የፕሮፌሰር አስመረት አስፋው ሹመት በመወሰኛ ም/ቤት ጸደቀ

ትውልደ ኤርትራ አሜሪካዊት ፕሮፌሰር አስመረት አስፋው የዩናይትድ ስቴትስ ኢነርጂ ሚኒስቴር የሳይንስ ክፍል ኃላፊነት ሹመት በመወሰኛ ምክር ቤት ጸደቀ።

የዩናይትድ ስቴትስ ኢነርጂ ሚኒስቴር የሳይንስ ክፍል ኃላፊነት የታጩት ትውልደ ኤርትራ አሜሪካዊት ፕሮፌሰር አስመረት አስፋው ሹመታቸው በትናንትናው ዕለት በህግ መወሰኛ ምክር ቤት ጸድቆላቸዋል።

ባለፈው ዓመት ሚያዚያ ወር ላይ በዕጩነት የቀረቡት በካሊፎርንያ ዩኒቨርሲቲ መርስድ መምሕርት እና ተመራማሪዋ የባዮኬሚስትሪ ትምህርት ክፍሉም ተተባባቂ ዲን የሆኑት ፕሮፌሰር አስመረት 54 በ45 በሆነ ብልጫ የሴኔቱን ድምፅ አግኝተው ሹመታቸው ጸድቆላቸዋል።

ትውልደ ኤርትራ አሜሪካዊት ፕሮፌሰር አስመረት አስፋው