“አዲስ አበባ ውስጥ ኦሮሚኛ የሥራ ቋንቋ ይሁን ከተባለ፣ አማርኛ ደግሞ ኦሮሚያ ውስጥ የሥራ ቋንቋ መሆን አለበት! – እስክንድር ነጋ

አዲስ አበባ ውስጥ ኦሮሚኛ የሥራ ቋንቋ ይሁን ከተባለ፣ አማርኛ ደግሞ ኦሮሚያ ውስጥ የሥራ ቋንቋ መሆን አለበት!”በዚህ ረገድ የምናየው ከሆነ ጥያቄው እንዲያውም የኦሮሚያ ክልል ይብሳል፡፡ ነዋሪዎች ከመላው አገሪቱ የሚሰባሰቡበት ክልል ኦሮሚያ ነው፡፡

በቅርባችን ያሉትን ናዝሬትና ደብረ ዘይት ተመልከት፡፡ በኦሮሚያ ውስጥ ያሉት አብዛኞቹ ከተሞች ውስጥ ያለ አብዛኛው ሕዝብ ኦሮሚኛ አይችልም፡፡ ይኼ ጥያቄ የሚነሳ ከሆነ በአዲስ አበባ ብቻ አይደለም የሚነሳው፡፡ ከማንም በላይ የሚነሳው ኦሮሚያ ውስጥ ነው፡፡

ኦሮሚያ ውስጥ ከኦሮሚኛ ውጪ አማርኛም የሥራ ቋንቋ ይሁን ተብሎ ተነስቶ ያውቃል እንዴ? የምናነሳው ከሆነ ስለአዲስ አበባ ብቻ አይደለም የምናነሳው፣ ከማንም በላይ ስለ ኦሮሚያ እናነሳለን፡፡

አዲስ አበባ ውስጥ ኦሮሚኛ የሥራ ቋንቋ ይሁን ከተባለ፣ አማርኛ ደግሞ ኦሮሚያ ውስጥ በክልል ደረጃ የሥራ ቋንቋ መሆን አለበት፡፡ ይኼ ጥያቄ ያለው በሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ አለ፡፡