ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥ ሆነው ተሾሙ


የመረጃ ቲቪን 24/7 የሳተላይት ስርጭት በመደገፍ የኢትዮጵያ ህዝብ አማራጭ እና ትክክለኛ መረጃ በማግኘት እራሱን ከተጋረጠበት አደጋ መከላከል እንዲችል እናግዝ። በአሁኑ ወቅት ከመረጃ ቲቪ በስተቀር ሌሎች ሁሉም በኢትዮጵያ ያሉ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የመንግስት የፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ናቸው። ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ የከፈትነው የመረጃ ቲቪ የሳተላይት ስርጭት የአንድ ዓመት ወጪን ለመሸፈን ነው። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን ድጋፍዎትን ይለግሱ » https://gofund.me/54405070
የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር ለተለያዩ ጄኔራሎችና ከፍተኛ የጦር መኮንኖች የሥራ ምደባ ሰጡ። የክልሉ ርእሰ መሥተዳድር ጽሕፈት ቤት ለአሚኮ እንዳሳወቀው ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የክልሉ ልዩ ኃይል አዛዥ ሆነው ተመድበዋል። ሌሎች ጄኔራሎችና ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ልዩ ልዩ የጸጥታ ተቋማትን እንዲመሩ በርእሰ መሥተዳድሩ ምደባ ተሰጥቷል። በዚህም መሰረት፦1ኛ. ጀኔራል ተፈራ ማሞ የልዩ ሃይል አዛዥ፣
2ኛ. ጀኔራል መሰለ በለጠ ም/አዛዥ ለኦፕሬሽናል፣
3ኛ.ኮሚ/ ቢሰጥ ጌታሁን ም/ አዛዥ ለኦፕሬሽን፣
4ኛ. ኮሚ/ አርአያ ካሴ ም/ አዛዥ ለኦፕሬሽናል፣
5ኛ. ጀኔራል ማሞ ግርማይ ም/ አዛዥ ለሎጀስቲክስ፣
6ኛ.ጀኔራል ዘዉዱ እሸቴ ም/አዛዥ ለሎጀስቲክስ፣
7ኛ. ጀኔራል አበራ ተ/ዮሃንስ ም/አዛዥ ለአስተዳደር፣
8ኛ. ረ/ ኮሚሽነር መለሰ ደገፋዉ ም/ አዛዥ ለአስተዳደር፣
9ኛ. ጀኔራል አዳምነህ መንግስቴ የሰላምና ደህንነት ቢሮ ሃላፊ ልዩ ረዳት፣ ሆነው ተመድበዋል።

May be an image of 1 person and beard