በአፋር አብዓላ ግንባር ከማለዳ ጀምሮ ከሕወሓት ጋር ውጊያ እየተደረገ ነው

Imageከአፋር አብዓላ የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው ከማለዳው ጀምሮ ከባድ ውጊያ እየተካሄደ ነው ። የሕወሓት ጦር በቁጥጥሩ ስር አውለዋቸው የነበሩት ስትራቴጂካዊ ቦታዎችና ለመዘዋወር ምቹ የሆኑ ተራራማ መስመሮች በመከላከያና በአፋር ልዩ ኃይል ቁጥጥር ሰር ውለዋል።

የሕወሓት ሰራዊት በከባድ መሳሪያ ተኩስ የጀመረው የማለዳው ውጊያ እስከ ከሰዐት በኃላ ቀጥሎ የሕወሓት ታጣቂዎች ከባድ መሳሪያዎቻቸውን ጥለው ወደኃላ ማፈግፈጋቸውን እና ከፍተኛ ዋጋ ከፍለው ገፍተው ሊመጡ ያሰቡት ሁኔታዎች ስላልተሳኩላቸው በርካቶች ሙትና ቁስለኛ ሆነዋል።

የጥምር ጦሩ በርካታ ቦታዎችን በማስለቀቅ የጠላትን ጦር እየደመሰሰ ሲሆን የሕወሓት ታጣቂዎች በርካቶች ምርኮኛ ሆነዋል፤ ሌሎች ደግሞ ከጦር አመራሮቹ ጋር ሸሽተው ወደ ትግራያ እየተመለሱ ሲሆን የተወሰነው ጦር ካለአመራሩ ውጊያውን
ቀጥለዋል ።