ባለፉት 50 አመታት ሲገዘገዝ የነበረውን አማራነት ከፈዘዘበት ቀስቅሰነዋል – አርበኛ ዘመነ ካሴ ።

ባለፉት 50 አመታት ሲገዘገዝ የነበረውን አማራነት ከፈዘዘበት ቀስቅሰነዋል አርበኛ ዘመነ ካሴ ።

ከውጭም፣ ከውስጥም ከእየ ጉድጓዱ ተጠራርቶ የመጣውን ጠላታችንን በሃይላችን እንበትነዋለን ያሉት አርበኛ ዘመነ አዲሱ የአማራ ትውልድ ባለፉት 50 አመታት ሲገዘገዝ የነበረውን አማራነት ነው ከፈዘዘበት እንደገና ቀስቅሰን ያስነሳነው፣ የተጠራቀመውን የፖለቲካ ክፋት አቧራ ነው አራግፈን እንዲያንፀባርቅ ያደረግነው፣ የጠወለገውን ቅጠል ነው እንደገና ውሃ ፈሶበት እንዲለመልም ያደረግነው ብለዋል።

ፋኖነት እና አርበኝነት የሚባሉ የአማራ እሴቶች እንዲጠፉ ተደርጎ ነበር። ይሄን አሁን እየመለስነው ነው። የአማራነት እሴታችንን አድሰናል ሲልም አክሏል አርበኛ እና ፋኖ

ፋኖ በመላው አማራ ውስጥ አለ። ፋኖነት ኢትዮጵያን ከመፍረስ የሚታደግ አስተሳሰብ ላይ የተመሰረተ አማራዊ መዋቅር ነው ። አስተሳሰብንና አላማን መሰረት ያደረገ የትውልድ አዲስ ቀመር ተምጦ ይወለዳል። ፋኖነት በጆግራፊ ወይም በወንዝ የተገደበ አይደለም፤ ውጤታማ ነን ። ፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴ

የፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴ ቃል !!ዘመነ ካሴ ከEthio 360 በነበረዉ ቆይታ። -> https://mereja.com/video2/watch.php?vid=fa77e4201