በኦሮሚያ ክልል ሁሮ ጉድሩ ወለጋ የአማራ ብሔር ተወላጆች በሸኔ ታጣቂዎች በአካባቢው መኖር አትችሉም፤ ለቃችሁ ውጡ ተባሉ


የመረጃ ቲቪን 24/7 የሳተላይት ስርጭት በመደገፍ የኢትዮጵያ ህዝብ አማራጭ እና ትክክለኛ መረጃ በማግኘት እራሱን ከተጋረጠበት አደጋ መከላከል እንዲችል እናግዝ። በአሁኑ ወቅት ከመረጃ ቲቪ በስተቀር ሌሎች ሁሉም በኢትዮጵያ ያሉ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የመንግስት የፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ናቸው። ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ የከፈትነው የመረጃ ቲቪ የሳተላይት ስርጭት የአንድ ዓመት ወጪን ለመሸፈን ነው። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን ድጋፍዎትን ይለግሱ » https://gofund.me/54405070
በኦሮሚያ ክልል ሁሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ጃርቴ ወረዳ ውስጥ የአማራ ብሔር ተወላጆች በሸኔ ታጣቂዎች በአካባቢው መኖር አትችሉም፤ ለቃችሁ ውጡ የተባሉ መሆኑን እና በዚህም በወረዳው በሚገኙ ሀሮሎጎ፣ ጃንጂማረ፣ ሆሮዳዴ፣ አብዲ ዳንዲ እና አሣ ጉዲና ከተባሉ አምስት ቀበሌዎች ሙሉ በሙሉ ያላቸውን እርሻ መሬት እንዲሁም ሌሎች ንብረቶች ለቀው የወጡ መሆኑን፣ በተቀሩት ስድስት የሚሆኑ ቀበሌዎች ያሉ ነዋሪዎችም በእነዚሁ ታጣቂዎች አካባቢውን ለቃችሁ ውጡ ተብለው ማዋከብ እና ጫና እየተደረገባቸዉ እንደሚገኝ ለኢሰመጉ የደረሱ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
በተመሳሳይ በሰንቦ-ጨፌ ቀበሌ ውስጥ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በርካቶች በሸኔ ታጣቂዎች የተገደሉ ሲሆን የተቀሩትም በሻምቡ በኩል አድርገው ወደተለያዩ የአማራ ክልል አካባቢዎች ለመሄድ ሲሞክሩ ተከልክለው ችግር ላይ እንደሚገኙ የሚጠቁሙ መረጃዎች ለኢሰመጉ ቀርበዋል::
May be an image of text
May be an image of text

No photo description available.