የአሜሪካ ኤምባሲ ከሽብር ፈጣሪ መግለጫዎቹ እንዲቆጠብ መንግሥት አሳሰበ

የተለያዩ አገራት ኤምባሲዎች ዜጎቻቸውን ለማውጣት ያደረጉት ሙከራ ስህተት መሆኑ ሲገባቸው ሀሳባቸውን እየቀየሩ ነው ሲል መንግሥት አስታወቀ፡፡ በዓለም ዐቀፉ ማኅበረሰብ የኢትዮጵያን ስም ለማጠልሸት የሚደረገው ሙከራ ፍጹም ስህተት መሆኑ ተገልጿል፡፡
የአሜሪካ ኤምባሲ እንደዚህ ዓይነት መግለጫ ከማውጣት እንዲቆጠብ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ደሲሳ አሳስበዋል፡፡ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት በአዲስ አበባ የሚገኙ ኤምባሲዎችን የማስፈራራት ስራ ከመስራት እንዲቆጠቡም በሰጠው መግለጫ አስጠንቅቋል፡፡

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ እንዲሁም ድርጅቶች የሀሰት መረጃዎችን በማሰራጨት መቀጠላቸውን የኢትዮጵያ መንግስት አስታውቋል።

ከዚህ ቀደም አዲስ አበባ ተከባለች የሚል መረጃን ያሰራጩ እንደነበር ያስታወሰው መንግስት አሁን ደግሞ የሽብር ጥቃት ይፈፀማል የሚል ሀሰት መቀጠሉን ገልጿል።

ኤምባሲው እና የአሜሪካ መንግስት የሀሰት መረጃዎችን ከማስተላለፍ እንዲቆጠቡ የኢትዮጵያ መንግስት አስጠንቅቋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ይህን ማስጠንቀቂያውን ያስተላለፈው ዛሬ በመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት በኩል በሰጠው መግለጫ ነው።