ትግራይ አለቅጥ የናረዉ የምግብ ሸቀጦች ዋጋ ለሕዝቡ ኑሮ የቀውስ ቀውስ ፈጥሯል ተባለ

DW ፡ በጦርነት እና እገዳ ከሌላዉ የኢትዮጵያ ክፍል በተገለለችዉ ትግራይ አለቅጥ የናረዉ የምግብ ሸቀጦች ዋጋ የሕዝቡን ኑሮ እያቃወሰዉ መሆኑ ተዘገበ።የመቀሌዉ ወኪላችን ሚሊዮን ኃይለ ስሳሌ እንደዘገበዉ መቀሌ ዉስጥ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ 5 ብር ይሸጥ የነበረዉ 50 ግራም ዳቦ (ፉርኖ) ሰሞኑን 8 ብር ገብቷል።የፉርኖ ዱቄት፣የጤፍ፣ የበርበሬና የመሰል የምግብ ሸቀጦች ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ ሲጨምር ማኮሮኒና ፓስታን የመሳሰሉ የፋብሪካ ምርቶችን ገበያ ላይ ማግኘት ሲበዛ ከባድ ነዉ።የዚያኑ ያክል እዚያዉ ትግራይ የሚመረቱ እንደ ሽንኩርትና ቲማቲም የመሳሰሉ ማጣፈጫዎች ዋጋ ብዙ ለዉጥ አላሳየም።የከብትና የስጋ ዋጋ ግን ቀንሷል።