ከአንድ የባንክ አካውንት ወደ ሌላ የባንክ አካውንት ማዛወር በሚችሉት የገንዘብ ዝውውር ብዛት ላይ የተጣለው እገዳ ተነሳ

Central Bank Lifts Transfer Restrictions

ብሄራዊ ባንክ ንግድ ባንኮች ከአንድ የባንክ አካውንት ወደ ሌላ የባንክ አካውንት ማዛወር በሚችሉት የገንዘብ ዝውውር ብዛት ላይ ጥሎት የቆየውን እገዳ ማንሳቱን ፎርቹን ጋዜጣ ዘግቧል።

ባንኩ እገዳውን ያነሳው፣ በገንዘብ ዝውውር መጠን ላይ የጣለውን እገዳ ያነሳው፣ እገዳው የታለመለትን ግብ በማሳካቱ እና እገዳው ያስከተላቸውን አሉታዊ ውጤቶች ለመቅረፍ እንደሆነ የባንኩ ከፍተኛ ሃላፊ ሰለሞን ደስታ ተናግረዋል።

The National Bank of Ethiopia (NBE) has removed the limits on bank transfers. Regulators restricted in January 2021, limiting account-to-account transfers to only five a week.

The following month, they placed the same restriction on transfers via mobile and internet banking; using ATMs or POS machines, and mobile money.

“The restrictions have met their target,” Solomon Desta, vice governor of financial institutions at the central bank, told Fortune. “The bank has decided to lift the restrictions to address the negative effects they were to entail.”

ብሄራዊ ባንኩ አንድ የንግድ ባንክ ደንበኛ በሳምንት ውስጥ ከአምስት ጊዜ በላይ ከአንድ አካውንት ወደ ሌላ አካውንት ገንዘብ ማዛወር እንዳይችል ገደቡን የጣለው አምና በጥር ወር ነበር። ባንኩ ገደቡን በሞባይል እና ኢንተርኔት የገንዘብ ዝውውሮች ላይ ጭምር ጥሎት እንደቆየ ይታወሳል።

https://addisfortune.news/news-alert/central-bank-lifts-transfer-restrictions/