የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከትላንት ጀምሮ ወደ ግንባር በመዝመት እዛው ሆነው አመራር እየሰጡ መሆኑን የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።
–
የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ዙሪያ መግለጫ እየሰጡ ነው።
–
ዶ/ር ለገሰ ፥ ” ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ከትናንትና ጀምሮ በግንባር አመራር እየሰጡ ነው ” ብለዋል። ሌሎችም አመራሮች የህልውና ዘመቻውን በመቀላቀል ወደ ግንባር መዝመታቸውን አሳውቀዋል።
–
መደበኛ ሥራዎች እንዳይስተጓጎሉ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እየተመራ መሆኑን ጠቅሰዋል።
–
ጠቅላይ ሚኒስትሩ መዝመታቸው በርካቶችን ያነቃቃና በርካቶች እንዲከተሏቸው አድርጓል ሲሉም ዶ/ር ለገሰ እየሰጡት ባለው መግለጫ ተናግረዋል።