በዕድሜ ትንሿ የኮሎራዶ የከተማ ምክር ቤት ተወዳዳሪ ትውልደ ኢትዮጵያዊት ሚሊየነር

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሃና ቦጋለ አሜሪካ ውስጥ በሪል ስቴት ኢንቨስትመንት ስኬታማ ከሆኑ መካከል ትጠቀሳለች። ሚሊየነር ናት። በማኅበራዊ ጉዳዮች ንቅናቄም የሃና ስም ይነሳል። በቅርቡ ደግሞ ፖለቲካውን ተቀላቅላለች። በአሜሪካዋ ኮሎራዶ ግዛት ውስጥ በምትገኘው የአውሮራ ከተማ ውስጥ ለምክር ቤት መቀመጫ እየተወዳደረች ትገኛለች።…