ከ150 ዓመት በላይ ከእይታ ተሰውረው የቆዩ ታቦታት ወደ ኢትዮጵያ ሊመለሱ መሆኑ ተሰማ

የእንግሊዝ ወታደሮች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ከመቅደላ በ15 ዝሆኖች እና በ200 በቅሎዎች ቅርሶችን ጭነው ዘርፈው ወስደዋል። ቅርሶቹ በተለያዩ የእንግሊዝ ሙዚየሞች እና ዩኒቨርስቲዎች የሚገኙ ሲሆን በግለሰቦች እጅ የሚገኙትም በሚሊዮን ፓውንድ ይቸበቸባሉ::

የመቅደላ ቅርሶች ከ400 በላይ ሲሆኑ ከቅርሶቹ መሀል ዘውድ፣ ታቦታት፣ ወደ 60 የሚጠጉ በብራና የተደጎሱ መንፈሳዊ መጽሐፍት፣ የአጼ ቴዎድሮስ የግል መጽሐፍ ቅዱስ እና የእቴጌ ምንትዋብ ነው ተበሎ የሚገመት ቀሚስ ይገኝበታል::

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስያን ንዋያት ቅድሳት እንዲመለሱ ላለፉት ዓመታት በኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እና በመንግሥት በኩል ጥረት ሲደርግ እንደነበር ቤተክርስቲያኗ አስታውቃለች።

በዚህም ባለፉት ዓመታት ሁለት ታቦታትና ሌሎች ቅርሶች የተመለሱ ሲሆን ቀሪ ታቦታት እና ቅርሶች እንዲመለሱ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕስ ሊቃነ ጳጳሣት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ለብሪቲሽ ሙዚየም ተደጋጋሚ ደብዳቤ ሲጽፉ መቆየታቸውን ገልጻለች።

ቅዱስነታቸው ሙዚየሙ በኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሥርዓተ አምልኮ የሚፈጸምባቸውን ቅዱሣት ንዋያት በተለይም የቃል ኪዳኑን ታቦት ይመለሳሉ በሚል እየጠበቁ መሆናቸውን ገልጸው ፤ሙዚያሙ እነዚህን በዝርፊያ የሄዱ ታቦታት የመመለስ የሞራል ኃላፊነነት እንዳለበት አሳስበዋል።

Ethiopian priests carry tabots during the Timket festival of Epiphany, celebrating the baptism of Christ.ዘ ጋርዲያን ከቀናት በፊት ይዞት በወጣው መረጃ ከ150 ዓመት በላይ ከእይታ ተሰውረው የቆዩ ታቦታት ወደ ኢትዮጵያ ሊመለሱ መሆኑን ገልጿል። የብሪቲሽ ሙዚያም መቼ ታቦታቱን ለመመለስ እንዳሰበ ቁርጥ ያለ ውሣኔ ግን አልተላለፈም።

They are hidden religious treasures that have been in the British Museum’s stores for more than 150 years, never on public display – with members of the public strictly forbidden from seeing them. Now hopes have been raised that Ethiopian tabots, looted by the British after the battle of Maqdala in 1868, could finally be returned home following a new legal opinion and an appeal backed by Stephen Fry, the author Lemn Sissay and the former archbishop of Canterbury George Carey.

Credit : EOTCTV and theguardian.com