ከኖርዌይና ከአሜሪካ የመጡ ዲያስፖራዎች ጫካ ተገኝተው የኦነግ ሸኔን ታጣቂዎች መጎብኘታቸውንና ቁሳቁሶችን መርዳታቸው ተሰምቷል።

በኦሮሚያ አራቱን የወለጋ ዞኖችና በምዕራብና ሰሜን ሸዋ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በማሕበረሰቡ ላይ ከፍተኛ ጥቃት እያደረሱ ይገኛሉ

( ማስረጃ የሚሆኑ ሶስት ቪዲዮዎችን ይዘናል ከታች ያገኙታል)

በኦሮሚያ ክልል በምስራቅና ምዕራብ ወለጋ ፣ በሆሮጉዱሩ ወላጋና በቄሌም ወለጋ ዞኖችና በምዕራብና ሰሜን ሸዋ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ከፍተኛ ጥቃት በማሕበረሰቡ ላይ እየፈፀሙ እንደሚገኙ በየኛ ቲቪ ላይ የተላለፈ አንድ ዘገባ አስታውቋል። ይህ ዘገባ በስፋት የዳሰሰው በወለጋ የሚደረገውን ጥቃት ለመንግስት ጥቆማ ለመስጠት እንደሆነ ገልጿል።

ሰሞኑን የተገኙት መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በጠቅላይ ሚኒስትር አብይን የዲያስፖራ ጥሪ ተቀብለው ወደ ሃገር ቤት ከኖርዌይና ከአሜሪካ የመጡ ዲያስፖራዎች የኦነግ ሸኔን ታጣቂዎች መጎብኘታቸውንና አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶችን መርዳታቸውን የኛ ቲቪ ያገኘው የቪዲዮ ማስረጃ ይፋ ሆኗል። ዲያስፖራዎቹ ይህን ሁሉ ካርቶኖች የመድሃኒትና የአልባሳት ድጋፍ በጅቡቲ በኩል ወይም በኬንያ አሊያም በኤርፖርት ይዘውት እንድገቡ ማስረጃው በመጣራት ላይ ነው።

በምዕራብ ሸዋ በደራና አከባቢዎች እንዲሁም በጅማና በወለጋ አራቱም ዞኖች መንግስት የማይገባባቸውና ኦነግ ሸኔ የራሱን አደረጃጀትና መዋቅር በመፍተር ማሰልተኛ ካምፕ በመክፈት በተለይ ቆፍቆፍቲ በሚባል በከተማ ውስጥ ወዳለው ማሰልጠኛ ወጣቶችን እየወሰዱ በማሰልተን ላይ ሲሆኑ በቆፍቆፍቲ ከተማ የሚገኙ የሕንድ ኢንቨስተሮችንና የመንግስት ተቋማት ንብረቶችን ወርሰዋል። በርካታ ፒካፕና አምፑላሶችን ወርሰዋል። በተለይ ከመንግስት ንብረት በላይ አማርኛ ተናጋሪ የሆኑ ነዋሪዎችን ንብረትና መኪናዎች እየወረሱ ነው።

አራቱን የወለጋ መንገዶችን ከሌሎች አከባቢዎች የሚያገናኘው በቅርቡ የተመረቀው ሻምቡ ባኩ አውራ መንገድ ሶስት ዞኖችን ወለጋን ከሸዋና ሌሎች ወረዳዎች የሚያገናኘውን መንገድ ሰብረው ዘግተውታል እንዲሁም ወደ ቡሬ የሚወስደውን መንገድ ከተዘጋ አመታት ተቆጥረዋል። ይህ የሽብርተኛ ቡድን ከባድ መሳሪያዎች የታጠቀ ነው። ከዘጠና በላይ ወረዳዎች እና ዞኖች እንዳይገናኙ መንገዶቹን ቆርጦ የመንግስትና የክልሉ ስራዎች እንዲቋረጡ ህዝብ ከHዝብ እንዲቆራረጥ አድርጓል።

አመራሮች ቀን ከብልፅግና ማታ ከኦነግ ሸኔ ይሰበሰባሉ። ይለናል የኛ ቲቪ ዘገባ ይህንን ዘገባ ለማግኘት ከታች ያለውን ቪዲዮ ይመልከቱት ።