ሰሚ አካል አላገኘንም ! – ከትግራይ ዩንቨርስቲዎች የተፈናቀሉ ተማሪዎች

በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች መንግሥት መፍትሔ እንዲሰጣቸው ጠየቁ።

በሰሜን ኢትዮጵያ ባለው ግጭት ምክንያት በክልሉ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የወጡ ተማሪዎች እና ወላጆቻቸው፣ ቅሬታቸውን ለማሰማት ዛሬ ወደ ትምህርት ሚኒስቴር ቢሔዱም ሰሚ አካል አላገኘንም ብለዋል፡፡

የአሜሪካ ድምጽም ተማሪዎች ስላቀረቡት ቅሬታ ምላሽ ለመጠየቅ የሚኒስቴሩን አመራሮች ለማግኘት ያደረገው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም፡፡