-
በአዲስ አበባ በርካታ የባልደራስ እባላት ዛሬ እየታደኑ ነውየታሰሩት ቤታቸው ተፈትሿል፣ እየተፈተሸ ነው!
- የባልደራሱ ፍቅረ ማርያም ሙላቱ በድጋሜ ታሰረ፣ ሌሎች አባላትም እየተዋከቡ ናቸው!
- “ፖሊስ ሊያስተናግደን ፈቃደኛ አይደለም” የብ/ጀኔራል ተፈራ ማሞ ባለቤት!
- የግፍ እስረኛው ቢንያም ታደሰ ለግንቦት 19 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠው!
- በሌሊት እየጠራ እንደሚመረምረው ፖሊስ አምኗል!
- የባልደራሶቹ ሰሎሞን አላምኔ እና አቤል ሰሎሞን በድጋሜ ታሰሩ!፣ ሌሎች እየታደኑ ናቸው
- ባልደራሰ ኦሮሚያ እየፈፀመ ስላለው የዘር ፍጅት ዛሬ በኒውዮርክ ለተ.መ.ድ. አቤቱታ ያቀርባል!
በሌሊት እየጠራ እንደሚመረምረው ፖሊስ አምኗል!የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) አባል የሆነው ወጣት ቢንያም ታደሰ ዛሬ ማክሰኞ፤ ግንቦት 9 ቀን 2014 ዓ.ም. የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ወንጀል ችሎት ከጠበቃው ቤተማርያም አለማየሁ ጋር ቀርቧል።
ባለፈው ቀጠሮ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን ለማሰባሰብ በሚል ሰበብ የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ የተፈቀደለት የአዲስ አበባ ፖሊስ ዛሬም በተመሳሳይ 14 ቀናት ጠይቋል። ሆኖም ባለፉት ሁለት ሳምንታት የሰበሰበውና ለችሎቱ ያቀረበው አንዳች ማስረጃ የለም።
ጠበቃ ቤተማርያም አለማየሁ ፖሊስ ቢንያምን በሌሊት ከእንቅልፍ ቀስቅሶ እያስወጣ ከባልደራስ እና ከእስክንድር ነጋ እንዲርቅ በኃይል ለማሳመን እየሞከረ መሆኑን ገልፀዋል። ለአራት ቀናት ያህል በሌሊት እየተጠራ ሲንገላታ እንደሰነበተም ቢንያም ተናግሯል።
ፖሊስ በበኩሉ “በሌሊት የምንጠራው 24 ሰዓት ስለምንሠራ ነው” ሲል አፊዟል። በቀጣዮቹ የምርመራ ጊዜያት የወጣቱን የፌስቡክ ገፅ በብሔራዊ መረጃና ደህንነት መሥሪያ ቤት እንደሚያስመረምርም ተናግሯል።
ለዚህ ምላሽ የሰጠው ቢኒያም፣ “እያንዳዳቸውን ፅሁፎች በፖሊስ ከፋችነት አብረን አንብበናቸዋል። ስለዚህ ከፖሊስ የተሰወረ ስላልሆነ ወደ ደህንነት መሥሪያ ቤት መላኩ አስፈላጊ አልይደለም። ፖሊስ ሆን ብሎ በሀሰት ክስ እኔን በእስር ቤት ለማቆየት ስለፈለገ ነው” ብሏል።
በፌስቡክ ሃሳብን መግለፅ በሕገ መንግሥት አንቀፅ 29 የተደነገገ መሆኑን የገለፁት ጠበቃ ቤተማርያም ፣ የግፍ እስረኛው በዋስትና እንዲፈታ ጠይቀዋል። ሆኖም ፍርድ ቤቱ ውድቅ አድርጎታል። ቢኒያም እስከ ግንቦት 19 በእስር እንዲቆይም ወስኗል።
ቢንያም ታደሰ በጎንደር ተከስቶ የነበረውን ግጭት ተከትሎ በአዲስ አበባ “ኦርቶዶክስ ተነስ በማለት ሁከትና ብጥብጥ ፈጥረሃል” በሚል የሀሰት ውንጀላ ነበር የታሰረው። ተፈፀመ ስላለው ብጥብጥ ማስረጃ ማቅረብ ያልቻለው ፖሊስ፣ በዛሬ ችሎት ደግሞ ውንጀላውን በማህበራዊ ሚዲያ ወደ አስተላለፋቸው መልዕክቶች እያዞረው ይገኛል።