ከሀገር እንዳልወጣ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተከልክያለሁ ክስ ተመስርቶብኛል – አብርሐ ደስታ

የትግራይ ጊዜያዊ እስተዳደር ተብሎ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የተቋቋመው በዶክተር እብርሃም በላይ የሚመራው ካቢኔ አባል በመሆን የሰራተኛና ማሕበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ የነበረው የአረና ሊቀመንበር አብርሃ ደስታ  አዲስ አበባ ነው ያለሁት። ከሀገር እንዳልወጣ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድቤት ተከልክያለሁ። ሲል በማሕበራዊ ገጹ የጻፈ ሲሆን ከዓመታት በፊት የታሰርኩበትና ነፃ የወጣሁበት ክስ እንደገና ተቀስቅሶ እንድከላከል ለሐምሌ 20, 2013 ዓም ቀጠሮ ተሰጥቶኛል።ብሏል።

አቶ አብርሃ ደስታ በፌስቡክ ገጹ የሚከተለውን አስፍርዋል።

እንደምን ሰነበታችሁ?
አዲስ አበባ ነው ያለሁት።
ከሀገር እንዳልወጣ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድቤት ተከልክያለሁ።
ከዓመታት በፊት የታሰርኩበትና ነፃ የወጣሁበት ክስ እንደገና ተቀስቅሶ እንድከላከል ለሐምሌ 20, 2013 ዓም ቀጠሮ ተሰጥቶኛል።
ከሐምሌ 20 በሓላ ከጠፋሁ ያው ታስሬያለሁ ማለት ነው።
ሳልታሰር ከቆየሁ መንገድ ሲከፈት ወደ ትግራይ እመለሳለሁ!
ሰላም!