለበት በጸጥታ አካላት መገደሉ ተሰምቷል።

አስከሬኑ ወደ አሙሩ ከተማ መምጣቱን ተከትሎ የሽብር ቡድኑ ደጋፊ ቄሮዎች አማራዎች በማያውቁትና በሌሉበት ነገር እንዳስገደሉ አድርገው በውሸት በማስወራት በከተማው እየዞሩ ቤታቸውን በድንጋይ በመደብደብ እና በማፈናቀል ላይ ናቸው።

ከቀብር በኋላም ከፍተኛ ጥቃት ይፈጸምብናል የሚል ስጋት እንዳላቸውም ገልጸዋል።

አሚማ ከጥቃቱ ያመለጡ አባትን እና በከበባ ስር ያሉ እናትን አነጋግሮ እንደተረዳው በአካባቢው ያሉ የፌደራል ፖሊስ አባላት ደርሰው እየታደጓቸው አይደለም።

አሚማ የአንድ ተሳዳጅ አባትን ስልክ ከቤተሰብ ተቀብሎ ቢደውልም ስልካቸው በገዳዮች እጅ መግባቱን አረጋግጧል፤ ሰውዬ ስለመገደላቸውና ስለማምለጣቸው ለጊዜው በቂ መረጃ ለማግኘት አልተቻለም።

 አሚማ