ሕወሓት የማይካድራ ዓይነት ጭፍጨፋ በሑመራ ከተማ ለመፈጸም ያሰበው ዕቅድ ተጋለጠ


የመረጃ ቲቪን 24/7 የሳተላይት ስርጭት በመደገፍ የኢትዮጵያ ህዝብ አማራጭ እና ትክክለኛ መረጃ በማግኘት እራሱን ከተጋረጠበት አደጋ መከላከል እንዲችል እናግዝ። በአሁኑ ወቅት ከመረጃ ቲቪ በስተቀር ሌሎች ሁሉም በኢትዮጵያ ያሉ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የመንግስት የፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ናቸው። ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ የከፈትነው የመረጃ ቲቪ የሳተላይት ስርጭት የአንድ ዓመት ወጪን ለመሸፈን ነው። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን ድጋፍዎትን ይለግሱ » https://gofund.me/54405070
ሕወሓት የማይካድራ ዓይነት ጭፍጨፋ በሑመራ ከተማ ለመፈጸም ያሰበው ዕቅድ ተጋለጠ
(ኢ.ፕ.ድ) – በዕቅዱ መሠረት ከትግራይ ክልልና ከሱዳን አስርጎ በሚያስገባቸው ሠርገ ገቦች አማካኝነት ጭፍጨፋውን እንደሚፈጽም ገልጧል።
ይሄንን ለማድረግ እንዲመች በራያና አፋር በኩል ተደጋጋሚ ትንኮሳ በመፈጸም የመከላከያ ሠራዊቱንና የአማራ ልዩ ኃይልን ትኩረት ለማዛባት ሞክሯል።
የጦር ኃይል ወደ ራያና አፋር ሲሰባሰብና የምዕራቡ ኃይል ሲሳሳ በዚያ በኩል ጥቃት በመክፈት ድርጊቱን ለመፈጸም ማቀዱን ያሳያል።
ሕወሓት ከሰሞኑ የአማራ ልዩ ኃይልና መከላከያ በሑመራ ጭፍጨፋ እንደሚፈጽሙ በማኅበራዊ ሚዲያ ማሠራጨት እንደሚጀምር ዕቅዱ ያሳያል ሲል የመንግስት የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ ማስጠንቀቂያ 1 በሚል ባወጣው ጽሁፍ አስታውቋል።

Image