የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ሊያበቃ የተቃረበ ከ100 ሚሊየን የሚበልጡ የኮቪድ 19 ክትባቶችን አንፈልግም – ድሃ ሃገራት

የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ሊያበቃ የተቃረበ ከ100 ሚሊየን የሚበልጡ የኮቪድ 19 ክትባቶችን ድሃ ሃገራት አንፈልግም ማለታቸውን የተመ የሕጻናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ አመለከተ።

Poorer nations forced to dump close-to-expiry COVID vaccines

More than 100 million doses of COVID vaccines were rejected in December, says UNICEF official, while 681 million shipped doses are unused in about 90 countries.

ጊዜያቸው ሊያበቃ መሆኑ የተነገረው ክትባቶች ባለፈው ታኅሣስ ወር ብቻ በዓለም አቀፉ የክትባት መርሃግብር ኮቫክስ አማካኝነት የቀረቡ እንደነበሩ የዩኒሴፍ የአቅርቦት ዘርፍ ዳይሬክተር ኢትሌቫ ካዲል ለአውሮጳ ፓርላማ ገልጸዋል። የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ሊያበቃ የተቃረበው አንድም ተቀባዮቹ ሃገራት ክትባቱን የሚያቆዩበት አመቺ ሁኔታ ካለመኖሩ ጋር እንደሚገናኝም ነው ያመለከቱት።

ለሁሉም እንዲዳረስ የቆዩ ክትባቶች ምክንያት እንዳይሆኑ በቅርቡ የተዘጋጁትን የመላክ ዝግጅቶች መኖራቸውም ተገልጿል። ዘገባው እንደሚለው በአብዛኞቹ ሃገራት ክትባቶቹ በእርዳታ ቢቀርቡም ያለመከተብ አዝማምያ በመኖሩ በወቅቱ ሥራ ላይ እንዳይውሉ ሌላው ምክንያት ነው።

የዩኒሴፍ መረጃ እንዳመለከተው 681 ሚሊየን ክትባት በአሁኑ ጊዜ በ90 ደሃ ሃገራት ተከማችቶ ይገኛል። በብዙዎቹ ሃገራት ለምሳሌ እንደ ዴሞክራቲክ ኮንጎ እና ናይጀሪያ ባሉት አብዛኛው ክትባት ሥራ ላይ አልዋለም። የዓለም የጤና ድርጅት እንደሚለው በያዝነው ጥር ወር በበለጸጉት ሃገራት 67 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ ክትባት ያገኘ ሲሆን በድሀ ሃገራት ግን ገና 8 በመቶው ብቻ ነው የተከተበው።

https://www.aljazeera.com/news/2022/1/13/poorer-nations-dump-close-to-expiry-covid-vaccines-unicef