እስራኤል ፊት የነሳቻት ግብፅ የግድቡን ጉዳይ ቻይና እንድትፈታላት መጠየቋ ተገለጸ


የመረጃ ቲቪን 24/7 የሳተላይት ስርጭት በመደገፍ የኢትዮጵያ ህዝብ አማራጭ እና ትክክለኛ መረጃ በማግኘት እራሱን ከተጋረጠበት አደጋ መከላከል እንዲችል እናግዝ። በአሁኑ ወቅት ከመረጃ ቲቪ በስተቀር ሌሎች ሁሉም በኢትዮጵያ ያሉ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የመንግስት የፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ናቸው። ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ የከፈትነው የመረጃ ቲቪ የሳተላይት ስርጭት የአንድ ዓመት ወጪን ለመሸፈን ነው። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን ድጋፍዎትን ይለግሱ » https://gofund.me/54405070
  • ተመሳሳይ ጥያቄዋ በእስራኤል ውድቅ የተደረገባት ግብፅ አሁን ደግሞ የግድቡን ጉዳይ ቻይና እንድትፈታላት መጠየቋ ተገለጸ
  • ቻይና ሁሉንም ወገን ያማከለ መፍትሄ ለመስጠት እንደምትሰራ አስታውቃታለች
ከሰሞኑ ለእስራኤል ተመሳሳይ ጥያቄ አቅርባ በእስራኤል ውድቅ የተደረገባት ግብፅ ቻይና በአባይ ግድብ ዙሪያ የተፈጠረውን አለመግባበት እንድትፈታላት መጠየቋ ተገለጸ፡፡ ግብፅ በአባይ ግድብ ዙሪያ ያለውን አለመግባባት ቻይና ትፈታዋለች የሚል ትልቅ እምነትና ተስፋ እንዳላት በፕሬዝዳንቷ በኩል መግለጿን አል ሞኒተር ዘግቧል። ግብፅ የሕዳሴው ግድብን ጉዳይ ይዛ ወደ ቻይና ፊቷን ማዞሯን የጠቀሰው ዘገባው፤ በታላቁ የህዳሴ ግድብ የውሃ አያያዝ ዙሪያ ስምምነት ላይ የሚያደርስ ድርድር ለማድረግ ግብፅ በቻይና ላይ እምነት እንዳላት ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ መግለጻቸውን አስነብቧል።
ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታህ አል ሲሲ በዚሁ ሳምንት በሰሜን ምዕራብ የባህር ዳርቻዋ አላሜይን ከተማ ከቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ጋር ውይይት ማድረጋቸውና ይሄንን ጉዳይ እንዳነሱላቸው ነው ዘገባው ያስታወቀው።
ዋንግ በበኩላቸው ቻይና የሁሉንም ወገኖች ፍላጎት ያማከለ መፍትሄ እንደምትፈልግ መግለፃቸው ተዘግቧል፡፡ ግብጽ የግድቡን ጉዳይ ወደተለያዩ አገራትና ተቋማት እየወሰደች ቢሆንም እስካሁን ይህ ነው የሚባል ምላሽ አላገኘችም፤ በቅርቡም ጉዳዩን ለእስራኤል አቅርባ እስራኤል የግብጽን ጥያቄ ውድቅ ማድረጓ ይታወሳል።
በተመሳሳይም ጉዳዩን ወደተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ወስዳ እንዲታይ ያደረገች ቢሆንም፤ ምክር ቤቱ ጉዳዩ መታየት ያለበት በአፍሪከ ህብረት ጥላ ስር ነው የሚለውን የኢትዮጵያ መከራከሪያ መደገፉ አይዘነጋም። ኢትዮጵያ አሁንም ድረስ የያዘቸው አቋም፤ ጉዳዩ መፈታት ያለበት በድርድር እና በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር ነው የሚል መሆኑና ይህንንም በርካታ የዓለም አገራትና ተቋማት መደገፋቸው ይታወቃል።
(ኢ ፕ ድ)