ጄኔራል ተፈራ እስሩን ለምዶታል ያለፈበትም ነው፤ የሚያሳስበን የጤናው ሁኔታ ነው – ባለቤታቸው ወ/ሮ መነን ኃይሌ

ባለቤታቸው ወ/ሮ መነን ኃይሌ ጄኔራል ተፈራ ማሞ ባለትዳር እና የአራት ልጆች አባት ናቸው። ጄኔራል ተፈራ የስኳር ሕመምተኛ መሆናቸውን የገለፁት ባለቤታቸው የታዘላቸውን መድኃኒት እየወሰዱ አንደነበር አመልክተው፣ መድኃኒታቸውን ካልወሰዱ አንደሚታመሙ በመጥቀስ ስጋት ውስጥ መሆናቸውን ባለቤታቸው ተናግረዋል። ከሚኖሩበት ባሕርዳር ወደ አዲስ አበባ የመጡት በእግራቸው ውስጥ የሚገኙትን ጥይቶች በተመለከተ የሕክምና ክትትል ለማድረግ እንደነበረም ጨምረው አስረድተዋል። “እስሩን ለምዶታል ያለፈበትም ነው፤ የሚያሳስበን ጤናው ሁኔታ ነው” ብለዋል።

ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ አዲስ አበባ ውስጥ ከቤታቸው እንደወጡ አለመመለሳቸውን ባለቤታቸው ወ/ሮ መነን ኃይሌ ለቢቢሲ ገለፁ።

ወ/ሮ መነን ስለ ባለቤታቸው ሲናገሩ ትናንት ሰኞ ግንቦት 08/2014 ዓ.ም. ከቤታቸው 5፡15 አካባቢ የወጡት ከጓደኛቸው ጋር ቀጠሮ እንደነበራቸው ገልፀው መሆኑን ያስረዳሉ።

ከዚያ በኋላ ግን ወደ ቤታቸው ባለመመለሳቸው ደጋግመው ወደ ተንቀሳቃሽ ስልካቸው ቢደውሉም ምላሽ አለማግኘታቸውን ይናገራሉ።

ጄኔራል ተፈራ ከዚህ ቀደም በአማራ ክልል የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም በቅርቡ የክልሉ ልዩ ኃይል አዛዥ ሆነው መስራታቸው ይታወሳል ።

እንደ ወ/ሮ መነን ገለፃ ከሆነ ጄኔራል ተፈራ ያገኟቸው ሰዎች በዕለቱ አስከ 10 ሰዓት ድረስ አብረው መቆየታቸውን እና ከዚያ በኋላ እንደተለያዩ ነግረዋቸዋል።

ከዚያ በኋላ ግን የደረሱበትን ለማወቅ እንዳልቻሉ ባለቤታቸው ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።

ጄኔራል ተፈራ ሞሞ ከአማራ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥነት ከተነሱ በኋላ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ላይ በመቅረብ አስተያየታቸውን ይሰጡ ነበር።

ወ/ሮ መነን የባለቤታቸውን መጥፋት አስመልክቶ ወደ ፌደራል ወንጀል ምርመራ እንዲሁም አዲስ አበባ ፖሊስ በመሄድ ቢጠይቁም ግለሰቡ “በቁጥጥራቸው ስር እንደማይገኝ” እንደገለፁላቸው ይናገራሉ።

በአሁኑ ሰዓትም ባለቤታቸውን ለማግኘት ሊኖሩበት ይችላሉ ወደተባሉ የተለያዩ የደኅንነትና የፀጥታ ተቋማት በመሄድ ፍለጋቸውን መቀጠላቸውን ጨምረው ገልፀዋል።

ጄኔራል ተፈራ ማሞ ባለትዳር እና የአራት ልጆች አባት ናቸው።

ጄኔራል ተፈራ የስኳር ሕመምተኛ መሆናቸውን የገለፁት ባለቤታቸው የታዘላቸውን መድኃኒት እየወሰዱ አንደነበር አመልክተው፣ መድኃኒታቸውን ካልወሰዱ አንደሚታመሙ በመጥቀስ ስጋት ውስጥ መሆናቸውን ባለቤታቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ከሚኖሩበት ባሕርዳር ወደ አዲስ አበባ የመጡት በእግራቸው ውስጥ የሚገኙትን ጥይቶች በተመለከተ የሕክምና ክትትል ለማድረግ እንደነበረም ጨምረው አስረድተዋል።

“እስሩን ለምዶታል ያለፈበትም ነው፤ የሚያሳስበን ጤናው ሁኔታ ነው” ብለዋል።

የጄነራሉን መሰወር በተመለከተ የፌደራልም ሆነ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስካሁን ያሉት ነገር የለም።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባል ሆነው ለዓመታት በከፍተኛ መኮንንነት ያገለገሉት ብርጋዲዬር ጄነራል ተፈራ ማሞ ከአስር ዓመት በፊት መፈንቅለ መንግሥት ለማካሄድ አሲረዋል በሚል ከሌሎች ጋር ተከሰው ለዓመታት በአስር ላይ ቆይተዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስተዳደር ወደ ሥልጣን መምጣቱን ተከትሎም ከእስር ተለቀው በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

በቅርቡም የህወሓት ኃይሎች ወደ አማራና አፋር ክልሎች በመግባት ጥቃት በሰነዘሩበት ጊዜ የክልሉን ልዩ ኃይል በበላይነት ሲመሩ የነበሩ ሲሆን፣ ከጥቂት ወራት በፊት ደግሞ ከዚሁ ኃላፊነታቸው እንዲነሱ መደረጋቸው ይታወሳል።

~ብ/ጀ ተፈራ ማሞ በጭንቅ ወቅት “ና አግዘን” ሲባል ሰተት ብሎ የገባ ባለውለታ ነው!

~ወታደራዊ መኮንኖች ከትህነግ ገንዘብ እንደገባላቸው መንግስትም አምኗል። ጄ/ል ተፈራ ከእነዛ መኮንኖች በተቃራኒ ነው። አንዳንዶች ድልን በገንዘብ ሲሸጡ ተፈራ ማሞ ሽንፈትን በሕይወቱ ለመለወጥ ከተራ ወታደሩ ጋር የከረመ ጀግና ነው። የአሸባሪው ተላላኪዎች “በ50 ሜትር ርቀት ውስጥ ነበር” እያሉ ሲናገሩ የሰማነው ነው።

~የፌደራል ባለስልጣናት ከመከላከያ መኮንኖች ያልተናነሰ ለተፈራ ሲደውሉ መክረማቸውን የማይሰማ ከመሰላቸው ተሳስተዋል። ግንባር ላይ ስለከረመ ነው።

~ ተፈራ እንደ ድፍረቱ ግልፅ ነው። የነበረውን ይናገራል። እጅግ የሚያሳዝነው ጦርነት የቀለበሰው ጀግናው ተፈራ የታፈነው ጦርነቱን ያስጀመሩት የትህነግ ፖለቲከኞችና ወታደራዊ አዛዦችን በፈታ ኃይል መሆኑ ነው።

~በተሾመበት ቦታ የገጠመውን ችግር ለሚዲያ በመናገር ተፈራ ቀዳሚው አይደለም። እነ ከማል ገልቹ ኦነግ ሸኔን የሚደግፈው መንግስት ነው እስከማለት ደርሰዋል። የመንግስትን ጥብቅ ሚስጥሮች ተናግረዋል። የነካቸው ግን የለም። ተፈራ የተናገረው ለሕዝብ ደሕነት ይጠቅማል ያለውን ነው። ይህ የሚያስከፋው ትህነግና ኃላፊነቱን ያልተወጣ ኃይል ብቻ ነው።

ተፈራ ትህነግ የሚቆጣጠረው ከተማ ውስጥ ቢታፈን አያስገርምም። ተፈራ የታፈነው አዲስ አበባ ላይ። አሸባሪው ሊይዛት ሲያሰፈስፍ ተፈራ ወሎና ሸዋ ላይ ታግሎ ያተረፋት ከተማ ውስጥ ነው የታፈነው። ይህን የሚያደርጉት ሌላ መገለጫ የላቸውም። ከአሸባሪው ህወሃት ጋር የጋራ አላማ ያላቸው ካልሆኑ በስተቀር።

ይህ አፈና እየደገ ብ/ጄ ተፈራ ማሞ ላይ ደርሷል። ይህ ነውር አድጎ ከዛሬ ደርሷል። በአስቸኳይ መቆም አለበት። ብ/ጄ ተፈራ ማሞን በአስቸኳይ ፍቱት።